ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክልሎች እና በኢንስቲትዩቱ በ150 ሚሊየን ዶላር ዘመናዊ የሆኑ ላቦራቶሪዎች ግንባታ እና የአቅም ማጎልበት ስራዎቸን እንደሚጀምር የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
የላብራቶሪ ግንባታው እና የአቅም ማጎልበት ስራው ከዓለም ባንክ በተገኘ 150 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ እና ብድር እንደሆነ ተገልጿል።
የሚገነቡት ላብራቶሪዎች ዘመናዊ እና ደረጃቸውን የጠበቁ በመሆናቸው ከኢትዮጵያ አልፎ ለምስራቅ አፍሪካ ሀገራትም ጭምር አገልግሎት የመስጠት አቅም ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡
የፕሮጀክቱ ትግበራ በአራት ዋና ዋና መርሀ ግብሮች የተከፋፈለ ሲሆን በአንደኛው መርሀ ግብር የሀገሪቷን አጠቃላይ የላቦራቶሪ አቅም የመገንባት ስራዎች እንደሚከናወኑ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ ጠቁሟል።
በመሆኑም ደረጃ ሶስት ባዮ ሴፍቲ ብሔራዊ ሪፈረንስ ላብራቶሪ በኢንስቲትዩቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገነባ ሲሆን ይህም ላቦራቶሪ ከዚህ ቀደም በሀገሪቱ የሌለና በአቅምም ሆነ በአይነቱ አዲስ እንደሚሆነም ተገልጸል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ 15 የክልል ሪፈረንስ ላቦራቶሪዎች የመገንባት እና ላቦራቶሪዎቹንም በመሳሪያ የማሟላት ስራዎች ይከናወናሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በሌላም በኩል አሁን በሀገሪቷ በስራ ላይ ያሉ 8 ላቦራቶሪዎችም የአቅም ግንባታ እና በመሳሪያ የማዘመን ስራዎች እንደሚከናወኑላቸው ተጠቁሟል።
የላቦራቶሪ ግንባታ ከ3 እስከ 4 ዓመታት የሚፈጅ ሲሆን በየክልሉ የሚገነቡት 15 ላቦራቶሪዎች ግንባታ በሁለት ዓመት ውስጥ እንደሚጠናቀቁ ይጠበቃል፡፡
እነዚህ ላቦራቶሪዎች ወደ ስራ ሲገቡ ደግሞ ከዚህ ቀደም ወደ ውጭ አገር የሚላኩ ከፍተኛ ደህንነትን የሚጠይቁ የምርመራ ስራዎችን ያስቀራሉ ተብሏል፡፡
#FBC
 
 
 
 
 
 
 
 
 • ሲሲሊ፥ ለወሲብ በባርነት የሚሸጡ ሴት ናይጄሪያውያን
  የተሻለ ሕይወት ፍለጋ በሺዎች የሚቆጠሩ የናይጄሪያ ወጣት ሴቶች ወደ አውሮፓ ይገሰግሳሉ። ብዙዎች የማያውቁት ነገር በህገ ወጥ ደላላዎች መታለላቸውን ነው። እውነታው እዛ ሲደርሱ እዳቸውን ለናይጄሪያ ማፊያዎች ለመክፈል ሲሉ ለወሲብ ንግድ ወደ ጎዳና ይወጣሉ ባለፉት ሶስት አመታት ውስጥ ከ 20 000 በላይ ሴት ናይጄሪያውያን በሜዲትራንያን በኩል አድርገው ጣሊያን ገብተዋል። አብዛኞቹ ገና 18Continue Reading
 • በመተንፈሻ መሳሪያዎችና ኦክስጅን እጥረት ሳቢያ ታካሚዎች አገልግሎቱን ሳያገኙ ለህልፈት እየተዳረጉ ነው
  በኮሮና ህክምና ማዕከላት የሚገኙ የመተንፈሻ መሳሪያዎችና የኦክስጅን አቅርቦት አነስተኛ በመሆኑ በቫይረሱ ተይዘው ወደ ማዕከላቱ የሚመጡ ታካሚዎች አገልግሎቱን ሳያገኙ ለህልፈት እየተዳረጉ መሆኑን የሚሊኒየም እና ኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል የኮቪድ19 ህክምና ማዕከላት ገልጸዋል፡፡ ህክምናውን ለመጠባበቅ  ወረፋ ይዘው የተመለሱ ዜጎችን ተራቸው ሲደርስ ሲደወልላቸው ቤታቸው ሆነው ህይወታቸው ማለፉን መስማትም የተለመደ ሆኗል ይላሉ ዶክተር ታሪኩ፡፡Continue Reading
 • ያደግንበት ኦሮሙማ
  ያደግንበት ኦሮሙማ ቁመቱ መለሎ እንደ አማዞን ዛፍ የተስተካከለ፤ አለባበሱ ዘወትር ሽክ፤ ትህትናና እንግሊዝኛ የሁል ጊዜ ማጌጫው፤ የሁላችን አባትና ከገርበጉራቻ አድባራት አንዱ፡፡ ለራሱ እንደነ ነብሪድ ያሉትን ለገርበጉራቻ ህዝብ ደግሞ አያሌ ምሁራንን ያፈራ ባለውለታ፡፡ የፊት ቅርፁ የቭላድሚር ፑቲንን የመሰለ፤ ቁመቱ ዘለግ ብሎ ሰውነቱ እንደጃንሆይ መጠጥ ያለ፤ ከቀደምት የከተማችን ዋርካዎች ተርታ የሚሰለፍ፡፡ የእነፍቅሩContinue Reading
 • ኢትዮጵያ በተራራ የተከበበች መሆኗ ዳመና አዝናቢ ኬሚካልን ወደ አየር ለመልቀቅ ምቹ መሆኑ ተገለጸ
  ኢትዮጵያ በተራራ የተከበበች አገር መሆኗ ዳመና አዝናቢ ኬሚካልን ወደ አየር ለመልቀቅ የተሻለ ዕድል እና ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር የብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አመለከቱ። ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ክንፈ ኃይለማርያም በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፣ ኢትዮጵያ የመልክአ ምድሯ መለያየት የሚታይባት፤ ተራራማ አካባቢዎች የሚበዙባት መሆኗ ዝናብ አምጪ ኬሚካሎችን ወደ ደመና ልኮ ለማበልጸግContinue Reading

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ሲሲሊ፥ ለወሲብ በባርነት የሚሸጡ ሴት ናይጄሪያውያን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *