የስነምግባ ችግር ያለባቸውን የፌደራል ፖሊስ አባላት ማሰናበቱን ባስታወቀ ቀናት ውስጥ ሰራዊቱ በቀላሉ ገበያ ላይ የማይገኝ መለያ ልብስ እንዲለብስ መወሰኑንን ኮሚሽነር ጀነራል እንዳሻው ጣሰው አስታወቁ። ዝርዝር ማብራሪያው የፊታችን ቅዳሜ ለህዝብ ይፋ ይሆናል ተብሏል።
“ኮሚሽነር ጀነራሉ ቃል በቃል ባይናገሩም የፌደራል ፖሊስ ትጥቅ የታጠቁ ሃሎች የተለያየዩ ወንጀሎችን እየሰሩ የቪዲዮ ምስል በመቅረጽ ፣ የሰዎችን ህይወት በሚዘገንን መልኩ በማጥፋት፣ ዝርፊያ በማካሄድና ህዝብን የሚያሸብሩ ድርጊቶችን በመፈጸም በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሆን ብሎ በመለጠፍ አንዱ ከሌላኛው ብሄርና የሃይማኖት ተከታይ ጋር እንዲጋጭ ሰፊ ስራ በሴረኞች አማካይነት ተፈጽሟል። ወደፊትም ይፈጸማል። አምራቾቹም ለጸጉረ ልውጥ ሃይላት ሆን ተብሎ እንዲከፋፈል ያደርጉታል ”
የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብሱን ሊቀይር መሆኑን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንዳሻው ጣሰው መግለጹ ፋና ዘገበ።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በ2012 ዓ.ም በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸምና የ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫን አስመልክቶ ለሁለት ቀናት ሲያካሄድ የነበረው ግምገማ ዛሬ ተጠናቋል።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንዳሻው ጣሰው የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብስ እንደሚቀየርና ጉዳዩን አስመልክቶ በመጪው ቅዳሜ ሰፊ ማብራሪያ በኮሚሽኑ እንደሚሰጥ በዚሁ ወቅት ገልጸዋል።
ለደንብ ልብሱ መቀየር አሁን ያለው የደንብ ልብስ በቀላሉ የሚገኝ ከመሆኑ በተጨማሪ በስነ ምግባር ችግር የተባበሩ ፖሊሶች ልብሱን ለብሰው እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን በምክንያትነት ጠቅሰዋል።
በዚህም የደንብ ልብሱን በመልበስ የሚፈጸሙ ወንጀሎችና ዝርፊያዎች መበራከታቸውን ነው ያስታወቁት።
በሌላ በኩል በ2013 ዓ.ም አዳዲስ የፖሊስ ዘርፎች በሙከራ ደረጃ ወደ ሥራ ሊገቡ እንደሆነ ኮሚሽነር እንዳሻው አያይዘው ገልጸዋል።
የዩኒቨርሲቲ፣ የቱሪዝምና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ፖሊስ በሚሉ ዘርፎች ወደ ሥራ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
በሙከራው የሚገኙ ልምዶችን በመውሰድ የፖሊስ ዘርፎቹ ወደፊት በዘላቂነት ሊሰራባቸው የሚችልበት ሁኔታ እንደሚኖር መግለፃቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።
ከላይ ያለውን የፋናን ዘገባ አስመልክቶ የዛጎል ዘጋቢ ያነጋገርናቸው የፌድራል ፖሊስ አባል ” “ኮሚሽነር ጀነራሉ ቃል በቃል ባይናገሩም የፌደራል ፖሊስ ትጥቅ የታጠቁ ሃሎች የተለያየዩ ወንጀሎችን እየሰሩ የቪዲዮ ምስል በመቅረጽ ፣ የሰዎችን ህይወት በሚዘገንን መልኩ በማጥፋት፣ ዝርፊያ በማካሄድና ህዝብን የሚያሸብሩ ድርጊቶችን በመፈጸም በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሆን ብሎ በመለጠፍ አንዱ ከሌላኛው ብሄርና የሃይማኖት ተከታይ ጋር እንዲጋጭ ሰፊ ስራ በሴረኞች አማካይነት ተፈጽሟል። ወደፊትም ይፈጸማል። አምራቾቹም ለጸጉረ ልውጥ ሃይላት ሆን ተብሎ እንዲከፋፈል ያደርጉታል ” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በተመሳሳይ ዜና
#FBC