የኢፌዴሪ አየር ኃይል ለ1 ሺህ 29 የአየር ኃይል መኮንኖች የማእረግ እድገት ሰጠ።
የማእረግ እድገቱን የአየር ኃይሉ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ይልማ መርዳሳ ሰጥተዋል። በዚህ ወቅት እንደተናገሩት ÷ የማእረግ እድገቱ ለተጨማሪ ኃላፊነት የሚጋብዝ በመሆኑ መኮንኖቹ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ለስኬት ማብቃት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በእለቱ የአየር ኃይል ከፍተኛ አመራሮችን ሀብት ማስመዝገብ፣ የተቋሙ የድረ ገፅ ምርቃት እና የአብራሪዎች ትጥቅ ትውውቅ ተደርጓል።
በዝግጅቱ ላይ የሰራዊቱ አባላት “ለገበታ ለሀገር” ፕሮጀክቶች የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለመስጠት ቃል መግባታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
Related stories   ዲጂታል “ወያኔ”፤ የ “እረኛውን ግደል፣ መንጋው ይበተናል” መርህ ያስፈጽማል፤ መሪዎቹ የፌደራል መንግስቱን እንታደግና ህግ ይከበር ጥሪ ያሰማሉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *