6ኛውን ሃገራዊ ምርጫ ለማከናወን የሚያስችሉ ሁሉንም ቁሳቁሶዎች ከውጭ ሃገር ገዝቶ ወደ ሃገር ውስጥ በማስገበት ዝግጁ ማድረጉን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ አደረገ።
መጋቢት 2012 ዓ.ም የኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ መከሰቱን ተከትሎ 6ኛው ሀገራ ምርጫ መራዘሙ ይታወሳል።
የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በተያዘው ዓመት እንዲካሄድ እና የኮቪድ 19 ወረሽኝን መከላከልን መሰረት ያደረገ የምርጫ ዝግጅት እንዲጀመር ውሳኔ ማሳለፉ የሚታወስ ነው።
የብሄራዊ ምርጫ ቦርዱ የኮሙዩኒኬሽን አማካሪ ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ÷ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት የተጀመረውን የምርጫ ሂደት በመሃል እንዲቋረጥ ቢያደርግም ቦርዱ ባለፉት 5 ወራት ሰዎችን ከቦታ ወደ ቦታ የማያንቀሳቅሱ ሰራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል ብለዋል።
በዚህም ቦርዱ ከስልጠና ጀምሮ በድምጽ መስጫ ቀን ጥቅም ላይ የሚውሉ ቁሳቁሶችን በሙሉ ዝግጁ እንዲሆኑ ማድረጉን ገልጸዋል።
ከእነዚህም መካከል መየራጮች ምዝገባ ወረቀትና ካርድ ፣በአምስት ቋንቋዎች የተዘጋጁ የምርጫ አስፈጻሚዎች ማሰልጠኛ መመሪያ፣ የማሰልጠኛ ቁሳቁስ፣ ስድተኛው ሃገራዊ ምርጫ እና አካባቢያዊ ምርጫዎችን ለማድረግ የሚያስችሉ የድምጽ መስጫ ሳጥንም ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ቦርዱ በኮሮና ቫይረስ ተጽህኖ ስር ሆኖ ካከናወናቸው ተግባራት አንዱ አቅሙን በቴክኖሎጂ ማሳደግ ይገኝበታል ብለዋል።
እንደ ኮሚኒኬሽን አማካሪዋ ገለጻ ÷ የመራጮች ምዝገባ በመዝገብና ካርድ ላይ የሚደረግ ቢሆንም እስከ ድምጽ መስጫ ቀን ድረስ ያሉ መረጃዎችን ለመያዝ፣የመራጮች ቁጥርን እና የምርጫ ውጤት በፍጥነት ለማሳወቅ ይደረዳል።
ከዚህ ባለፈ ምርጫ አስፈጻሚዎች ከመራጩ እና ከሌሎች ሰዎች የሚለዩበትን አልባሳት ጨምሮ በምርጫው ቀን ጥቅም ላይ የሚውሉ በርከት ያሉ ግብዓቶችም ዝግጁ መደረጋቸውን አማካሪዋ አረጋግጠዋል ።
እስካሁን በሃገሪቱ የምርጫ ታሪክ ያልነበረ እና በምርጫው ታማኝነት ላይ ከፍተኛ ቦታ ያለው የድምጽ መስጫ ቦታ መከለያ ተጠቃሽ ነው ተብሏል።
ይሄም ከዚህም ቀደም መራጮች በጨርቅና በላስቲክ በተከለሉ ቦታዎች ድምጽ ሲሰጡ የነበረበትን ሂደት በማስቀረት መራጮች በነጻነት ፍላጎታቸው በድምጽ መስጫዎቹ እንዲያሳርፉ ያደርጋል።
በተጨማሪም በ50 ሺህ 900 የምርጫ ጣቢያዎች የሚገኙ የምርጫ አስፈጻሚዎች የሚጠቀሙባቸው ቁሳቁሶችም ወደ ሃገር ውስጥ ማስገባትም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባለፉት 5 ወራት ካከናውናቸው ስራዎች መካከል ይጠቀሳሉ ነው ያሉት።
ከቁሳቁስ ዝግጅት ባሻገርም ለመራጮች ትምህርት ለመስጠት ያመለከቱ 240 ሲቪክ ማህበራትን በምርጫ ህጉ በተቀመጠው መስፈርት የሲቪክ ማህበራት ሰነዶች ሲያጣራ ቆይቷል ብለዋል።
በዚህም መስፈርቱን የሚያሟሉ እውቅና እንዲያገኙ እና ሰነድ ያላሟሉ እንዲያሟሉ የማሳወቅ ስራ ተከውኗልም ነው ያሉት።
ወይዘሪት ሶሊያና አያይዘውም የቀሩ ስራዎች ኮቪድ 19 ታሳቢ በማድረግ ምርጫውን ለማስፈጸም አዲስ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየት ቦርዱ ይፋ እንደሚያደርግም ተናግረዋል ።
የሚዘጋጀው አዲስ የምርጫ ሰሌዳ ግን ቀሪ ሰራዎችን ብቻ ታሳቢ የሚያደርግ መሆኑን የኮሚኒኬሽን አማካሪዋ ገልፀዋል።
በበላይ ተስፋዬ / FBC
 • የቻይናው ሮኬት ስብርባሪ በኢትዮጵያ ቢወድቅ ምን ዓይነት የጥንቃቄ እርምጃዎች ሊወስዱ ይገባል?
  ከቁጥጥር ውጪ የሆነው የቻይና ሮኬት አካል ስብርባሪ በኢትዮጵያ ቢወድቅ ምን ዓይነት የጥንቃቄ እርምጃዎች ሊወስዱ ይገባል? ። የቻይናው 5 ቢ ሮኬት ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ወደ መሬት ለመምዘግዘግ ምድርን በመሽከርከር ላይ ይገኛል። 5 ቢ ሮኬት ከቁጥጥር ውጭ ከሆነበት ከሚያዝያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. እንስቶ በከፍተኛ ፍጥነት በመሬት ዙሪያ እየተሸከረከረ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ስፔስContinue Reading
 • ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መግለጫ
  ጠላቶቿ ፈርሰው ያልቃሉ እንጂ ኢትዮጵያ መቼም አትፈርስም፤ አዲስ አበባም ከሰላማዊ የብልፅግና ጉዞዋ አትስተጓጎልም! ሀገራችን ኢትዮጵያ በታሪኳ ለበርካታ ጊዜያት ከውጭ ጠላቶች ወረራ እና መሰል ጥቃቶች ተሰንዝሮባታል፤ ሁሉንም የውጪ ወረራ እና ጥቃቶችን በጀግኖች ልጆቿ በመመከት ጠላትን አሳፍራ መመለስ የቻለች ሲሆን በአንፃሩ ደግሞ ከአብራኳ የወጡ ከሃዲዎች እና ባንዳዎች ከውጭ ጠላት ጋር በማበር ሲያደሟትContinue Reading
 • አቡነ ማቲያስ መነጋገሪያ ሆነዋል – ኢትዮጵያ ላይ ዘመቻው እንዲከር ጥሪ አቅርበዋል
  ከትሀንግ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው መረጃ የተያዘባቸው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ሰፊ መነጋገሪያ ሆነዋል። በአዎንታና በአሉታዊ ጎን የተሰነዘረባቸው ተቃውሞ መነሻው ” ታፈንኩ” በማለት ሲናገሩ የሚያሳይ ቪዲዮ ወዳጆቻቸው ወይም የቅርብ ታዛዦቻቸው ካሰራጩና ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በኤፒ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ በቲውተር ገጻቸው ካሰራጩት በሁዋላ ነው። ቪዲዮውን ተከትሎ ሙስሊም የኢትዮጵያ ልጆች የአፍጢር ስነContinue Reading
 • Warshaan Keenyaa tiraaktaroota 950 qonnaan bultootaaf dabarse
  Magaalaa Shaashamanneetti kan argamu Warshaan Meeshaalee Qonnaa Ammayyaa Keenyaa kaleessa tiraaktaroota 950 qonnaan bultootaaf dabarse. Sirni walharkaa fuudhiinsaas qonnaan bultoota, dargaggoota waldaan gurmaa’aniifi dhaabbata Keenyaa gidduutti taasifameera. Sirnicharratti Pirezdaantiin Mootummaa Naannoo Oromiyaa, Obbo Shimallis Abdiisaa dabalatee hoggantoonni olaanoo federaalaafi naannolee, akkasumas abbootiin gadaa argamaniiru. Tiraaktaroota 950 qonnaan bultootaafi dargaggoota waldaanContinue Reading

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   "የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጀግኖች አርበኞች ነፃ ህክምና እንዲሰጥ ወሰነ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *