“Our true nationality is mankind.”H.G.

ብልጽግና ሁለት ቦታ የሚረግጡ “ወላዋዮችን” ማስወገድንና ህግ ማስከበር ላይ እንደማያፈገፍግ አስታወቀ

የአባላት ግምገማ ፕሮግራሞችን የማካሄድ ሥራ ተሠርቶ ስለነበረ አንዳንድ ቦታዎች ሁለት ቦታ የሚቆሙ ሰዎች ተገኝተዋል። እነዚህ በጣም ወላዋይ የሆነ አቋም ያላቸው አመራርና አባላት ከአባልነትም ከአመራርነትም እንዲወገዱ ተደርጎ የብልጽግና ፓርቲ ወደፊት እንዲቀጥል ተደርጓል።

ዶክተር ቢቂላ በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የዓለም አቀፍና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ቢቂላ

በአቋም ያልጠሩና ከአዲሱ የብጽግና ፓርቲ አስተሳሰብ ጋር መራመድ የሚቸገሩ አባላትን ከአመራርነት የማውጣት ሥራ ሲሠራ የቆየው ፓርቲው በቀጣይም በደረሰበት የትግል ምዕራፍ ሊመጥን የሚችል አባላትን የማጥራት ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የዓለም አቀፍና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ አስታወቁ። የብልጽግና ፓርቲ በመደመር ስለሚያምን መቀነስን እንደ መጨረሻ ዓይነት መፍትሔ አድርጎ እንደማይወሰድ አመለከቱ።

ዶክተር ቢቂላ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ፓርቲው ለአባላቱ የተለያዩ ስልጠናዎችን ሲሰጥ ቆይቷል። አንዳንድ ቦታዎች ላይ ግን ሁለት ቦታ የመቆም፣ በአስተሳሰብ ያለመጥራትና ወጥ የሆነ አቋም ይዞ ከፓርቲው ጋር ለመሰለፍ አለመቻል የታየባቸው አካባቢዎች በመኖራቸው እነሱን የማጥራትና ከአመራርነት ገለል የማድረግ ሥራዎች ሲከናወኑ ቆይቷል፤ በቀጣይም ፓርቲው የደረሰበትን የትግል ምዕራፍ ሊመጥን የሚችል አባላትን የማጥራት ሥራ ይቀጥላል።

እርሳቸው እንደገለጹት፤ አባላቱን የማጥራት ሥራ በአብዛኛው ክልል ላይ የተከናወነ ነው። በኦሮሚያም የተካሄደው ተመሳሳይ ነው። ይሁንና ይህ መቶ በመቶ ተሠርቶ ተጠናቋል ባይባልም ወደፊትም የሚቀጥል ነው። በኦሮሚያ ክልል የክልል መስሪያ ቤት ጀምሮ እስከታች አባላት ድረስ የማስልጠን፣ ኮንፈረንሶችን የማካሄድ የአባላት ግምገማ ፕሮግራሞችን የማካሄድ ሥራ ተሠርቶ ስለነበረ አንዳንድ ቦታዎች ሁለት ቦታ የሚቆሙ ሰዎች ተገኝተዋል። እነዚህ በጣም ወላዋይ የሆነ አቋም ያላቸው አመራርና አባላት ከአባልነትም ከአመራርነትም እንዲወገዱ ተደርጎ የብልጽግና ፓርቲ ወደፊት እንዲቀጥል ተደርጓል።

Related stories   ኤፒ ለቅጥፈቱ ይቅርታ አልጠየቀም – ምርጫ ተራዘመ፤ለምን?

ይህ ከሞላ ጎደል በሁሉም ከልሎች እየተከናወነ ነው ያሉት ዶክተር ቢቂላ፣ ምንም እንኳ በሁሉም ክልሎች ወጥና ተመሳሳይ ባይሆንም በጣም ቀደም ብለው የማጥራት ሥራ የሠሩ ክልሎች እንዳሉ ሁሉ ገና እየሠሩ ያሉ ክልሎች መኖራቸውን አመልክተዋል። ነገር ግን በሁሉም ክልሎች አቅጣጫው ተመሳሳይ ስለሆነ ሁሉም ክልሎች አባሎቻቸውንና አመራሮቻቸውን የማጥራት፤ በጣም ጠንካራ የሆኑትን አባላት ወደፊት ይዞ የመሄድ፤ ስልጠናውንና የአባላትን የአቋም ሁኔታ የማጠናከርና ብዥታዎችን የማጥራት ሥራዎችን በማከናወን የሚኬድ እንደሆነም ጠቅሰዋል። በዚህም ትልቅ ውጤት ተገኝቷል ብለዋል።

በቅርብ ጊዜ በተሠሩ ሥራዎች በጣም በርካታ ብዥታ ያለባቸው አመራሮች በመጥራታቸው ጠንካራ የሆኑና ግልጽ አቋም ያላቸውን አመራሮች ወደፊት ይዞ የመሄድ ሥራ እየተሠራ መሆኑን ጠቅሰዋል። መልካም ውጤትም በዚህ ረገድ ተገኝቷል ያሉት ኃላፊው፣ ፓርቲው ነገሮችን ከስር መሰረቱ እያስተካከለና እየተማረ የሚሄድ ነው ብለዋል።

ዶክተር ቢቂላ እንዳብራሩት፤ የፓርቲው ትልቁ ትኩረት ማሳወቅ፣ ማሰልጠንና አባላት ሐሳባቸውን እያስተካከሉ እንዲሄዱ ማድረግ ነው። ነገር ግን ከስንዴ መሃል እንክርዳድ አይጠፋም እንደሚባለው በሚሊዮን የሚቆጠር አባል ባለበት በጣት የሚቆጠሩ ደግሞ ሐሳባቸው በግልጽ የማይታወቅና እዚህና አዚያ የሚቆሙ ብሎም ለመረዳትም የሚቸገሩ አካላት አይታጡም። ስለዚህ እንዲህ ዓይነት ነገር በሚያጋጥምበት ጊዜ ቆም ብሎ ለማስተካከል መሞከር፤ ማስተካከል በማይቻልበት ጊዜ ከአመራርና ከአባልነት ገለል አድርጎ የብልጽግና ጉዞውን በፍጥነት ወደፊት ማስቀጠል ያስፈልጋል። ይህ ደግሞ የዓለም አቀፍ ተሞክሮ ነው።

Related stories   ማዕድን ቀጣዩ የኢትዮጵያ ጉሮሮ - "የሕዝብ ሃብት ለሚያባክኑ ዝምታ የለም" ታከለ ኡማ

ተከታታይነት ያለው ሥራ ሲሠራ ነበር ያሉት ዶክተር ቢቂላ፣ እኛ የብልጽግና ሰዎች በመደመር ስለምናን መቀነስን እንደ መጨረሻ ዓይነት መፍትሔ አድርገን አንወስድም ሲሉ ተናግረዋል። ለዚህም በምክንያትነት የተናገሩት ፍልስፍናችን መደመር ነው ሲሉ ነው። ማንኛውም ሰው ከብልጽግና አስተሳሰቦች ጋር መራመድ የሚችል ከሆነ ተደምሮ መንቀሳቀስ እንደሚችል አመልክተዋል።

ኢትዮጵያን ለማልማት፣ ለማሳደግና የሕዝባችንን ችግሮች ለመፍታት ቁርጠኝነት ያለውና ያመነበት ማንኛውም አባል ከእኛ ጋር ተሰልፎ መሄድ ይችላል የሚል ፍልስፍና ስለምንከተል ቅድሚያ ሰጥተን ስንሠራ የነበረው የማሰልጠን አባላትን፣ የማብቃት፣ ብዥታ ያለባቸውን አካባቢዎች እንዲጠሩ የማድረግ ላይ ነበር ብለዋል። አባላት በፕሮግራሞች ላይ የጠራ ግንዛቤ እንዲኖራቸው የማድረግ ሥራ መሠራቱንና በዚህም ትልቅ ውጤት መገኘቱን ጠቅሰዋል። ወደፊትም በዚሁ አቅጣጫ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

ሁሉም ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች የተሰጠውን ስልጠና ወስደው በየዕለቱ በሚከናወነው የአባላት ግንባታዎች ውስጥም አልፈው ጠንካራ አቋም ይዘው ማንኛውም ፈተና ቢያጋጥማቸው ሊወጡ በሚችል ቁመና ላይ ይገኛሉ ብሎ መናገር እንደሚቻል አመልክተዋል። ስልጠናው ብዙ አባላት ሐሳባቸውን እንዲያስተካክሉ፣ ትክክለኛ የሆነ አመለካከት እንዲኖራቸው፣ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ለመራመድ በሚያስችል ሁኔታ በቂ እውቀት፣ ክህሎትና አስተሳሰብ እንዲኖራቸው አድርጓል ብለዋል።

Related stories   መካከለኛዉ ምሥራቅ ሌላ ዘመን ሌላ ጥፋት

ብልጽግና፣ በሁሉም የአገሪቱ አቅጣጫ የሚገኙ ፓርቲዎችን አቅፎ ወጥ ፓርቲ መሆኑ በራሱ እጅግ በጣም ትልቅ ድል መሆኑን ጠቅሰው፤ ፓርቲው በአዲስ መልክ ከተመሰረተ ወደ ስምንት ወር ያህል ቢሆንም በሚፈለገው ደረጃ በጣም ጠንካራና ማንኛውንም ዓይነት ፈተና ሊጋፈጥ የሚችልና አርኪ ሆኖ እንዲወጣ ተጨማሪ ሥራዎች እንደሚያስፈልጉት ኃላፊው አስታውቀዋል።

አዲስ ዘመን ጳጉሜን 3/2012

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0