“Our true nationality is mankind.”H.G.

ደብረጽዮን “የአማራን ሕዝብ ልዩ ክብር ይገባዋል” ፤ ኢትዮጵያን የቀይ ባህር ህልመኛ አሉዋት

ከትግራይ ሕዝብ ጋር እንዲዋጋ ሲቀሰቀስ የነበረው የአማራ ሕዝብ የጦርነት አዋጁን ባለመቀበሉ እጅግ አድረገው እንደሚያከብሩት የትግራይ ክልል መስተዳድርዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል አስታወቁ። በተመሳሳይ የወልቃይት፣ የራያና አላማጣ ነዋሪዎች አማራነታቸውን በግድ ተነጥቀውና በጥይት ተገደው ድምጽ እንዲሰጡ መደረጋቸውን አመልክተዋል። ኢትዮጵያን የቀይ ባህር ህልመኛ እንደሆነች አድረገው አቀረቧት።

ዶክተር ደብረጽዮን የሰማዕታት ሃውልት ስር ሆነው ለበበዓል ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳቹህ መልዕክት የአማራ ክልል መሪዎችን የጦርነት ነጋሪት ደብዳቢዎች አድርገው ስለዋቸዋል። ይሁን እንጂ የአማራ ሕዝብ ይህንን የጦርነት ቅስቀሳ ” አንዋጋም፣ አንፈልግም ” በማለት  ሳይቀበለው በመቅራቱ ምስጋና አቅርበዋል።

” የአማራን ሕዝብ እናከብራለን፣ ክብር ይገባዋል” ያሉት የትግራይ ክልል መሪ ምርጫ ለማስተጓጎል ሙከራ ተደርጎ በተሰጠው የአጻፋ መልስ መክሸፉን አስታውቀዋል። አያይዘውም ለኤርትራ ሕዝብ ” አብረን እንደግ” ሲሉ ጥሪ አቅረበዋል። ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ” ድንበራችን ቀይ ባህር ነው” ከሚሉ ወገኖች ጋር አብረው ለመስራት ተስማምተዋል ሲሉ ከለውጡ ማግስት የተደረገውን የኢትዮጵያና ኤርትራ እርቅ አጣመው አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ባልተጠበቀ ፍጥነት ኤርትራ ሄደው ለሁለት አስርት ዓመታት የነበረውን የጦርነት ፍጥጫ በቀየሩ ማግስት ፓሪያቸው ባደረገው ስብሰባ ላይ  ዶክተር ደብረጽዮን ” የማይታመን፣ በብርሃን ፍጥነት የሆነ፣ በህልሜ የሚመስል…” ሲሉ አድናቆታቸውን ለመግለጽ የተቸገሩበት ሁኔታ በምስል ተደግፎ መቅረቡ የሚዘነጋ አይደለም።

የአሜሪካ ሬዲዮ የትግራይ ክልል ዘጋቢ የዶክተር ደብረጽዮንን የበዓል መልዕክት ካስተላለፈ በሁዋላ የአማራ ክልል የቪኦኤ ዘጋቢ በበኩልዋ የወልቃይት እንዲሁም የራያና አላማጣ ህዝብ ምልከታ አሰምታለች። ነዋሪዎቹ በድምጽ እንዳሉት በምርጫው ቀን ጥይት የተኮሰው የትግራይ ልዩ ሃይል ሲሆን እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የታተቀ ሃይል መሰማራቱን ተናግረዋል። የተኮሱትም በአካባቢው ፋኖ ላይ እንደሆነ አንደኛው ምስክር ተናግረዋል። ተኩሱ ከአማራ ክልል ልዩ ሃይልም ሆነ ከመንግስት ወገን እንዳልሆነ ግልጸዋል።

በግድ ትግሬ እንዲሆኑ መደረጋቸውን፣ ሳይምኑ በጠብ መንጃ ሃይል ድምጽ እንዲሰጡ መደረጋቸውን ነዋሪዎችሁ ለቪኦኤ አስታውቀዋል። አያይዘውም በግድ ማንነታቸው በመጨፍለቁ መንግስት መፍትሄ ሊፈልግላቸው እንደሚገባ ጠይቀዋል። በርካታ ጉዳዮችንም አንስተዋል። ዘጋቢዋ የአማራ ክልል ባልስልታኖችን አግኝታ ሃሳባቸውን ለማካተት እንዳልቻለች አስታውቃለች።

ሁለቱንም ወገኖች ያደመጡ እንዳሉት ራያ፣ ወልቃይትና አላማጣን በሃይል ወሮ ለአማራ ህዝብ ክብር መስጠት ስድብ ነው። ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ለምን ተስማማች ብሎ ማሰብ የተለመደው የትህነግ የዘር ፖለቲካ እሳቤ ውጤት እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም። ትናንት የኤርትራ ህዝብ የዓይንህ ቀለም አስተላን ተብሎ ለፍቶ ያገነውን በአደባባይ እየተነጠቀ ወደ ኤርትራ ሲጋዝ፣ በበረሃ እንደ ቆሻሻ ሲዘረገፍ፣ ሃብቱን ከመዘርፍ በቀር ሌላ ህልም ያልነበራቸው ዛሬ በምን ሞራላቸው ለኤርትራ ተቆርቋሪ እንደሚሆኑ ለሰሚው ግራ ነው። የሚሉና ሌሎች አስተያየቶችን በተለያዩ መገናናዎች ሰጥተዋል።

በተለይም ላለፉት 27 ዓመታት የመሯትን ኢትዮጵያን የቀይ ባህር ህልመኛ አድረገው በመሳል የትህነግን ሸፍጠኛነት ግልጽ ማውጣታቸው በርካቶችን አስቆጥቷል። ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር የጀመረችውን ሰላም ለማበላሸት በሁለቱ አገራት መሪዎች መካከል ጸብ ለመፍጠር በርካታ አሉባልታዎች በስፋት ሲሰራጩ የነበረ ቢሆንም፣ የደብረጽዮን ንግግር ግን ለኢትዮጵያዊያን የህልውና ደወል መሆኑ ተመልክቷል።

ትህነግ የሚያስተዳድረውን ክልል አልፎ በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚፈተፍተው እስከመቼ እንደሆነ በጥያቄ የሚያስቀምጡ ወገኖች ህዝቡ ከመቼውም ጊዜ በላይ ህብረት ሊፈጥር እንደሚገባ የሚያስገድድ የማስጠንቀቂያ ደወል እንደሆነ የገለጹ ወገኖች፣ በአማርኛና በትግርኛ እየተከፋፈለ ሲቀርብ የነበረው የዶክተሩ ንግግር ህብረት ለመፍጠር ትልቅ ግብዓት መሆኑንን ገልጸዋል።

 

 

 

Share and Enjoy !

0Shares
0
0Shares
0