“ኢትዮጵያን ተጽዕኖ ፈጣሪ አገር ማድረግ የምንችለው ዛሬ ላይ ለቴክኖሎጂ ትኩረት ሰጥተን ከሰራን ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ተናገሩ።

በመሆኑም ወጣቶች በቴክኖሎጂ ዘርፍ ላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲመራመሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ማዕከል ዛሬ መርቀው በይፋ ስራ ባስጀመሩበት ወቅት ነው።

ማዕከሉ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀሳብ አመንጪነት በ2012 ዓ.ም የተቋቋመ ነው።

አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ማሽኖች ሰው ሰራሽ የሆነ የማሰብ ክህሎትን በተለያዩ የስራ መስኮች የሚያሰማራ ቴክኖሎጂ ነው።

ማሽኖቹ ሙሉ ለሙሉ ራሳቸውን ችለው ለሰው ልጅ አድካሚ የሆኑ ተግባራትን በፍጥነት ማከናወን እንደሚችሉም ነው የተገለጸው።

Related stories   ሲሲሊ፥ ለወሲብ በባርነት የሚሸጡ ሴት ናይጄሪያውያን

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ማዕከሉን ስራ ባስጀመሩበት ወቅት አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በተለይ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገች ላለችው ኢትዮጵያ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

ቴክኖሎጂው በኢትዮጵያ በተለይ ለጤና፣ ለግብርና፣ ትምህርት፣ እንዲሁም ለህዝብ ጥበቃና ደህንነት አገልግሎቶች እንደሚውል ነው ያብራሩት።

ኢትዮጵያ የብዙ ባህል፣ ቋንቋና ማንነት አገር ብትሆንም በቴክኖሎጂና እውቀት ውስንነት ምክንያት የኢኮኖሚ ምንጭ ማድረግ እንዳልተቻለ ተናግረዋል።

በአንጻሩ ውስን ህዝብ ያላት እስራኤል “የሂብሩ ቋንቋን” በኮምፒውተር በመታገዝ በቀላሉ መማር እንዲቻል ማድረጓን ለአብነት አንስተዋል።

ከዚህ አንጻር በማዕከሉ ያሉ ማሽኖች የአማርኛ፣ ኦሮሚኛ፣ ትግርኛና ሶማሌኛ ቋንቋዎችን በመጠቀም እንዲተገብሩ መደረጉንም አውስተዋል።

Related stories   ሲሲሊ፥ ለወሲብ በባርነት የሚሸጡ ሴት ናይጄሪያውያን

ከ30 ዓመት በኋላ ኢትዮጵያን ከዓለም 20 ተጽዕኖ ፈጣሪ አገሮች መካከል አንዷ እንድትሆን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው፤ ”ለዚህ ደግሞ ዛሬ ላይ ለቴክኖሎጂ ትኩረት ሰጥተን መስራት አለብን” ብለዋል።

በመሆኑም በተለይ ወጣቶች ከማዕከሉ ጋር ግንኙነት በመፍጠር ምርምሮቻቸውን በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እንዲደግፉ በማድረግ ተፈላጊ ሙያተኞች እንዲሆኑም መክረዋል።

አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሰው ልጅ ሊደርስባቸው የማይችሉ ተግባራትን በፍጥነት ያከናውናል እንጂ የሰውን ልጅ ስራ ሙሉ ለሙሉ እንደማይተካም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወርቁ ጋቸና በበኩላቸው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ስራ ላይ መዋል ድምጽን በመጠቀም ብቻ ማንኛውንም ተግባር ለማከናወን እንደሚያስችል ገልጸዋል።

Related stories   ሲሲሊ፥ ለወሲብ በባርነት የሚሸጡ ሴት ናይጄሪያውያን

መጻፍ የማይችሉ ሰዎች የባንክ አገልግሎትን በቀላሉ መጠቀም እንዲችሉ እንደሚያደርግ ለአብነት አንስተዋል።

በመሆኑም ማሽኖቹ የአማርኛ፣ ኦሮሚኛ፣ ትግሬኛና ሶማሌኛ ቋንቋዎችን እንዲተገብሩ መሰራቱን ገልጸዋል።

ማዕከሉ በቀጣይ በዩኒቨርሲቲዎች ያሉ ወጣቶች ለቴክኖሎጂው ቅርበት እንዲኖራቸው ስልጠና ከመስጠት ጀምሮ የተለያዩ ተግባራትን እንደሚያከናውንም ጠቁመዋል።

ማዕከሉ አሁን ላይ በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ የተደገፉ የጡት ካንሰርና የጭንቅላት እጢ የጤና እክሎችን መለየት የሚያስችሉ መተግበሪያዎች እየሰራ ይገኛል።

ENA

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *