“Our true nationality is mankind.”H.G.

ሕገ ወጥና ሐሰተኛ ገንዘቦችን በሚሰበስቡ ባንኮች ላይ ኅልውናን የሚያሳጣ እርምጃ ይወሰዳል፤ ህገ ወጥ ተግባር ላይ የተሰማሩ ተለይተዋል

የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ እንዳመለከቱት “ከኢትዮጵያ ውጪ በጎረቤት አገራት ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው የኢትዮጵያ ብር ተከማችቶ ይገኛል።”
ከብር ለውጡ ጋር ተያይዞም በውጪ አገራት ውስጥ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብር ወደ አገር ውስጥ እንዳይገባ ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
ባለፈው ዓመት ብሔራዊ ባንክ ያወጣው ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ በቤት ውስጥ ማስቀመጥ የሚከለክለው ሕግም ተግባራዊ መሆኑ የሚቀጥል ሲሆን፤ ይህንን ደንብ በመተላለፍ የሚንቀሳቀስ ገንዘብ በቁጥጥር ስር ውሎ ለመንግሥት አገልግሎት ይውላል። ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ በየጊዜው ድንገተኛ ፍተሻ እንደሚኖርም ተገልጿል።
 
 
“ባንኮች” አሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ “በምንጠብቃችሁ መጠን ጠብቁን፣ ባገዝባችሁ መጠን አግዙን” አስከትለው ” እንዳንጣላ” ሲሉ እሬት የሆነውን ማስጠንቀቂያ አሰሙ። በቴሌቪዥን እንደታየው የባንኮች ቦርድ አመራሮችና ሃላፊዎች እንዲሁም የካቢኔ አባላት መካከል ትንፋሻቸውን እንደሳቡ የቀሩ የሚመስሉ ይታያሉ።
አብይ አህመድ ወተቱን ጨርሰው አጥንቱን መመገብ የጀመሩ ይመስላሉ። እጅግ እያዋዙ ማስጠንቀቂያ ሲያስተላልፉ ከወትሮው ለየት ባለ አኳኋን ነው። ” ሌቦች ላይ እንዝመት” ሲሉ የባንኮችን ስርዓት ጠብቆ መስራትና ታማኝን የመሆን ጉዳይ ላይ ደጋግመው አስምረዋል።
ዛሬ ካቢኔዎቻቸውንና የባንክ ሃላፊዎችን ሰብስበው ስለ ብር ኖት ቅያሬ መብራሪያ ሲሰጡ ህገወጥ የሆነ መንገድ የሚከተሉትን ባንኮች በውስጥ፣ በውጭና በተጠና መልኩ ክትትል እየተደረገ መሆኑንን ጠቁመው ” አንድ የተጭበረበረ ብር ከተገኝ ምህረት የለም” ብለዋል። 
የቦርድ አመራሮች የተጠሩት ስራውን በቅርብ ሆነው እንዲመሩ፣ አልሰማንም ከሚል ሮሮ እንዲታቀቡና እለት እለት ባንካቸው ህጋዊ ሆኖ መስራቱን እንዲከታተሉ ለማሳሰብ መሆኑንን ያመለከቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፣ ችግር ከተፈጠረ በሁዋላ ” አልሰማንም” የሚል ጩኸት ዋጋ ውሳኔ እንደማያስቀር አስረግጠው አስገንዝበዋል።፤
በፋይናንስ ደርህንነት መረጃ በኩል አንዳንድ ባንኮች በህገወጥ ተግባር ውስጥ እየተሳተፉ መሆኑንን መረጃ መኖሩን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በህገወጥ ተግባር የሚሳተፉ የባንክ ሃላፊዎች ወይም ባንከሮች ከወነጀል ጋር በተያያዘ ከተያዙ በማናቸውም ተቋማት በድጋሚ ተቀጥረው እንደማይሰሩ ይፋ አድረገዋል።
ያከማቹ የገንዘብ ኖት ለመቀየር በተለያዩ ሰዎች ስም ወደ ገንዘቡን አከፋፍለው የሚመጡ እንደሚኖሩ ያመለከቱት ዶክተር አብይ መታወቂያ በማየት፣ መታወቂያው ላይ ባለው አድራሻ አዲስ አካውን በመክፈት ገንዘቡን ባመጣው ሰው እንዲመዘገብ መመሪያ መውጣቱን አስታውሰዋል። ገንዘብ ካከማቹ ሰዎች በአደራ እንዲያስቀምጡ የተመረጡ አግባብ ባይሆንም ብሩን እንዳይመልሱ መክረዋል። ምክንያቱም ያለአግባብ የተሰበሰበ ነውና።
የጸጥታ አካላት መከላከያን ጨምሮ በድንበር በተለይም በሶማሌ፣ በጅቡቲ እንዲሁም በሱዳን ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚኖር ስለሚጠበቅ በቅንጅት ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። አያይዘውም የወረሳችሁትን ውሰዱት ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትርይ ይህንን ሲሉ ዋናው ዓላማቸው ተዘርፎ የተከማቸውን ብር ወረቀት ማድረግ ዋና ዓላማ በመሆኑ ነው። 
በተደጋጋሚ ባንኮችን ያሳሰቡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፣  ከብር ኖቶች መቀየር ጋር በተያያዘ ሕገ ወጥና ሐሰተኛ የብር ኖቶችን የሚሰበስቡ ባንኮች መኖራቸውን መንግሥት ከፋይናንስ ደኅንነት መረጃ አግኝቷል” በማለት በድጋሚ ካሳሰቡ በሁዋላ ‘‘አዲስ የገንዘብ የብር ኖቶች መቀየራቸውን ተከትሎ መንግሥት ሕገ ወጥና ሐሰተኛ የብር ኖቶችን የሚሰባስቡ ባንኮች ላይ ጠበቅ ያለ እርምጃ ይወሰዳል፤ የሰበሰቡትን ብር ለብሄራዊ ባንክ ስታመጡ አንድ በአንድ ማጣራት ይደረግበታል” ሲሉ አሰራሩ ላይ ጥብቅ የቁጥጥር ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል። 
መንግሥት የባንኮችን ችግር ለመፍታት የተለያዩ የመፍትሔ እርምጃዎችን መውሰዱን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‘‘ባንኮችም በተለይ አሮጌውን ገንዘብ በአዲሱ የመቀየር ሥራ ሲሠራ ሐሰተኛና ሕገ ወጥ ገንዘቦችን ከመሰብሰብ በመቆጠብ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል’’ ብለዋል።
ኃላፊነታቸው በማይወጡና ሕገ ወጥ ድርጊት በሚፈጸሙ ባንኮች ላይ መንግሥት ኅልውናቸውን እስከማቋረጥ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ ጠቅላይ ሚኒስትር በከባዱ አስጠንቅቀዋል።
በዚህ ወቅት የአዳዲሶቹ የገንዘብ ኖቶች አብዛኛው የሕትመት ሥራ ተገባድዶ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ግምጃ ቤት እንደሚገኝና የስርጭት ሥርዓት እና ዕቅድ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
ኢትዮጵያ ገንዘቧን የሚወክል ምልክት እንዳልነበራት ይታወቃል። በቅርቡ ለብር መለያ የሚሆን አዲስ ምልክት ተዘጋጅቶ በጥቅም ላይ እንደሚውልም ተገልጿል።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   የሲኤንኤን ዘጋቢ ኒማ- በተወነችው ተውኔት ውስጥ ዳግም ሞት የተፈረደባቸው ዜጎች
0Shares
0