“Our true nationality is mankind.”H.G.

የመሬት ጉዳይ እንጨርሳለን በሚል ጉቦ ሲቀበሉ የተገኙ ዋና ስራ አስፈጻሚና ሌሎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

NtJDO

 በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ከመሬት ጋር በተያያዘ አገልግሎት ለማግኘት ወደ ቢሮው የሄዱ ተገልጋዮችን ጉዳይ እንጨርሳለን በሚል ጉቦ ሲቀበሉ የተገኙ የወረዳውን ስራ አስፈጻሚ እና የወረዳው ስነ-ምግባር መኮንን ያካተተ ቡድን በቁጥጥር ስር ውሏል።
 
በወንጀል ድርጊቱ ውስጥ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ካሉት ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ከተዘረጋው ሰንሰለት በተጨማሪ ደላሎችም ይገኙበታል ነው የተባለው።
 
ለከንቲባ ፅህፈት ቤት በመጣ የተገልጋይ ጥቆማ የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ጋር በመተባበር ለአገልግሎት እንዲከፈላቸው የጠየቁትን ገንዘብ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል።
 
ህብረተሰቡም በህጋዊ መንገድ ማግኘት የሚገባውን አገልግሎት ከተማ አስተዳደሩ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ጠቁሞ÷ ጥቆማውን ላደረሡን ተገልጋይ ያለንን ታላቅ አክብሮት እና ምስጋና እናቀርባለን ብለዋል።
 
በመንግስት መዋቅር ውስጥ ተሠግስገው በአቋራጭ ገንዘብ በመቀበል በህገ-ወጥ መንገድ አገልግሎት እንሠጣለን የሚሉ አካላትን በማጋለጥ ህብረተሠቡ ጥቆማውን በመስጠት ግዴታውን እንዲወጣ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል ።
 
የወንጀል ድርጊቱን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃዎች በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ በኩል በቀጣይ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረጉ ከከንቲባ ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬተሪያት ቢሮ ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል።
 
#FBC

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ይናገር ደሴ -"እየተዶለተብንና እየተቀመመልን ያለው ኢትዮጵያን የመበተን ሴራ ጉዳይ ለእኛ ኢትዮጵያውያን አዲስ ነገር አይደለም"
0Shares
0