“Our true nationality is mankind.”H.G.

ስልጠና ላይ ከነብሩ አምባሳደሮች መካከል በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ አሉ

ኮሮና ቫይረስ አጥቅቷቸዋል በሚል ስለተጠቀሱት የኢትዮጵያ አምባሳደሮች @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia በሚልስያሜ የሚለይ የቴሌግራም ገጽ የሚከተለውን ዘግቧል።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ “በቢሾፍቱ ከተማ ስልጠና ላይ ከነበሩ አምባሳደሮች መካከል ሃያ አንዱ (21) በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ታውቋል ፣ እንዲሁም የUN አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ወደ ኒው ዮርክ አይመለሱም” የሚል መረጃ በስፋት እየተሰራጨ ተመልክተናል።

በዚህ ጉዳዩ ላይ ስማቸውን የማንገልፅላችሁ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራሮች/እንዲሁም በስልጠናው ላይ ተሳታፊ ከነበሩት መካከል አንድ ሰው ተከታዩን ብለውናል ፦

Related stories   ፋኦ በትግራይ ክልል ለአርሶ አደሮች የእህል ዝርያዎችን ማሰራጨትና እንስሳቶችን መከተብ ጀመረ

“አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ወደ New York ትላንትና እንደሚበሩ ነግረውኛል። አዲስ ነገር አልሰማሁም። 21 አምባሳደሮች በCOVID-19 አልተያዙም።

ነገር ግን ከስብሰባችን በኋላ አንዴ ከመውጣታችን በፊት ከዛም አርብ እለት ምርመራ አድርገናል ነገር ግን የጤና መረጃ የግል confidential ስለሆነ በትክክል ቁጥሩን መናገር አልችልም።

ከአምባሳደሮቻችን መካከል ወደ አስራ አምስት (15) የሚሆኑ ወደየሚሰሩበት ሀገር ተመልሰዋል። አሁን ደግሞ እዚህ MINT ያዘጋጀው program ላይ አብዛኞቻችን አለን።

Related stories   የዘረኝነት ጥግ “እናት ነኝ የሌሎች ህፃናት ወላጆችን ግን ገደልኩ”

ቁጥሩን ባላውቀውም 21 ግን እንዳልሆኑ እርግጠኛ ነኝ ከላይ በጠቀስኩት ምክንያት።”

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0