ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አድርገው ሾመዋል።
ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት በፓለቲካ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ከቆዩ አንጋፋ ሰዎች መካከል አንዱ ናቸው።
በአሁን ወቅት የተፎካካሪ ፓርቲው የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር ሆነው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።
ፕሮፌሰር በየነ የተለያዩ ፓርቲዎችን በአባልነት የያዘውን የመድረክ ፓርቲንም በሊቀመንበርነት መርተዋል።
እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በመምህርነት ሲያገለግሉ የቆዩ ምሁር ናቸው።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   «አባ ገዳዎች ያስተላለፉትን ውሳኔ ተቀብሎ ህዝቡ ኦነግ ሸኔን ለማፅዳት በየዞኑ ተግባራዊ እያደረገ ነው»

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *