“Our true nationality is mankind.”H.G.

“በጥቁር ገበያ” የገንዘብ ምንዛሪ አገልግሎት የተጠረጠሩ ሱቆች ታሸጉ

የኢትዮጵያ መንግስት አሁን በአገልግሎት ላይ የሚገኙትን የብር የገንዘብ አይነቶች እንዲሚቀይር በትላንትናው ዕለት ማስታወቁን ተከትሎ የ“ጥቁር ገበያ”ውን ለመቆጣጠር እርምጃ መውሰድ ተጀመረ።

በአዲስ አበባ ከባንክ ውጭ የሚደረጉ የውጭ ሀገር ገንዘብ ግብይቶችን በድብቅ ያከናውናሉ ከተባሉ ሱቆች መካከል የተወሰኑት ከትላንት ጀምሮ እንዲታሸጉ ተደርገዋል።

የእርምጃው ሰለባ የሆኑት በይፋ ከሚታወቁባቸው አገልግሎቶች ባሻገር የውጭ ሀገር ገንዘቦች ምንዛሬን በተደራቢነት የሚሰጡ ሱቆች ናቸው። በኢትዮጵያ ሆቴል እና ጋንዲ ሆስፒታል አካባቢ የሚገኙት እነዚህ ሱቆች “ታሽጓል” የሚል ጽሁፍ እና ማህተም የሰፈረባቸው ወረቀቶች በየበሮቻቸው ላይ መለጠፋቸውን ዛሬ ረፋዱን በቦታው የተገኘው የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘጋቢ ተመልክቷል።

በሱቆቹ አካባቢ የአዲስ አበባ ፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሱ የጸጥታ ኃይሎች በርከት ብለው የሚታዩ ሲሆን የተወሰኑቱ በወንበሮች ላይ ተቀምጠው ጥበቃ ሲያደርጉ ተስተውለዋል።

Related stories   “ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን በአንድነት በመከባበር፤ በመተሳሰብ እና በመረዳዳት ሊያከብር ይገባል”

ፖሊስ የተወሰኑ ሱቆች የሚገኙባቸውን እና ቀደም ሲል እግረኞችና ተሽከርካሪዎች ይተላለፉባቸው የነበሩ መጋቢ መንገዶችን ለተጠቃሚዎች ዝግ አድርጓል። ከተዘጉት መንገዶች መካከል ከጋንዲ ሆስፒታል ወደ ብሔራዊ ትያትር የሚወስደው ማቋረጫ እና ከኢትዮጵያ ሆቴል ጎን የሚገኝ፣ ተሽከርካሪዎች በአንድ አቅጣጫ ብቻ የሚተላለፉበት መስመር ይገኙበታል።

በሱቆቹ አቅራቢያ ሸቀጦችን በመቸርቸር የሚተዳደር አንድ ወጣት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” እንደተናገረው፤ ሱቆቹ የተዘጉት ትላንት ሰኞ አስር ሰዓት ገደማ በአካባቢው ድንገተኛ ፍተሻ ከተደረገ በኋላ ነው። በአካባቢው ባለ ሆቴል እና ፋርማሲ የሚሰሩ ሁለት ግለሰቦች ይህንኑ የወጣቱን ገለጻ አረጋግጠዋል።

የትላንትናው ድንገተኛ ፍተሻ በሚደረግበት ወቅት የፊት እና የጉልበት መከላከያ ያደረጉ የፌደራል ፖሊስ አባላት በአካባቢው ጥብቅ የጸጥታ ቁጥጥር ሲያደርጉ እንደነበር ወጣቱ ገልጿል። በፍተሻው ጋንዲ ሆስፒታል አካባቢ በነበሩ ሱቆች የተቀመጡ የውጭ ሀገር ገንዘቦች በጸጥታ ሃይሎች እንደተወሰዱ መስማቱንም አክሏል።

ዛሬ የታሸጉት ሱቆች

ነባሮቹ የ10፣ የ50 እና የ100 ብር መገበያያዎች መቀየራቸውን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በትላንትናው ዕለት በሰጡት ማብራሪያ፤ ከፋይናንስ ተቋማት ውጪ የተከማቹ ገንዘቦችን ለመያዝ በየቦታው ድንገተኛ ፍተሻ እንደሚደረግ አስታውቀው ነበር። ድንገተኛ ፍተሻዎቹ የሚደረጉት “በሚጠረጠሩ ቦታዎች” ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ አሰሳ የግለሰብ ቤትም ይሁን የንግድ ቦታ ሊካተት እንደሚችል ጠቁመዋል።

Related stories   የሲኤንኤን ዘጋቢ ኒማ- በተወነችው ተውኔት ውስጥ ዳግም ሞት የተፈረደባቸው ዜጎች

“የሕግ አስከባሪ ተቋማት አንደኛ ጥቁር ገበያ፤ ሁለተኛ አየር መንገድ ከዛሬ ጀምሮ ባስቀመጥንው አቅጣጫ መሠረት እያንዳንዷ ሻንጣ ማስወጣት፤ ማስገባት በማይችል በአየር መንገድ ጥብቅ ሴኪዩሪቲ ይደረጋል። በድንበር አካባቢዎች በተለይ ከጅቡቲ ሶማሌ ሱዳን ከፍተኛ ገንዘብ እንዳለ ይታወቃል። በነዳጅ ቦቴም ይሁን በተለያየ መንገድ ገንዘቡ እንዳይገባ የሕግ አስከባሪ ተቋማት በወጣው ዕቅድ መሠረት ከመነሻው ጀምሮ ሰፊ ጥበቃ ያደርጋሉ። እኛ ገንዘቡን አንፈልገውም። ወርሰው የሕግ አስከባሪ ተቋማት ይጠናከሩበታል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስጠንቅቀዋል።

Related stories   ኦሮሞ ኦሮሞን አድፍጦ እየገደለ ነው፤ ኦነግ ሸኔ ለስራ የሚጓዙ አምስት ኦሮሞዎችን ገደለ

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ባለፉት ሁለት ተኩል ዓመታት የአሸባሪው የወንበዴዎች ቡድን ህወሓት አባላትና ደጋፊዎች ብር ይቀየራል በሚል እሳቤ ከሕዝብ የዘረፉትን ወደ ዶላር ሲቀይሩ እንደነበር ይታወቃል። የብር ኖቶች መቀየራቸውን ተከትሎ ይህንን ሥራቸውን በሥፋት እንደሚያከናውኑት በመረዳት በተለይ በዳያስፖራ የሚገኘው ወገን ለጥቂት ብሮች ልዩነት በሚል በጥቁር ገበያ የሚልከው ገንዘብ መልሶ አገር ለማፍረስ ተግባር እንደሚውል በመገንዘብ ከዚህ ሥራ እንዲታቀብ አገራዊ ጥሪ ቀርቧል።

ጭንቅላቱ የደረቀውና መቀሌ በየሆቴሉ የመሸገው ራሱን ህወሓት እያለ የሚጠራው የወንበዴዎች ጥርቅም በቅርብ ጊዜ ውስጥ ኪሱም እንደሚደርቅ ይጠበቃል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0