ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ እና ያስከተለው ከፍተኛ ብሥጭት /Disappointment/ እንዲሁም ከፍተኛ ፈንጠዝያ /Euphoria/

በዚህ እሳቤ ምርጫ አካሂደው የክልሉን ሹሞች ለማዕከላዊ መንግስት ማቅረብ አይችሉም። በትህነግ ለተመረጡት የፌዴራል መንግስት እውቅና አይሰጥም። በጀት አይመድብም። ምንም ዓይነት ግንኙነት አይመሰርትም። ምክር ቤቱ “ምርጫው እንዳልተደረገ ይቆጠራል” ሲል ምንም ውጤት የሌለው Of no effect ነው ማለቱ ነው። ከዚህ ሁሉ በላይ ” ኢህገመንግስታዊ” ሲልም መድቧቸዋል። በዚህ መሰረት አንድ ህጋዊ መንግስት ራሱን ወዶና ፈቅዶ ወደ ህገወጥነት ካሳደገ ቡድን ጋር ፈር ያለው ግንኙነት ማድረግ የሚታሰብ አይሆንም። ውሳኔው የላላ የመሰላቸው ይህን ሃሳብ ሊያሰሉት የሚገባ ይሆናል።

 

ነጻ አስተያየት – በስብሃት በአምላክ 

እንደገባኝና ይፋ እንደሆነው መረጃ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የተለሳለሰ /diluted/ እና ብዙ ያልጮኽ /Muted/ የምትመስል፣ ነገር ግን ትህነግ  ምርጫው ከካሄደ  በኋላ የትግራይ ክልል ከእስር ክልሎች እንደ አንዱ ክልል እንዳይቀጥል የሚያደርግ ውሳኔ ስለመተላለፉ ብዥታ የለውም።
እውነታው ይህን ቢመስልም ትህነግ የውሳኔውን ጥልቀት፣ ወርዱን ፣ ስፋቱን አልተረዳችውም። ግልብ በሆነ በተለመደ አረዳዷ ” ከስብሰባው ሁለት ቀን በፊት በሰጠሁት ማስፈራሪያ ፈርተው የበጀት ማነቆና የማዕከላዊ መንግስት ጣልቃ ገብነት የሚፈቅድ ውሳኔ አልወሰኑም” ብላ እየፈነጠዘች ነው። የትህነግ የፌስቡክ ሰራዊቷም ይህን እያስተጋቡ ነው።
ትህነግ ጥሩ ግንዛቤ ቢኖራት፣ አርቆ አሳቢ ብትሆን ኖሮ ምርጫ ማካሄዱን በተወች ነበር። “ካፈርኩ አይመልሰኝ” እንዲሉ አይኗን ጨፍና ምርጫ ማካሄዷ አይቀሬ ይመስላል። ትህነግ እንደ ጓያ ነቃይ የፊት ፊቷን እንጂ አንድ እርምጃ ወደፊት ሄዳ የማሰብ፣ የማስተዋል፣ የማገናዘብ ባህሉም ሆነ እውቀቱ  ስለሌላት “ይገድስ አይገድስ” ብላ ምርጫውን እንደምታካሂድ በኔ በኩል በአሁን ደረጃ እርግጠኛ ነኝ።
ውሳኔውን ተከትሎ ሁለት ዓይነት ስሜቶች አስተውታለሁ። ትህነግ የሰጠችው ማስጠንቀቂያ የፈጠረው ጫና ነው የሚሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ደጋፊዎች መበሳጨት ወይም /Disappointment/ ሲታይባቸው ፣ በዚህ ትይዩ ደግሞ ” የፌዴሬሽን ምቤት በጀት ይቆርጣል፣ ይከለክላል ወይም ማዕከላዊው መንግስት ጣልቃ እንዲገባ ሲል ይወስናል ብላ ፈርታ ዋ ፣ ዋ ፣ዋ ዋ፣ ይሄ ይደረግና ወዮላችሁ፣ በአርጩሜ እገርፋችኋለሁ”  ብላ የዛቻ መግለጫ ከስብሰባ ሁለት ቀን በፊት ያወጣችው ትህነግ እና ደጋፊዎቿ ደግሞ እጅግ በጣም ከፍተኛ ፈንጠዝያ Euphoria ሰክረዋል።
ሁለቱ ተቃራኒ ወገኖች ማለትም የመንግስት ደጋፊዎች በአንድ በኩል እንዲሁም Tigrai People Literation Front የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግንባር ደጋፊዎች በሌላ በኩል ብስጭታቸውንና ደስታቸውን በመግለፅ ሶሻል ሚድያን፣ በተለይ ፌስቡክን አጣበውታል። ሁለቱም ወገኖች በጥሬና ብስል አስተያየት እንደ ብሽሽቅም ሲቃጣቸው አይተናል። ግናም እናያለን።

የእኔ እይታ 

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በጀት ላይ፣ የፌዴራል መንግስት ጣልቃ መግባት ላይ በአሁን ደረጃ ኣልወሰነም ማለት ነገ ከነገ ወዲያ አይወስንም ማለት አይደለም። ዛሬ አልወሰንክምና ሁለተኛ ይሄን ጉዳይ አጀንዳ አድርገህ ልትወያይበት አትችልም ብሎ የሚከለክል ሕግም የለም። በጀት መቁረጥ ፣ ጭራሹን መከልከል፣ የግንኙነት መረብ ወይም ቻነል መዝጋት ወዘተ ሁሌም ጠረጴዛ ላይ ናቸው። ይሄ አሁን ለምን አልተወሰነም የሚሉት ይህ ጉዳይ ድጋሚ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት መቅረብ የማይችል መስሏቸው ከሆነ ስህተት ነው።
የፌዴራል መንግስት ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ጨምሮ በማናቸውም መንገድ ጣልቃ መግባት በሕገ መንግስት የተደነገገ ስለሆነ ትህነግ አደብ ካልገዛች የመጨረሻ አማራጭ /Last resort/ እንደሚሆን ሳይታለም የተፈታ ነው። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጣልቃ እንዲገባ ወይም በጀት ላይ ቢወስንም ትህነግ ምርጫውን ማካሄድ እንደማታቆም ምክር ቤቱ ውሳኔውን ሲወስን ግምት ውስጥ አስገብቶታል።
ትህነግ ምርጫ በማካሄዷ ሳቢያ የሚገጥማትን ችግር፣ የክልሉም ህዝብ ይህንኑ ተከትሎ የሚገጋፈጠውን ጣጣ አገናዝበው እንዲወስኑ የሚረዳ እንደ ማሳሰቢያ ብቻ የሚያገለግል ውሳኔ ነው የተሰጠው። በትግራይ ክልል ምርጫን ለማክሄድ ትህነግ ያቋቋመችውን የክልል ምርጫ ቦርድ ነገረ ስራ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሙሉ በሙሉ ” ኢህገመንግስታዊ ስለሆነ እንዳልተደረገ ይቆጠራል” ብሏል።
በዚህ እሳቤ ምርጫ አካሂደው የክልሉን ሹሞች ለማዕከላዊ መንግስት ማቅረብ አይችሉም። በትህነግ ለተመረጡት የፌዴራል መንግስት እውቅና አይሰጥም። በጀት አይመድብም። ምንም ዓይነት ግንኙነት አይመሰርትም። ምክር ቤቱ “ምርጫው እንዳልተደረገ ይቆጠራል” ሲል ምንም ውጤት የሌለው Of no effect ነው ማለቱ ነው። ከዚህ ሁሉ በላይ ” ኢህገመንግስታዊ” ሲልም መድቧቸዋል። በዚህ መሰረት አንድ ህጋዊ መንግስት ራሱን ወዶና ፈቅዶ ወደ ህገወጥነት ካሳደገ ቡድን ጋር ፈር ያለው ግንኙነት ማድረግ የሚታሰብ አይሆንም። ውሳኔው የላላ የመሰላቸው ይህን ሃሳብ ሊያሰሉት የሚገባ ይሆናል።
ትህነግ “ይገድስ አይገድስ” ብላ ምርጫ ማካሄዷን እንጂ በዚህ ሕገወጥ ምርጫ የሚመሰረት የትግራይ ክልል ፓርላማ የመገንጠል ጥያቄ እንኳን ማቅረብ አይችልም። አሁን ያለው የትግራይ ክልል ፓርላማ ህጋዊ ነው፣ ከምርጫው ዘመን በኋላ ደግሞ የፌዴራሉ ፓርላማ የቆይታ ዘምኑን በፌዴራል አዋጅ አራዝሞለታል። ትህነግ ሕጋዊውን የትግራይ ክልል አስተዳደርና ፓርላማ በአንድ ጀንበር ሕገወጥ ምርጫ እካሂዳ ሕገወጥ ታደርገዋለች ማለት ነው። ወይም በራሳዋ ፈቃድ ከህጋዊነት ወደ
ምርጫ ተካሂዶ የሚመሰረት ፓርላማ፣ የክልሉ መስተዳድር ምንም ዓይነት ሕጋዊ መሰረት የሌለው ሕገወጥ ስለሚሆኑ የበጀት ክልከላው እና የፌዴራል መንግስት ጣልቃ ገብነት ምንም ሌላ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ይሆናል። ይህ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ የመንግስትን ደጋፊዎች ሊያስከፋ አይገባም። ይህ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ትግራይ ክፍለ ሀገርን ከምርጫው በኋላ የተገለለች ክፍለ ሀገር Renegade province ያደርጋታል። ስለሆነም የትህነግን ደጋፊዎች ፈንጠዝያ በቦይ ውሃ ውስጥ እንደሚጮኸዋ እንሰሳ ማለት ነው።
ትህነግ ሐቁን ማየት ተስኗት ከገፋችበት በትህነግ ባዶ እብሪት፣ በትህነግ ብራቫዶ፣ በትህነግ የማሰብ ችግር ህዝቡ ዋጋ ይከፍላል ። አሁንም አልረፈደም። የትግራይ ምሁራን እና ጨዋ ዜጎች ለትግራይ ህዝብ ጥቅም ሲሉ ይሄን ምርጫ ማስቆም ይኖርባቸዋል። ምርጫውን ካላስቆሙትና ምርጫው ተካሂዶ ከፌዴራል መንግስት ጋር ጦርነት ከተከፈተ መላው ህዝብ እንዲህ ይላል:— “ቀደሞ ነበር እንጂ ደህና አርጎ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ” ቸር ይግጠመን