“Our true nationality is mankind.”H.G.

የአንበጣ መንጋ በ2011 ክረምት ወራት 3.5 ሚሊዮን ኩንታል እህል እምሽክ አድርጓል

ሰኔ 2011 አጋማሽ ላይ ከየመን በሶማሌ ላንድ አድርጎ ወደ አፋር እና ሶማሌ ክልል የገባው የአንበጣ መንጋ ሊገኝ ከታቀደው ምርት 2 በመቶውን ወይንም 3.5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ማውደሙ ተገለጸ።

መንጋው ከ70 እሰከ 100 ፐርሰንት ምርት ሊያጠፋ ይችል ነበር ያሉት በግብርና ሚንስቴር የዕጽዋት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታምሩ ከበደ በተደረገው ርብርበብ የደረሰው ጉዳት አነስተኛ ሊሆን ችሏል ብለዋል።

የአንበጣ መንጋው ሶማሌ እና አፋር ክልል ላይ የመከላከል ሥራ ሲሠራ ቢቆይም ከአፋር የተረፈው ወደ ወሎ እና ደቡብ ትግራይ ወጥቶ ማሳ ላይ ጉዳት አድርሷል። ከሶማሌ ክልል በመነሳት ደግሞ ምስራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ ላይ ጉዳት አድርሶ ነበር ብለዋል።

ባለፉት ወራት በተሠራው የመከላከል ሥራ ዓመቱን ሙሉ በግጦሽ እና ቁጥቋጦ እንጂ በሰብል ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ሲሉ ገልጸዋል።

ሆኖም በግጦሽ እና ቁጥቋጦ ላይ ያደረሰውን ጉዳት ቦታዎቹ ስለማያመቹ ማጥናት እንዳልተቻለ አስታውቀዋል።

ሰኔ 2011 ጀምሮ በአፋር እና በሶማሌ ክልል የመከላከል ሥራ ቢሠራም፣ ለመድረስ አስቸጋሪ ከሆኑ አካባቢዎች ላይ አንበጣው በመነሳት በምስራቅ ኦሮሚያ፣ ድሬዳዋ እንዲሁም በምዕራብ አማራ ወሎ፣ ቃሉና አርጎባ አካባቢዎች መጠነኛ የሆነ የምርት መቀነስ አድርሶ ነበር ሲሉ ተናግረዋል።

Related stories   የዘረኝነት ጥግ “እናት ነኝ የሌሎች ህፃናት ወላጆችን ግን ገደልኩ”

በሁለተኛ ዙር ደግሞ ህዳር እና ታህሳስ ላይ በምስራቁ የሃገሪቱ ክፍል የተከሰተ ቢሆንም ሰብል በመሰብሰቡ ጉዳት አላደረሰም።

በበልግ ምርት ወቅት በደቡብ ኢትዮጵያ በዳሰነች፣ ኛንጋቶም፣ ኦሞ እና የኬንያ አቅራቢያ አካባቢዎች ቢከሰትም በበልግ ሰብል ላይ ጉዳት ሳያደርስ መከላከል መቻሉን አቶ ታምሩ ለቢቢሲ ገልጸዋል።

በ2012 የክረምት ወራት በአፋር እና በሶማሌ ላይ በሚገኙ ሰፊ አካባቢዎች፣ በአውሮፕላን የተጋዘ የአሰሳ እና መከላከል በሰው ሃይል እና በመኪና እየተሠራ ነው።

“አምና በጣም ጥሩ የመከላከል ሥራ ተሰርቷል። ሁሉንም የሚያስመሰግን ሥራ ነው። ከአምና የሄሊኮፕተር እና ተሽከርካሪ ቁጥር ጨምረናል። የክልሎችም ተሳትፎ የተሻለ ነው ዘንድሮ” ብለዋል።

የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል ሰዎችን ከማሰማራት ጎን ለጎን በእጅ የሚያዙ መሣሪያዎች፣ በርካታ መኪናዎች፣ 4 ለኬሚካል ርጭት የሚሆኑ እና ሁለት የአሰሳ ሄሊኮፕተሮች ዝግጁ ሆነዋል።

Related stories   የዘረኝነት ጥግ “እናት ነኝ የሌሎች ህፃናት ወላጆችን ግን ገደልኩ”

“አሁን በድሬዳዋ የመከላከል ቤዝ አንድ አውሮፕላን አለ። በሰሜን ምስራቅ ኮምቦልቻም አንድ አውሮፕላን አለ። በጅቡቲ እና ከኤርትራም የሚገባም ስለሚኖር ሰመራም አለ። ሰፊ የመከላከል ሥራው አለ፤ አሁንም ይቀጥላል” ብለዋል።

የበረሃ አንበጣ በዛፍ ላይ

አሁን በዋናነት አንበጣው ያለው በሃገሪቱ ምስራቅ እና ሰሜን ምስራቅ በሶማሌ እና አፋር ክልሎች ነው። ከሶማሌ የሚነሳው አንበጣ ባሌ እና ሐረርጌ አካቢዎችን የሚወር ሲሆን ከአፋር የሚነሳው ደግሞ ወሎ እና ደቡብ ትግራይ ነው የሚወረው። የመከላከል ስራውም በሁለት ሄሊኮፕተር እና በአንድ የአሰሳ አውሮፕላን ሶማሌ እና አፋር ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ ነው ያለው” ሲሉ አስረድተዋል።

አንድ አቶ ታምሩ ከሆነ በቅርብ ጊዜም በኬንያ በኩል ከቱርካና ሐይቅ ተነስቶ ደቡብ ኦሞ በኩል የሚገባ አምበጣ ስላለ እሱን ለመጠባበቅ አርባምንጭም ላይ ሄሊኮፕተር ተዘጋጅቷል።

መረጃ ለመለዋወጥ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በቅርበት እየተሠራ ሲሆን በተለይ በአፋር ክልል ዳጉ የሚባለው የመረጃ መለዋወጫ ባህላዊ ዘዴን፣ እንዲሁም በሶማሌ እና በኦሮሚያ ደግሞ ስካውቶችን በመጠቀም መረጃዎችን እያገኘን የሚወሰደው እርምጃ ይወሰዳል ሲሉ ገልጸዋል።

Related stories   የዘረኝነት ጥግ “እናት ነኝ የሌሎች ህፃናት ወላጆችን ግን ገደልኩ”

የመከላከል ሥራው ‘ጥሩ’ የሚባል ቢሆንም ከሌሎች ሃገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ እና ከኢትዮጵያም ወደ ጎረቤት ሃገራት የሚንቀሰቀስ አንበጣ መንጋ መኖሩን ገልጸዋል። ሆኖም ከሚወጣው ይልቅ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው ይበልጣል ብለዋል።

“በጣም ጥሩ ስራ ቢሰራም ወደ ኤርትራ እና ወደ ሌላም የሚያመልጥ ይጠፋል አይባልም። ከኬንያ፣ ከሶማሌ ላንድ እና ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ እየገባ ነው። በንፋስም ወደ ኤርትራ፣ ሰሜንና እና ወደ ምስራቅ የሃገሪቱ ክፍል የመውጣት ዕድል አለው” ብለዋል።

ችግሩን ለመቆጣጠር እንዲሁም ወደ ሌሎች አገራት እንዳይዛመት እና ጉዳት እንዳያደርስ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚሰራው ጠንካራ የመከላከል ሥራ ጎን ለጎን ከጎረቤት አገራት ጋር የመረጃ ልውውጥ ለማድረግ ዓለም አቀፉን የምግብና ግብርና ድርጅት /ፋኦ/ ያካተተ የጋራ ማዕከል ተቋቁሟል። በማዕከሉ በኩል የቅድመ ትንበያ መረጃዎች ለአካባቢው አገራት አበየጊዜው እየተሰራጨ ይገኛል ሲሉ ገልጸዋል።

ቢቢሲ አማርኛ 

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0