የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ በሱዳን ጉብኝት እያደረጉ ከሚገኙት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ጋር መወያየታቸውን ፋና ቢቢሲን ጠቅሶ ዘግቧል። ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጉዞ በፊት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ፣ ከዛም የኤርትራው ጀነራል ካርቱም ተገኝተው እንደነበር የሚታወስ ነው።

እስካሁን በይፋ የተባለ ምንም ነገር ባይኖርም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓምፒዮ ካርቱም ለይፋዊ ጉብኝት መገኘታቸውና የጠቅላይ ሚኒስትር ድንገተኛ ጉዞ መደራረብ ጉዳዩ በዝምታ የሚታለፍ አልሆነም። በቀጣናው ሊተገበር የታቀደውን አዲስ የትሥሥርና የሰላም እቅድ እንዲመሩ ሃላፊነት የተሰጣቸው አብይ አህመድ ጉዟቸው በጋራ ጥቅም ላይ ውጤታማ እንደነበር በይፋ ቢናገሩም ተጨማሪ ማብራሪያ አልሰጡም:;

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዶክ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፖምፒዮ ጋር በሁለትዮሽ እና የተለያዩ የድጋፍ ጉዳዮች ዙሪያ ቀጥተኛ እና ግልጽ ውይይትን አድርገናል ብለዋል። ከዚያም ባለፈ ሃገራቸው ከአሜሪካ ሽብርተኝነትን ከሚደግፉ ሀገራት ጥቁር መዝገብ የምትሰረዝበትን ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስታወቁት። ሱዳን የአልቃይዳው መሪ ኦሳማ ቢን ላደን በሀገሯ ከኖረበት ከ1990ዎቹ ጊዜ ጀምሮ ሽብርተኝነትን ከሚደገፉ ሃገራት ዝርዝር ውስጥ ተካታ ቆይታለች። 

Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

ስለሆነም ሱዳን የተጣለባት ማዕቀብ እንዲነሳላትና ከዚህ ዝርዝር ላይ እንድትሰረዝ ትፈልጋለች ። ለ30 አመታት ሱዳንን የመሩት ፕሬዚዳንት ኦማር ሃሰን አል በሽር በህዝባዊ ተቃውሞ ከስልጣን ከወረዱ በኋላ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት እየተሻሻለ መምጣቱም ነው የሚነገረው ። 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ጋር ተወያይተዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተመራ የልኡካን ቡድን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በዛሬው እለት ሱዳን ካርቱም መግባቱ ይታወቃል።

በጉብኝቱም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ጋር ተገናኝተው በሁለትዮሽና በሌሎች ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

Related stories   Egypt-Sudan alliance shifting in row with Ethiopia over Nile dam

በውይይታቸውም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ፥ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ ወዳጅነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን አንስተዋል።

“ኢትዮጵያ እና ሱዳን አንድ ህዝብ፤ አንድ ቤተሰብ ነን” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ፥ ከህዳሴ ግድብ እና ከድንበር ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጉዳዮች ተከታታይነት ባላቸው ውይይቶች የሚፈቱ ናቸው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ውይይቱን አስመልክቶ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃም፥ “ዛሬ በካርቱም ባደረግነው ውይይት ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ያላትን አጋርነት ለጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ በድጋሚ አረጋግጨላቸዋለሁ” ብለዋል።

“የሁለትዮሽ ትሥሥራችንን ለማጠናከር ያሉንን ሰፊ አማራጮች በምንፈትሽበት በዚህ ወቅት፣ ለኢኮኖሚያዊ ትብብር፣ የጋራ እድገት እና ቀጣናዊ መረጋጋት ያለን ቁርጠኝነት ይቀጥላል” ሲሉም ገልፀዋል።

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክም በውይይቱ ላይ፥ ኢትዮጵያና ሱዳን ዘመናትን የተሻገረ ወዳጅነት እንዳላቸው በመጥቀስ፤ ግንኙነቱ ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ እንዲል እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

Related stories   የትህነግ "ውሮ ወሸባዬ" - የመንግስት ሩጫ - የሃላኑ የኢትዮጵያን ቋንጃ የመበጠስ የእባብ አካሄድና ባንዳዎች!

ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ የመጠቀም መብቷን ሱዳን እንደምታከብር ጠቁመው፤ በግድቡ ዙሪያ ያሉ ጉዳዮች በድርድርና ውይይት መፈታት እንዳለባቸውም አንስተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በካርቱም ቆይታቸው ከሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሌተናል ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩም ይጠበቃል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *