” እንዴት ብትንቁን ነው” ሲል ባለቤት ቁጣ የተሞላ ምላሽ ሰጠ። ባልና ሚስት የቆየ ወዳጆቻቸው ቤት ሄደው እንደ ሃበሻ ወግ ከተጋበዙ በሁዋላ  ” ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ ውሰዱልን” ብለው ሲጠይቃሉ። እንግዶቻቸውን እየጋበዙ ያሉት ቤተሰቦች ምን ያህል እንደሆነ ይጠይቃሉ። እንግዶች ” ሁለት መቶ ሺህ ” ሲሉ ይመልሳሉ።

ጥያቄው የቀረበላቸው ሰዎች በመደነቅና በተደበላለቀ ስሜት ” ሁለት መቶ ሺህ ዶላር ?” ሲሉ በመገረም ማብራሪያ እንደሚፈልጉ ይገልጻሉ። ” አይደለም የኢትዮጵያ ብር” ሲሉ እንግዶች ይመልሳሉ። ከዛም አንድ ሁለት ይባባሉና ይካረራሉ። ጥያቄው የቀረበላቸው ቤተሰቦች በተለይም ባል ” እንዴት ብትንቁን ነው ” ሲል ቅሬታውን በቁጣ ያሰማል። በዛው የቃላት ልውውጡ በርትቶ በሚስት ሸንጋይነት እንግዶች ቤቱን ለቀው የሄዳሉ። ነገሩ እንዲህ ነው።

ለርዥም ዓመታት አሜሪካን አገር የኖሩ እናት ከእርጅና ጋር በተያያዘ ስለተዳከሙና ስለታመሙ ” ለአገሬ አፈር አብቁኝ” በማለት ልጃቸውን ወትውተው ወደ አዲስ አበባ ለማምራት ከሁለት ቀን በፊት ጉዞ ነበራቸው። በጣም ስለተዳከሙ ቤተሰቦቻቸው አዲስ አበባ በሰላም እንዲደርሱ ለእሳቸው ድጋፍ ስለማድረግና ስለ ጉዞው ከማሰብና ከመቸነቅ ውጪ ሌላ ሃሳብ አልነበራቸውም። ጉዞው ረዥምና የስንበትም ዓይነት በመሆኑ!

በዚህ መሃል ነበር የቀድሞ ወዳጆቻቸው ልጅ እናቱን ይዞ ወደ አገር ቤት እንደሚያመራ በመስማታቸው ለጉብኝት የሄዱት። ይሁን እንጂ  ጉብኝቱ ሁለት ዓላማ ያለው ነበረው። መሰናበትና ብር መላክ። ለዚህም ውለታ ክፍያ መስጠት።

ድርጊቱን በስልክ የተከታተለች ለዛጎል እንደነገረችው ሁለት መቶ ሺህ የኢትዮጵያ አሮጌ ብር ወደ አገር ቤት ለመላክ የቀረበው ጥያቄ መጨረሻው የበርካታ ዓመታት ወዳጅ ቤተሰቦችን አለያይቷል። ወዳጅነታቸው ተበጥሷል። በደከሙ እናት ሻንጣ ውስጥ በመደበቅ ገንዘቡን ወደ ኢትዮጵያ እንዲሄድላቸው የጠየቁት ሰዎች ሌላም ብር እንዳላቸው፣ ብሩንም በተለያዩ ጊዜያት ወደ አሜሪካ ንብረት ሸጠው እንዳመጡት አስረድተዋል።

Related stories   "በፕሮፓጋንዳ እስካሁን የተወናበድኩት ይበቃኛል ብሎ ቆም ብሎ ማሰብም ይገባል ... ወጣቱን ያለ እድሜው ህይወቱን ይቀጩታል"ሌ.ጀ ዮሐንስ

ለዛጎል ታሪኩን ያስረዳችው ” ተደፈርን ” ያሉት ቤተሰቦች ዘመድ ስትሆን ይህንን መረጃ ከሰማች በሁዋላ ፊንላንድና ሎንደን ከባልደረቦቿ ጋር በዚሁ አስገራሚ ጉዳይ ስትወያይ እነሱ አካባቢም በተመሳሳይ መልኩ ጥያቄው እንደሚቀርብ ጠቅሰው ይህንን ጉዳይ የኤርፖርት ሃላፊዎች እንዲሰሙ ቢደረግ መልካም እንደሆነ እንደነገሯትና ለዛጎል ለመግለጽ እንዳነሳሳት ገልጻለች።

” ማሰብ የተሳነን ይመላል። እናት የደከመባቸውን ቤተሰቦች በህገወጥ ገንዘብ ውሰዱልን። ወሮታ እንከፍላለን ማለት ፍጹም ሰዋዊ አይደለም። ሰው ራሱ ህገወጥ መሆኑ ሳያንሰው ሌሎችን ህገወጥ ለማድረግ መድፈሩ ያስገርማል” ብሎ እናቷ የደኩማባት ዘመዷ ባለቤት መናገሩንና እልህ መጋባቱን የገለጸችው ሴት፣ ከድንበር ጥበቃ ባልተናነሰ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጓዦች፣ እንዲሁም የበረራ ሰራተኞች ላይ ጠንካራ ፍተሻና ቁጥጥር ሊደረግ እንደሚገባ መክራለች።

ከሁሉም በላይ ግን በአሜሪካና በአውሮፓ የኢትዮጵያ ብር በግለሰቦች እጅ እንዳለ ማረጋገጧ አንዳስገረማት፣ ይህም ገንዘብ በአየር መንገድ በኩል ስለመውጣቱ ጥርጥር እንደሌለውና ማምከን የሚቻለውም የወጣበትን ቀዳዳ በመድፈን እንደሆነ አመልክታለች። ሕዝብ ገንዘብ መቀየር የተፈለገበት ምክንያት ግልጽ ከሆነለት በተመሳሳይ የሚቀርቡለትን ጥያቄዎች ወደ ጎን በማለት ወደ ህግ በማቅረብና ጥቆማ በመስጠት ሊተባበር እንደሚገባም አመልክታለች። ለወደፊቱም በተመሳሳይ መረጃ ከመስጠት ወድሁዋላ እንደማትል አስታውቃለች።

ጥቆማ ሰጪዋ የሰዎቹን ስምና የመኖሪያ ከተማ የገለጸች ቢሆንም ከማተም ተቆጥበናል። መንግስት የብር ኖት እንደሚቀየር ይፋ ካደርረገ በሁዋላና በፊት ከፍተኛ መጠን ያለው የአግር ውስጥና የተላያዩ አገራት የብር ኖቶች በፍተሻ ኬላዎች ላይ መያዛቸው ሪፖርት ሲደረግ መሰንበቱ ይታወቃል።

Related stories   አቡነ ማቲያስ መነጋገሪያ ሆነዋል - ኢትዮጵያ ላይ ዘመቻው እንዲከር ጥሪ አቅርበዋል

በኢትዮጵያ ከ113 ቢሊዮን ብር በላይ ከመንግስት ባንክ ቁጥጥር ወይም ስርዓት ውጪ እንደሚንቀሳቀስ፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ህገወጥ የብር ኖት ገበያው ላይ መሰራቸቱ አንድ ላይ ተዳምሮ የአገሪቱን የግሽበት መተን እንዳናረው ባለሙያዎች ሲናገሩ፣ መንግስትም ይህንኑ አውቆ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል።

የብር ኖት ለውጡ ይፋ ከሆነ በሁዋላ ውሳኔውን እጅግ አክርረው የሚቃወሙ ወገኖች መሰማታቸው ጉዳዩን አስገራሚ እንዳደረገው ከተለያዩ ባለሙያዎች እየተደመጠ ነው። ማንም ተቃዋሚም ሆነ የመንግስት አካል ህገወጥ ገንዘብ የአገሪቱን ኢኮኖሚ እያሽመደመደና ለሽብር ተግባር እየዋለ ባለበት ወቅት የመንግስትን ውሳኔ መቃወሙ ” ህገወጥ ገንዘብና ህገወጥነት ይሻለኛል በማለት አገሪቱ ላይ ማፊያ እንዲፈነጭ መፈቀድ ነው” በሚል ክፉኛ ተተችቷል።

 • የቻይናው ሮኬት ስብርባሪ በኢትዮጵያ ቢወድቅ ምን ዓይነት የጥንቃቄ እርምጃዎች ሊወስዱ ይገባል?
  ከቁጥጥር ውጪ የሆነው የቻይና ሮኬት አካል ስብርባሪ በኢትዮጵያ ቢወድቅ ምን ዓይነት የጥንቃቄ እርምጃዎች ሊወስዱ ይገባል? ። የቻይናው 5 ቢ ሮኬት ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ወደ መሬት ለመምዘግዘግ ምድርን በመሽከርከር ላይ ይገኛል። 5 ቢ ሮኬት ከቁጥጥር ውጭ ከሆነበት ከሚያዝያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. እንስቶ በከፍተኛ ፍጥነት በመሬት ዙሪያ እየተሸከረከረ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ስፔስContinue Reading
 • ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መግለጫ
  ጠላቶቿ ፈርሰው ያልቃሉ እንጂ ኢትዮጵያ መቼም አትፈርስም፤ አዲስ አበባም ከሰላማዊ የብልፅግና ጉዞዋ አትስተጓጎልም! ሀገራችን ኢትዮጵያ በታሪኳ ለበርካታ ጊዜያት ከውጭ ጠላቶች ወረራ እና መሰል ጥቃቶች ተሰንዝሮባታል፤ ሁሉንም የውጪ ወረራ እና ጥቃቶችን በጀግኖች ልጆቿ በመመከት ጠላትን አሳፍራ መመለስ የቻለች ሲሆን በአንፃሩ ደግሞ ከአብራኳ የወጡ ከሃዲዎች እና ባንዳዎች ከውጭ ጠላት ጋር በማበር ሲያደሟትContinue Reading
 • አቡነ ማቲያስ መነጋገሪያ ሆነዋል – ኢትዮጵያ ላይ ዘመቻው እንዲከር ጥሪ አቅርበዋል
  ከትሀንግ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው መረጃ የተያዘባቸው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ሰፊ መነጋገሪያ ሆነዋል። በአዎንታና በአሉታዊ ጎን የተሰነዘረባቸው ተቃውሞ መነሻው ” ታፈንኩ” በማለት ሲናገሩ የሚያሳይ ቪዲዮ ወዳጆቻቸው ወይም የቅርብ ታዛዦቻቸው ካሰራጩና ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በኤፒ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ በቲውተር ገጻቸው ካሰራጩት በሁዋላ ነው። ቪዲዮውን ተከትሎ ሙስሊም የኢትዮጵያ ልጆች የአፍጢር ስነContinue Reading
 • Warshaan Keenyaa tiraaktaroota 950 qonnaan bultootaaf dabarse
  Magaalaa Shaashamanneetti kan argamu Warshaan Meeshaalee Qonnaa Ammayyaa Keenyaa kaleessa tiraaktaroota 950 qonnaan bultootaaf dabarse. Sirni walharkaa fuudhiinsaas qonnaan bultoota, dargaggoota waldaan gurmaa’aniifi dhaabbata Keenyaa gidduutti taasifameera. Sirnicharratti Pirezdaantiin Mootummaa Naannoo Oromiyaa, Obbo Shimallis Abdiisaa dabalatee hoggantoonni olaanoo federaalaafi naannolee, akkasumas abbootiin gadaa argamaniiru. Tiraaktaroota 950 qonnaan bultootaafi dargaggoota waldaanContinue Reading

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *