“Our true nationality is mankind.”H.G.

በሕዝብ ጥቆማና በጸጥታ ሃይሎች ክትትል አራት ሚሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ አልጋ ስር ተደብቆ ተገኘ፤

ቀደም ባሉት ዓመታት መጠኑ ይህን ያህል ባይሆንም ከሰበታ አንድ የመሬት ምሪት ሃላፊ መሐንዲስ መኖሪያ ቤት ሮቶ የውሃ ጋን ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው ብር ተይዞ ነበር። ከዚያ ግዜ በሁዋላ ገንዘብ አልጋ ስር ተቀብሮ ሲገኝ በብዛትም በዓይነትም ይህ ትልቁ ነው።

ባሌስትራ ወርቅ ነው በማለት በቅንጅት ብሄራዊ ባንክን ሲዘርፉ የነበሩ ከበርካታ ጩኸት በሁዋላ ዋናዎቹ ጠግበው ከኮበለሉ በሁዋላ በቁጥጥር ስር የዋሉት ዱርዬ ሃብታሞች ቤት ሲፈተሽ ብር የተገኘው እመኝታ ስር በተሰራ የአርማታ ጉድጓድ ውስጥ ነበር። አንደኛው ተጠርጣሪ በአርማታ እተሰራው ጉድጓድ ላይ ዘመናዊ ማድራስ አድርጎ ለእናቱ ከላይ ያስተኛ ነበር። ይህ ዜና በውቅቱ አስገራሚ ነበር።

Related stories   “አቡነ ማቲያስ የሰጡት መግለጫ የግላቸው እንጂ የቅዱስ ሲኖዶስ ወይም የቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ አይደለም”

ዛሬ ከሰበታ የተሰማው ሌላ ዜና ደግሞ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ብሮች አልጋ ስር ተከማሽቶ መገነቱ ነው። የተገኘው ደግሞ አንድ ፓኪስታናዊ ተከራይቶ በሚኖርበት የመኖሪያ ቤት ውስጥ ነው። ፋና የከተማውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቀነኒሳ ዳዲ ጠቅሶ እንደዘገበው ከ3 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ የእገር ውስጥ ብርና የውጭ ሀገራት ገንዘቦች በተጠቀሰው ሰው ቤት ተከማችቶ ተይዟል።

ከተማው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቀነኒሳ ዳዲ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት የተያዘው ገንዘብ 3 ሚሊየን 751 ሺህ 830 የኢትዮጵያ ብር፣ 2 ሺህ 950 የአሜሪካ ዶላር እና የዱባይ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬት፣ የፓኪስታንና የኦማን ገንዘቦች ናቸው፡፡

Related stories   አየር ሃይል " ትዕግስትም ልክ አለው" ሲል ለሱዳን ምክረ ሃሳብ ሰጠ

በከተማው የ3ኛ ክፍለ ከተማ የፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ታደሰ ሁሪሳ ገንዘቡ በግለሰብ ቤት ውስጥ አልጋ ስር ተከማችቶ የተያዘው በህብረተሰቡ ጥቆማና በፀጥታ መዋቅር ክትትል ነው ብለዋል፡፡ገንዘቡ የተያዘው አንድ ፓኪስታናዊ ተከራይቶ በሚኖርበት የመኖሪያ ቤት ውስጥ ነውም ብለዋል ኃላፊው፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ወደ ፊትም ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርና ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር በትኩረት የሚሰራ መሆኑን አቶ ቀነኒሳ ዳዲ ተናግረዋል፡፡

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0