ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

የአዳነች አቤቤ ካቢኔ የኮንዶሚኒየም ቤት ባለቤት ለመሆን ገንዘብ ቆጥበው ሲጠባበቁ ለቆዩ ተጨማሪ አዲስ መፍትሄ አቀረበ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅረፍ ለ20/80 እና 40/60 ተመዝጋቢ ሆነው ቤት ላልደረሳቸው ፍላጎት እና አቅም ያላቸው ነዋሪዎች በማህበር ተደራጅተው የጋራ ቤት ለመገንባት እንዲችሉ አማራጭ የመፍትሄ ሀሳብ አስተላልፏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በዛሬው ዕለት 30ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል። ጉባኤው በተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ የተወያየ ሲሆን÷ በከተማዋ የሚታየውን የመኖሪያ ቤትና የትራንስፖርት ችግር ከመፍታት አንፃር አፅንኦት ሠጥቶ ተወያይቷል።

ችግሮቹን ለመፍታትም ካቢኔው በተለያዩ አማራጮች ሃሳቦች ዙሪያ ሠፊ ውይይት አድርጎ ውሳኔውን አስተላልፏል።

Related stories   በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ከተሞች የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የሽብር ቡድን በቁጥጥር ስር ዋለ- ትህነግ “ክብሪት” የተባለ ገዳይ ቡድን ማቋቋሙ ታወቀ፣

በዚሁ መሰረት የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅረፍ ለ20/80 እና 40/60 ተመዝጋቢ ሆነው ቤት ያልደረሳቸው ፍላጎት እና አቅም ያላቸው ነዋሪዎች በማህበር ተደራጅተው የጋራ ቤት ለመገንባት እንዲችሉ ከተማ አስተዳደሩ የመሬት አቅርቦት በማድረግ እራሳቸው እንዲገነቡ ለማድረግ አማራጭ የመፍትሄ ውሳኔ አስተላልፏል።

ከዚያም ባለፈ በከተማዋ የሚስተዋለውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ 400 አውቶቢሶች ግዢ በልዩ ሁኔታ እንዲከናወን እና በብልሽት አገልግሎት መስጠት ያቆሙ 125 አውቶቡሶች በአስቸኳይ አስፋላጊው ጥገና ተደርጎላቸው ከአዲስ አመት የመጀመሪያ ቀናት ጀምሮ አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ውሳኔ ተላልፏል ።

Related stories   ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ የ200 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራረሙ

የማህበር ቤት ልማት መመሪያ እና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ቢሮ በቀጣይ ዝርዝር መረጃ የሚሰጥ መሆኑን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪያት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

#FBC