በ2013 ዓ.ም መንግስት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት ህከምና ለሚከታታሉ ዜጎች አመቱን ሙሉ የህክምና ወጪያቸው በመንግስት የሚሸፈን መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ምክትል ከንቲባዋ የምስጋና ቀንን ምክንያት በማድረግ የዘውድቱ ሆስፒታል ለይቶ ማቆያን ጎብኝተዋል። በመንግስት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት ህከምና ለሚከታታሉ ዜጎች አመቱን ሙሉ የህክምና ወጪያቸው በመንግስት የሚሸፈን መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባዋ ገልጸዋል።
ህሙማኑ በሳምንት ሶስት ጊዜ የኩላሊት እጥበት በማድረግ ለከፍተኛ ወጭ እየተዳረጉ መሆኑ ይታወቃል። ስለሆነም መንግስት ችግሩን ተረድቶ ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚያደርግ መሆኑን ወይዘሮ አዳነች ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት በሶስት የመንግስት ሆስፒታሎች ማለትም በሚኒሊክ፣ ዘውዲቱና ጳውሎስ ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል።
በእነዚህ ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት እያደረጉ ላሉ ዜጎች በ2013 ዓ.ም አመቱን ሙሉ ወጪያቸው እንደሚሸፈን ምክት ከንቲባዋ ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
 • “የአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎችን ላለመላክ የወሰነው የማይታዘዝና የማያጎበድድ መንግሥት ይመጣል የሚል ስጋት ነው”አንዳርጋቸው ፅጌ
  ”የአውሮፓ ህብረት ነፃ ፉክክር፤ ነፃ ሚዲያ እና ነፃ የምርጫ ቦርድ ባልነበረበት ይታዘብ የነበረው ለኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ስርዓት ተቆርቋሪ ሆኖ አልነበረም ታዛቢዎችን ላለመላክ የወሰነው የማይታዘዝና የማያጎበድድ መንግሥት ይመጣል የሚል ስጋት ነው”  ፖለቲከኛና የኢሳት ሥራ አስኪያጅ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ አስታወቁ። ታዛቢዎችን ላለመላክ የወሰነው ለህብረቱ ሀገራት የማይታዘዝና የማያጎበድድ መንግሥት ይመጣል የሚል ስጋት ስላለው መሆኑንContinue Reading
 • የአውሮፓ ህብረት የይስሙላ ምርጫዎች ሲታዘብ ቆይቶ አሁን አልታዘብም ያለበትን ምክንያት ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያሳውቅ ተጠየቀ
  የአውሮፓ ህብረት የይስሙላ ምርጫዎች ሲታዘብ ቆይቶ አሁን አልታዘብም ያለበትን ምክንያት ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያሳውቅ ተጠየቀ የአውሮፓ ህብረት የይስሙላ ምርጫዎችን ሲታዘብ ቆይቶ አሁን ከታዛቢነት ለመውጣት የወሰነበትን ምክንያት ለኢትዮጵያ ህዝብ ሊያሳውቅ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት አስታወቀ። ምክር ቤቱ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ምርጫ ጉዳይ ላይ ላለመታዘብ ያሳለፈውContinue Reading
 • ምርጫውን ለማደናቀፍ ያሴሩ አካላት ህልማቸው አይሳካም – አቶ ገዱ አንዳርጋቸው
  ምርጫውን ለማደናቀፍ ያሴሩ አካላት ያሰቡት ሊሳካላቸው አይችልም – አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ምርጫውን ለማደናቀፍ የሚያሴሩ አካላት ያሰቡት በፍጹም ሊሳካላቸው እንደማይችል የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት ጉዳዮች አማካሪና የምርጫ ጉዳይ ደህንነትና ጸጥታ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አስታወቁ። ምርጫውን ለማደናቀፍ የዐመፅ ፍላጎት ያላቸው አካላት አቅደው እየሠሩ ቢሆንም የዚህ ምርጫ ዋነኛ ባለድርሻ በሆነው በኅብረተሰቡ፣ በፌዴራልናContinue Reading
 • የዓለም ጤና ድርጅት ለቻይናው ክትባት ይሁንታውን ሰጠ
  ሚያዝያ 30/2013 (ዋልታ) – በቻይና መንግሥት በሚተዳደረው ሲኖፋርም ኩባንያ የተመረተው የኮቪድ-19 ክትባት ለአስቸኳይ ጊዜ ጥቅም ላይ እንዲውል የዓለም ጤና ድርጅት ይሁንታውን ሰጠ። ድርጅቱ አርብ ዕለት የሲኖፋርም ክትባትን “ደህንነት፣ ውጤታማነት እና ጥራት” ማረጋገጡን ገልጿል፡፡ የክትባቱ ፈቃድ ማግኘት የጤና ሠራተኞችን እና ለአደጋ የተጋለጡ ዜጎችን ለመከላከል የሚያስፈልገውን የኮቪድ-19 ክትባት ተደራሽነት የማፋጠን አቅም እንዳለውምContinue Reading

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “ህወሓት” እና “ሸኔ” በሽብርተኝነት እንዲሰየሙ ወሰነ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *