የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት፣ አስፈፃሚ አካላት እና የምርጫ ኮሚሽን ምርጫን በሚመለከት ያወጣው የምርጫ አዋጅ ቁጥር 351/2012 ያሳለፏቸው ውሳኔዎች እና የፈፀሟቸው ተግባራት ከሕገ መንግስቱ ጋር የሚቃረኑ በመሆናቸው በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 9(1) መሰረት እንዳልተደረጉ የሚቆጠሩ፣ የማይፀኑ እና ተፈፃሚነት የሌላቸው ናቸው በማለት የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሙሉ ድምጽ የመጨረሻ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

 
ህወሃት የሚመራው መንግስት ህጋዊ ልዕልና የመከነ መሆኑንን የፌዴሪሽን ምክር ቤት ህግ በመጥቀስ፣ ህግ በመተላለፍ የፈጸሙትን ተግባራት በመዘርዘር አስታወቀ። በውሳኔው  ህወሃት የፌደሬሽን ምክር ቤት ለሰጠው ውሳኔ አለመገዛቱ ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ አመክቷል።
ውሳኔውን ያዩ የህግ ባለሙያ እንዳሉት ይህ ማለት የህወሃት ቡድን ኢ-ህገመንግስታዊ ሆኗል ተፈርጇል እንደማለት ነው። ስለዚህ ኢ- ህገመንግስታዊ ከሆነ ቡድን ጋር የሚደረገው ግንኙነት ልክ በሂሳብ ቀመር ውጤቱ ኔጋቲቭ ይሆናል ማለት ነው። ብለዋል።
ፉከራ የሌለበት ለስላሳ ነገር ግን የተጠቀሱት አንቀጾች ሲብላሉ ውሳኔው ከባድ እንደሆነ ያመለከቱት የህግ ባለሙያው፣ በውሳኔው መሰረት ይህ ቡድን የሚሰራውና የሚያቅዳቸው ሁሉ “እንዳልተደረጉ የሚቆጠሩ፣ የማይፀኑ እና ተፈፃሚነት የሌላቸው” መባላቸው የውሳኔው ቁልፍ ጉዳይ ነው።
የህግ ባለሙያው እንዳሉት ምርጫው እንዲራዘም ተወስኖ ሳለ ህወሃት ከውሳኔው አፈንግጦ መንቀሳቀሱ ህጋዊ ልዕልውን አሳጥቶታል። ህጋዊ ልዕልናውን ያጣ ቡድን ምን ተብሎ እንደሚሰየም ማንም እንደሚያውቀው ግለጸዋል።
“ሌላው ውናው ጉዳይ በህወሃት በሃይል ተውጠን ማንነታችን ተገፏል” የሚሉ ወገኖች ጉዳይ ትኩረት እንደሚሰጠው ውሳኔው ግልጽ አድርጓል። በለሰለሰ ቋንቋ አውግዟል። ይህንን አስመክቶ የህግ ባለሙያው በውሳኔው ስር በተዘረዘሩት አንቀጾች መሰረት የፌደራል መንግስት በተጠቀሱት አካባቢዎች ጣልቃ እንደሚገባ አመላካች መሆኑንን አሳይተዋል። 
ህወሃት ይህንን ውሳኔ ማስቀየር የሚችለው ወደ ህጋዊ መንገድ በመለስ ብቻ እንደሆነ በግልጽ መቀመጡን ያወሱት የህግ ባለሙያው፣ የሰላም ንግግርም ቢሆን ህጋን ከማክበር በሁዋላ በመሆኑ ውሳኔው ከባድ እንደሆነ፣ ተከታታይ ጉዳዮች እንደሚኖሩ የሚያሳይ ነው።
ህወሃት የተገፈፈውን የህግ ልዕና ለማስመለስ ወዴትም ሄዶ አቤት ማለት እንደማይችልም ባለሙያው አስታውሰዋል። ይህንን እውነት ። እነሱ ጠንቅቀው እንደሚያውቁት ጠቁመዋል
 
 
የፕሬስ መግለጫ
ቀን፡- 30/12/2012
አዲስ አበባ
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ነሐሴ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ባካሄደው 5ኛ ዙር የፓርላማ ዘመን 5ኛ አመት 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን ወደ ጎን በመተው የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ያወጣው የምርጫ አዋጅ ቁጥር 351/2012 እና አዋጁን መሰረት አድርጎ ያቋቋመው የምርጫ ኮሚሽን፣ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች እና የፈፃማቸው ተግባራት የሕገ መንግስት ትርጉም ውሳኔ እንዲሰጥበት በሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ተጣርቶ ለመጨረሻ ውሳኔ ለምክር ቤቱ በሕገ መንግስት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች በኩል በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ ውይይት አድርጓል፡፡
በውይይቱም ላይ በእስከ አሁኑ ሂደት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለትግራይ ሕዝብ ትልቅ ክብር ያለው መሆኑንና ህገወጥ አካላት በሚፈፅሙት ድርጊት ምክንያት በሕዝቡ ላይ ጉዳት ሊደርስበት አይገባም ብሎ የሚያምን መሆኑ እና በቀጣይም ችግሮችን በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ለመፍታት እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
በሌላ በኩል የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የራያ ራዩማ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ እና የወልቃይት ጠገዴ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ለምክር ቤቱ ያቀረቧቸውን ቅሬታዎች በመጥቀስ የትግራይ ክልል እያካሄደ ካለው ህገወጥ ምርጫ ጋር ተያይዞ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና በሕገ መንግስቱ የተረጋገጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች መብት አለማክበር ተቀባይነት የሌለውና ሊታረም የሚገባው መሆኑ ከማስቀመጡም ባሻገር የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ.ም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛውን አገራዊ ምርጫ በተመለከተ ያስተላለፈውን ውሳኔ እና የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ በደብዳቤ ሕገ መንግስቱና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ እንዲከበር የሰጡትን ማሳሰቢያ አለመቀበሉ ኢ-ሕገ መንግስታዊ ነው ብሏል ምክር ቤቱ፡፡
በተጨማሪም ምክር ቤቱ የሚከተሉትን የሕገ መንግስት ትርጉም ውሳኔዎች በሙሉ አፅድቋል፡፡
1) የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ያወጣው የምርጫ አዋጅ ቁጥር 351/2012 ከሕገ መንግስቱ አንቀጽ 55(15) እና አንቀጽ 55(2)(መ) ጋር ይቃረናል፤
2) የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የምርጫ አዋጅ ቁጥር 351/2012ን መሰረት አድርጎ የምርጫ ኮሚሽን ማቋቋሙ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 102 ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠውን ስልጣን ይጥሳል፤
3) የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት፣ አስፈፃሚ አካላት እና የምርጫ ኮሚሽን ምርጫን በሚመለከት ያወጣው የምርጫ አዋጅ ቁጥር 351/2012 ያሳለፏቸው ውሳኔዎች እና የፈፀሟቸው ተግባራት ከሕገ መንግስቱ ጋር የሚቃረኑ በመሆናቸው በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 9(1) መሰረት እንዳልተደረጉ የሚቆጠሩ፣ የማይፀኑ እና ተፈፃሚነት የሌላቸው ናቸው በማለት የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሙሉ ድምጽ የመጨረሻ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ደመቀ መኮንን በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሚመራ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *