” ተቀባይነት የለውም” በሚል ሙሉ ዶክመንቱን በመሰረዛቸው ባስንሳው አለመግባባት ሳቢያ አጋጣሚ ጠብቆ ወጣቶችን ለማሰር የተሰራ ድራማ እንደሆነ የጸጥታ ሃላፊው ለዛጎል አስረድተዋል። በወቅቱ መሳሪያም ሆነ ማንኛውም ዓይነት ቁሳቁስ የያዙም ሆነ በሃይል ማናቸውንም ድርጊት ለመፈጸም የሞከሩ እንዳልነበር አረጋግጠዋል። “

“እኔ የምናገረው እውነት ነው። ይህንን በመናገሬ ሊደርስብኝ የሚችል ችግር ካለም እችለዋለሁ። ዋሽ እያሉኝ ነው። በፍጹም አልዋሽም። እምነቴም አይፈቅድልኝም። አላደርገውም። ዜናውን በስሜ ልትጽፍይት ትችላላቹህ።እሞታለሁ እንጂ አልዋሽም። የሚያሳዝነው አንድ የክልል መሪ ሲዋሽ ማየት ነው። የሚበጀው ቦታው ድረስ በመምጣት ህዝቡን ይቀርታ መጠየቅ ብቻ ነው።”

አቶ ኦሞት ኡጁሉ ኦቡፕ አዲሱ የጋምቤላ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሆነው  በህዳር 2011 ነበር የተሾሙት። ከሹመታቸው በፊት የክልሉ የጸረ ሙስናና ስነ ምግባር ኮሚሽነር ነበሩ። ሹመታቸውን ተከትሎ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጋትሉዋክ ቱት ላይ እሳቸው በሚመሩት ኮሚሽን አማካይነት የተሰበሰበውን መረጃ ተንተርሰው ህጋዊ እርምጃ ያስወሰዳሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር።

ጋትሉዋክና ተባባሪዎቻቸው በሙሉ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው” በሚል ርዕስ የክልሉን ነዋሪዎች ጠቅሶ ጎልጉል የድረ ገጽ ጋዜጣ  እሳቸውና ምክትላቸው ሰናይ አክዎር ሃላፊነታቸው በፈቃዳቸው ሲለቁ  በምትካቸው የክልሉ የሥነምግባርና ጸረ-ሙስና ኃላፊ ኦሞት ዑጁሉ ሊቀመንበር፤ የጋትሉዋክ ሚስት ወንድም የሆኑትና የክልሉ የንግድ ቢሮ ኃላፊ ታንኩዌይ ጆክ ሮምን ምክትል ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው ይፋ እንደሆነ የክልሉ ነዋሪዎች ምርጫውን ” ፌዝ” በማለት ነበር ቀድሞ ሰፊ ዘገባ ያስነበበው። አስፈንጣሪ ሊንኩን እዚህ ላይ በመጫን ሙሉ ዘገባውን ያንብቡ።

በዘገባው በግምገማ ከቀረበባቸው ክስ አፈና፣ ግድያ፣ ከህወሃት ጋር ያላቸው የጎንዮሽ ግንኙነት ወዘተ በተጨማቲ  ከሙስና ጋር በተያያዘ የአዳራሽ ግንባታ፣ የመንገድ ሥራ፣ የ150 ተገጣጣሚ ቤቶች ግንባታ፣ የሦስት ዘመናዊ ሞተር ጀልባ ግዢ፣ የእንግዳ ማረፊያ ቤቶች ግንባታ፣ የትራፊክ መብራት ዝርጋታ፣ ወዘተ ለሚቴክ፣ ከህወሃት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ላላቸው ግለሰቦች፣ ከአመራሩ ጋር በጥቅም ለተሳሰሩ ባለሃብቶች፣ ወዘተ ያለ አንዳች ጨረታ ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ቢደረግም አብዛኛዎቹ ፕሮጀክቶች የግንባታ ፈቃድ የላቸውም፣ እስካሁንም ተሠርተው አልተጠናቀቁም  አንዳንዶቹም ያለዲዛይን እንዲሠሩ የተደረጉ መሆናቸው ከጋምቤላ የተገኘው የሰነድ መረጃ ያመለክታል።

በ2008ዓም ኢህአዴግ “የብሔር ብሔረሰቦች ቀን” በማለት በጋምቤላ ከበሮ በደለቀበት ወቅት የጋትሉዋክ አመራር መጠነሰፊ ምዝበራ ማካሄዱን ይኸው ለዶ/ር ዐቢይ የተላከው ሰነድ ያብራራል። ኃይለማርም ደሳለኝ በተገኘበት የተከናወነው ሥነሥርዓት ላይ በክልሉ ካቢኔ “ለእንግዶች የምግብ አገልግሎት” በሚል የተመደበው 12 ሚሊዮን ብር ሆኖ ሳለ ወ/ሮ ትልቅሰው ገዳሙ ለተባሉት የሆቴል ባለቤትና ከህወሓት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ላላቸው ሴት ለተመሳሳይ ወጪ 16,659,200 (አስራ ስድስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሃምሳ ዘጠኝ ሁለት መቶ) ብር የተከፈላቸው ሲሆን ከዚህም አብዛኛው ከዚህ በፊት እንደሚደረገው በካሽ በግል እንዲሰጣቸውና ግለሰቧ ከትርፍ እና ከመሳሰለው ግብር ነጻ እንዲሆኑ ተደርጓል ይላል ሰነዱ።

Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

ከዚሁ ሙስና ጋር በተያያዘ ለዋግ ኽምራ ልማት ማኅበር ዕርዳታ በሚል በጋትሉዋክ ፊርማ “በ2006 እና በ2009ዓም በድምሩ 10ሚሊዮን ብር እንዲሰጥ” የታዘዘ ሲሆን ገንዘቡ ግን ለማኅበሩ “በባንክ ሒሳብ በቀጥታ ከማስገባት (ይልቅ) በግለሰብ ስም ወጪ” መደረጉ ገንዘቡ ለታሰበለት ማኅበር ለመዋሉ ትልቅ ጥርጣሬ እንደሚጭር ሰነዱ ይጠቁማል።

በተገመገሙበት ወቅት 142 ጥያቄ ሲቀርብላቸው መቋቋም አቅቷቸው ዝለው በመውደቅ ወደ ሆስፒታል የተወሰዱት ጋት ካገገሙ በሁዋላ ” ሁሉም ነገር እኔን ስለሚመለከት ራሴን ለማየት ያለ አንዳች አስገዳጅነት በራሴ ፈቃድ ስልጣኔንን ለቅቄያለሁ” ነበር ያሉት። ጋት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ላይ የግድያ ሙከራ ሲደረግ ያልተቃወሙ ብቸኛው የክልል መሪም ናቸው።  እንግዲህ ይህ ሁሉ የግምገማ መረጃ እጃቸው ላይ የነበረው አዲሱ ፕሬዚዳንት ወደ ስልጣን ሲመጡ ጋትን ህግ ፊት ያቀርባሉ የሚል ተስፋ ነበር።

አንዳንዶች እንደሚሉት አሁን ስልጣን ላይ ያሉት የቀድሞ የጸረ ሙስና ኮሚሽነር ወደዚህ ሃላፊነት የመጡት በጋት ስልታዊ ተግባር በቀጣይ እንዳይነኩ ታስቦ ነው። ለዚሁ ይመስላል ኦሞት ወነበራቸውን ከያዙ በሁዋላ ዝምታን መርጠዋል። ይባስ ብለውም አምባ ገነን ሆነዋል። ምክትላቸውም ቢሆኑ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ጋትሉዋክ እህት ባል መሆናቸው ለጉዳዮች መድበስበስ አንድ ተጨማሪ ማሳያ መሆኑንን ነዋሪዎች ይገልጻሉ።

ኦሞት ኡጁሉ ወደ ሃላፊነት ሲመጡ ብዙ ቢጠበቅም እሳቸው ግን በተጠበቀው መጠን ሊሰሩ ቀርቶ ይባስ ፍትህ እየረገጡና ክልሉን ለማልማት የሚያስችል ብቁ አመራር መስጠት ባለመቻላቸው የሚሰማባቸው ቅሬታ ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ ነው። አንዳንድ በማህበራዊ ገጾች ትችት የሚጸፉና በህዝባዊ ውይይቶች ላይ የሚቃወሙዋቸውን ማሰርና ማስፈራራት መለያቸው መሆኑንን የድርጊቱ ሰለባ የሆኑ እየመሰከሩ ነው።

ከአንድ የክልል ከፍተኛ አመራር በማይጠበቅ መልኩ ፌክ አካውንት በፌስ ቡክ ከፍተው ራሳቸውን ማሞገስና ማስተዋወቅ ላይ ትኩረት የሰጡ መሪ መሆናቸውን በማስረጃ ለዛጎል ያደረሱ እንዳሉት ” ፕሬዚዳንቱ ከሽፈዋ ብልጽግናም እሳቸውን ይዞ ሊቀጥል እንደማይችል ሊረዳ ይገባል” ብለዋል። እንደ ቀድሞው ፕሬዚዳንት በከፍተኛ ደረጃ በክልሉ ትሥሥር ካላቸው የህወሃት አንጃዎች ጋር ግንኙነት ሊኖራቸው እንደሚችልም ይጠረጥራሉ።

በጋምቤላ ሰሞኑንን መነጋገሪያ የሆነውና የፕሬዚዳንቱን ስብዕና ጥያቄ ውስጥ የከተተው በአደባባይ መዋሸታቸውና ማስዋሸታቸው ነው። በመንግስት ሚዲያዎችና በጀርመን ድምጽ ” ከግድያ ተረፍኩ” ያሉት ኦሞት ይህንኑ ዜና ያስተጋቡት በክልሉ የጸጥታ ሃላፊ በኩል ነው።

“በጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድሩን ለመግደል የሞከሩ ተጠርጣሪዎች ተያዙ” በሚል ርዕስ የጀርመን ድምጽ አስቀድሞ ይፋ ባደረገው ዜና ነሐሴ 22 ቀን 2012 ዓ.ም. በስብሰባ ላይ እያሉ ግድያው እንደተሞከረባቸው  የክልሉ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ቱት ኮር ለጀርመን ድምጽ የተናገሩት። በዚህም  ከጆር ወረዳ በአጠቃላይ 26 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

Related stories   ደመቀ መኮንን በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሚመራ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

ይሁን እንጂ የወረዳው የጸትታ ሃላፊ በስልክ ለዛጎል እንደተናገሩት”ይህ ዘገባ ሙሉ በሙሉ ሃሰት ነው። የግድያ ሙከራ ማንም በማንም ላይ አላደረገም። ድራማ ነው” የወረዳው የጸጥታ ሃላፊ እንዳስረዱት የተጋጩት ሁለት ግለሰቦች ነበር። እርግጥ ፕሬዚዳንቱ በተባለው ቀን በተጠቀሰው ስፋራ ተገኝተዋል። ከስምንት ቀበሌዎች ተወካዮች ጋር ለመወያት እቅድ ቢያዝም እሳቸው ከኈት ቀበሌ ተወካዮች ጋር ብቻ እንደሚወያዩ በማሳወቃቸው ከስብሰባው አዳራሽ ውጪ በርቀት ሰዎች ነበሩ። ወጣቶችም!!

በውይይቱ ላይ የጃን ወረዳ አስተዳዳሪ በአካባቢው የተከሰተውን የጎርፍ አደጋ አስመልክቶ ወረዳው አስፈላጊውን ሁሉ እያደረገ መሆኑ፣ ክልሉም በቂ ድጋፍ እንደሚሰጥ አድንቆ ሲናገሩ የተበሳጩ የውይይቱ ተሳታፊ ተነስተው ” ይህ ውሸት ነው። ህዝብ በጎርፍ ተጠቅቶ በረሃብ እየተጎዳ ነው። መንገድ የለም። … ” ብለው ሲናገሩ የአስተዳዳሪው ዘመድ የሆነ ሌላ የውይይቱ ተሳታፊ ተነስተው አስተያየት ሰጪውን ተሳደቡ። ፕሬዚዳንቱ በሚመሩት ስብሰባ ንትርክ ቀጠለ። ይህን ጊዜ ለዛጎል ምስክርነታቸውን የሰጡት የጸጥታ ሃላፊ ሁለቱንም ከስብሰባው አዳራሽ አስወጥተው ከፌደራል የጥበቃ ሰዎች ጋር በመሆን ገሰጹዋቸው።

በዚህን ወቅት ስብሰባውን እንዳይገቡ የተከለከሉ ” ቦታ አላ ለምን አታስገቡንም” በሚል እየተየቁ ሳለ የወረዳው አስተዳዳሪ ዘመድ ከአዳራሹ አብረዋቸው እንዲወጡ የተደረጉትን አስተያየት ሰጪ በድንገት በጥፊ መቱዋቸው። በዚሁ መነሻ ሁለቱም ታሰሩ። ቀደም ሲል የኒኬኒ ቀበሌ የወረዳነት ጥያቄ በሰነድ ከምክንያት ጋር ተያይዞ ቀርቦ ስለነበር በዚህ ደስ ያለተሰኙት የጆር ወረዳ አስተዳዳሪ የሁለቱን ሰዎች ጸብ ተከትሎ ከስብሰባው አዳራሽ ውጪ ያሉ ወጣቶችን በጣታቸው አያመለከቱ እንዲያዙ መመሪያ ሰጡ። አስራ ዘተን ሰዎች ታሰሩና ወደ ጋምቤላ ተወሰዱ።

በወረዋ ውስጥ ካሉት ቀበሌዎች መካከል ኒኬኒ ያቀረበቸውን የወረዳነት ጥያቄ ፐሪዚዳንቱ ” ተቀባይነት የለውም” በሚል ሙሉ ዶክመንቱን በመሰረዛቸው ባስንሳው አለመግባባት ሳቢያ አጋጣሚ ጠብቆ ወጣቶችን ለማሰር የተሰራ ድራማ እንደሆነ የጸጥታ ሃላፊው ለዛጎል አስረድተዋል። በወቅቱ መሳሪያም ሆነ ማንኛውም ዓይነት ቁሳቁስ የያዙም ሆነ በሃይል ማናቸውንም ድርጊት ለመፈጸም የሞከሩ እንዳልነበር አረጋግጠዋል።  እኔ የምናገረው እውነት ነው። ይህንን በመናገሬ ሊደርስብኝ የሚችል ችግር ካለም እችለዋለሁ። ዋሽ እያሉኝ ነው። በፍጹም አልዋሽም። እምነቴም አይፈቅድልኝም። አላደርገውም። ዜናውን በስሜ ልትጽፍይት ትችላላቹህ።እሞታለሁ እንጂ አልዋሽም። የሚያሳዝነው አንድ የክልል መሪ ሲዋሽ ማየት ነው። የሚበጀው ቦታው ድረስ በመምጣት ህዝቡን ይቀርታ መጠየቅ ብቻ ነው።”

የጸጥታ ሃላፊው እንደሚሉት የመንግስት ሚዲያዎችም ሆኑ የግል ሚድያዎች ጉዳዩን አጣርተው ሊያቀርቡ እንደሚገባ ነው። የጸጥታ ሃላፊው እንደማይፈሩና ለሚወሰድባቸው ማናቸውም እርምጃ ዝግጁ እንደሆኑ ይፋ በማድርግ መረጃ ከሰጡ በሁዋላ ለዛጎል ተጨማሪ መረጃ ደርሷል።

Related stories   የትህነግ "ውሮ ወሸባዬ" - የመንግስት ሩጫ - የሃላኑ የኢትዮጵያን ቋንጃ የመበጠስ የእባብ አካሄድና ባንዳዎች!

የክልሉ ፐሬዚዳንት ለአኝዋክ ዞን መመሪያ መስጥታቸው ተሰምቷል። መመሪያው የተላለፈው ፕሬዚዳንቱ መዋሸታቸውን የገለጹ፣ የወረዳነት ጥያቄ የሚደግፉትንና እሳቸው ላይ ግልጽ ማጣራት እንዲደረግ በጠየቁ ላይ ርምጃ እንዲወሰድ ነው። ውሳኔውን ተከትሎ ” ይህ የህወሃት መንግስት አይደለም። አንፈራም” በሚል እርምጃ እንዲወሰድባቸው የተፈረደባቸው ምላሽ ሰጥተዋል።

ከክልሉ ስማቸውን እንዲጠቀስ ያልፈለጉ እንዳሉት የብልጽግና ፓርቲ በፕሬዚዳንቱ ላይ ምርመራ ለማካሄድ ዝግጅት ላይ መሆኑ ታውቋል። ቀደ ሲል ኦሞት ገና ወደ ስልታን እንደመጡ የፋይናንስና የውሃ ቢሮ ሃላፊዎችን ለምን ተፈታተኑኝ በሚል ከሃላፊነታቸው ማንሳታቸውን የገለጹት መረጃ ሰጪ፣ በጋምቤላ በርካታ የአስተዳደር፣ የሙስና፣ የመሰረት ልማት ግንባታና ጥራት እንዲሁም የሰዎችን ነጻ ሃሳብ የመስጠት መብት የማፈን ድርጊት መባባሱ ፕሬዚዳንቱ ከሚገመገሙበት ጉዳዮች መካከል ቀዳሚዎቹ ናቸው።

በጋንቤላ አብዛኛው መንገዶች ገንዘብ የተበላባቸው ፕሮጀክቶች በመሆናቸው በክረምት አይሰሩም። የተሻለ የሚባሉት መንገዶች ዝናብ ሲዘንብ ጎርፍ ይዘጋቸዋል። የውሃ መጥለቅለቅ ችግር ላይ የጣላቸው ወገኖችን በመኪና መርዳት ስለማይቻል ጀልባ መጠቀም ግድ ነው። በዚሁ የመንገድ ችግር ሳቢያ ህዝብ በረሃብ እየተሰቃየ መሆኑን ካካባቢው ያገኘነው ዜና ያመለክታል።

 

 

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *