የማንም ፖለቲካ ፓርቲ መጠቀሚያ አይደለም ፣በየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲና አክቲቪስት ጫጫታ ከተልዕኮው አይደናቀፍም፤ ሰራዊቱ ጠንካራ ውስጣዊ አደረጃጀት አለው

ሰሞኑንን የትህነግ ሰዎች “ከመስከረም 25 በሁዋላ የመንግስት ህጋዊነት ያበቃል” የሚለውን መፈክር እየደጋገሙ እያሰሙ ነው። ከአንድ ወንበር በቀር ሙሉ በሙሉ አሸነፍን ማለታቸው በክልሉ ፖለቲካ ውስጥ እየፈጠረ ያለው ጉምጉምታ መጨረሻው ምን እንደሆነ ባይታወቅም ትህነግ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ላይ በማነጣጠር ” ተነስ ” የሚል መግለጫም ከትግራይ ነቅሎ በወጣው የፌደራሊስት ሃይሎች ጥምረት ስምም መግለጫ በማውጣት አሰራጭተዋል።

ዛቻና ማስፈራሪያ ያዘለው የትህነግ ሰዎች ማስጠንቀቂያ የመጨረሻ ግቡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን መገርሰስና ተመልሶ ወደ መሀል አገር ፖለቲካ መመለስ ነው። ይህ ይሳካ ዘንድ ትህነግ ሁሉንም አቅሙን እንደሚጠቀም፣ መሄድ ያለበት እርቀት ድረስ እንደሚነጉድ፣ መግባት አለበት ተራራና ጉድጓድ እንደሚገባ ፣ አድርገ የተባለውን ሁሉ ከማድረግ ወደሁዋላ እንደማይል በፋት ከመረጃ ጋር አስተያየት እየተሰጠ ነው።

በቅርቡ ውብሸት ታዬ “ከሕወሓት ተወካዮች አንዱ ከግብጽ የደህንነት አካላት ጋር ለመደራደር ከለንደን ካይሮ መግባቱን አስተማማኝ የመረጃ ምንጭ አረጋግጫለሁ” በሚል ሃሳብ በግል የፌስቡክ ገጹ ላይ እንዳሰፈረው ወደ ካይሮ ያመሩት የትህነግ ሰው ድርድር አድረገዋል።
“በድርድሩ ትህነግ 10 ቢሊዮን ዶላር እና ራሷን የቻለች አገር ለመሆን፥ የግብጽን ሁለንተናዊ ድጋፍ የጠየቀች ሲሆን ለዚህ በምላሹ ግብጽ በአባይ ላይ ላላት ፍላጎት አስፈላጊ የስልት ድጋፎችን ማድረግ እና በትግራይ ክልል ወታደራዊ ቀጠና መስጠት ተካተውበታል፤ የመረጃው ሙሉ ዝርዝር ከተደራዳሪዎቹ አንዱ በነበረና በመጨረሻው ሰዓት ‘አገራዊ ክህደት አልፈጽምም’ ባለ የትግራይ ተወላጅ የኢትዮጵያ ልጅ ለመንግሥት መድረሱ ሙሉ ለሙሉ ተረጋግጧል” ሲል አበይት ዜና ማስፈሩ ይታወሳል።

ይህ ዜና በታተመ ማግስት ዳንኤል ብርሃኔ ” ከመስከረም 25 በሁዋላ የሚሆነው አይታወቅም” ሲል ሊደረግ የታሰበ ሴራ እንዳለ የሚያመላክት ሃሳብ በፌስ ቡክ ገጹ አሰቀምጧል። ይህ ከሆነ በሁዋላ በአገሪቱ በተለያዩ አቅጣቻዎች በተለይም በደቡብና ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ እንዲሁም በምስራቅ የአገሪቱ ክፍል በተመሳሳይ ወቅት ጥቃት ለመሰንዘር እቅድ መነደፉን የአገሪቱ ደህንነትና ከነ ሙሉ እቀዱ እንደደረሰበት ተሰማ።

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

መስከረም 30 እና ሦስቱ ምስጢራዊው ዝግጅቶች

ከመስከረም 30 በኋላ ሕገመንግሥታዊ መሰረት ያለው መንግሥት አይኖርም ሲባል የቆየበት ጉዳይ ባዶ ምኞት ሳይሆን የመጨረሻ ዕድል ለመሞከር በተቀናጀ ሁኔታ እየተሠራ ያለበት ሁኔታ ስለመኖሩ የደረሱ አስተማማኝ መረጃዎች አረጋግጠዋል።
1ኛ፦ ለዚህ ሲባል በተመሳሳይ የንቅናቄ ዘመቻ ከሰሜን፤ ህወሓት ያዘጋጀችው ሃይል በአንድ በኩል፤ ደቡብና ምዕራባዊውን ቀጠና አማክሎ ሌሎች ሃይሎች ንቅናቄ እንዲያደርጉ እና የመንግሥትን ስልጣን በሃይል እንዲቆጣጠሩ፥
2ኛ:- እንቅፋት ሊሆኑ በሚችሉ ከፍተኛ አመራሮች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ
3ኛ:- መንግሥት የተቀናጀ ንቅናቄውን ለማክሸፍ ይገልገልባቸዋል የሚባሉ የግንኙነትና መሰል መዋቅሮችን ማፍረስ የሚሉ ናቸው።
በተያያዘ መረጃው የደረሰው የሚመለከተው የመንግሥት ክፍል በቂ ዝግጅት ስለማድረጉ የተጠቆመ ሲሆን ለ27 ዓመታት የዘለቀውን የጭቆና ሥርዓት ለመመለስ ማንኛውንም ድጋፍ ለማድረግ የሚሞክሩ ወገኖች የሕግ፣ የህሊናና የታሪክ ተጠያቂነት ስለሚኖርባቸው ጥንቃቄ እንዲያደርጉ፣ በቅርቡ የሁነት ማስገንዘቢያ መግለጫ እንደሚሰጥ ለማረጋገጥ ተችሏል።


በሚስጢር የተያዘው እቅድ መታወቁ ይፋ ሲሆንና መንግስትም ለጊዜው ይፋ ያላደረጋቸው እርምጃዎች መውሰድ ሲጀምር የቃላት ጨውታው ገኖና ገዝፎ እንዲወጣ ግድ ሆነ። በተለይም የአማራን ህዝብ በመነካካት ወደ ግጭት እንዲገባ የተሞከረው ሙከራ መክሸፉ ትህነግን ጦር እንዳስዋጣት ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ በአሽሙር መልክ እየገለጹ ነው።

ከመስከረም 25 በሁዋላ አሰልፈውት የነበረው ምስኪን ሚሊሻና ሃይል ወደ አራት ኪሎ ማዝገም ይጀመር አይጀምር ባይታወቅም መከላከያ ከወዲሁ ጥብቅ ማሳሰቢያ አሰራጭቷል። እንደሚከተለው ይነበባል

ህገ-መንግስቱን በጣሰ መልኩ በኃይል ፍላጎቴን አሳካለሁ በሚል ማንኛውም አካል ላይ እርምጃ ለመውሰድ እንገደዳለን ሲሉ በኢፌዴሪ መከላከያ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹምና የኦፕሬሽናል ጉዳዮች ኃላፊ ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ። የኢትዮጵያ የብር ኖት መቀየርን ተከትሎ ሰራዊቱ በህገ-ወጥ ገንዘብ ዝውውር ላይ ጠንካራ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

 ከዚህ ቀደም አገልግሎት ላይ ሲውል የነበረው የአብዮታዊ ሰራዊት መገንቢያ ሰነድ ሰራዊቱን ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነጻ እንዳላደረገው ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ አስታውሰዋል። ስለሆነም በአገራዊ ሪፎርሙ አዲስ የሰራዊት መገንቢያ ሰነድ አገልግሎት ላይ መዋሉን ጠቁመው÷አሁን ላይ ሰራዊቱ ያለ ምንም ፖለቲካ ወገንተኝነት ህዝብንና ሀገርን ህልውና እየጠበቀ ይገኛል ብለዋል። 

በመሆኑም ሰራዊቱ “የማንም ፖለቲካ ፓርቲ መጠቀሚያ አይደለም ፣በየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲና አክቲቪስት ጫጫታ ከተልዕኮው አይደናቀፍም ሲሉም ነው የተናገሩት። ሰራዊቱ ጠንካራ ውስጣዊ አደረጃጀት እንዳለው ጠቁመዋልከዚህ አንጻር ፖለቲከኞች በየትኛውም የፖለቲካ ቅስቀሳቸው ላይ የመከላከያ ሰራዊቱን የሚመለከት አጀንዳ ማራመድ የለባቸውም ብለዋል። በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተራዘመው አገራዊ ምርጫ አጠቃላይ ሂደት ህገ-መንግስቱን የተከተለ መሆኑንም ጀኔራል ብርሃኑ አብራርተዋል። 

በህገ መንግስቱ መሰረት ስልጣን የሚያዘው በምርጫ ብቻ እንጂ ‘ሽግግርና ባለአደራ’ በሚል ትርምስ አይደለም ሲሉም ነው የተናገሩት። ከዚህ አንጻር ከመስከረም 30 በኋላ መንግስት የለምና እንደፈለኩ እሆናለው የሚል አካሄድ ህገ-ወጥ መሆኑን ገልጸዋል።

 ህገ-መንግስቱን በጣሰ መልኩ ‘በሃይል ፍላጎቴን’ አሳካለሁ በሚል የትኛውም አካል ላይ ሰራዊቱ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድም ገልጸዋል። ጀኔራል ብርሃኑ አክለውም የኢትዮጵያ የብር ኖት መቀየርን ተከትሎ ሰራዊቱ በህገ-ወጥ ገንዘቦች ወደ ሀገር እንዳይገቡ ጠንካራ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል። ነገር ግን ሰራዊቱ ህገ-ወጥ በሚል ሰበብ ገንዘብ እየነጠቀ እንዲወስድ ፈቃድ ተሰጥቶታል በሚል የሃሰት ፕሮፓጋንዳ የሚነዙ አካላት እንዳሉም ነው የገለጹት። 

ሰራዊቱ ከተገነባበት እሴት ይህን እንዲያደርግ ፈጽሞ አይፈቅድለትም ብለዋል። በህገ-ወጥ መልኩ ሲዘዋዋር የተያዘ ገንዘብ በአንድ ቋት ተሰብስቦ የጸጥታ መዋቅሩን ለማጠናከር እንደሚውል በማብራራት። ሆነ ብለው በተደራጀ መልኩ የሀገር ኩራት የሆነውን የመከላከያ ሰራዊት ስም ጥላሸት የሚቀቡ አካላት እንዳሉም ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም ከውስጥ ምንጭ አገኘነው በሚል ሰበብ የመከላከያ ሰራዊት ስም የሚያጠፉ ጽሁፎችን ያሳተሙ ግለሰቦች መኖራቸውን ለአብነት አንስተዋል። 

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

ድርጊቱ ከባድ ወንጀል ቢሆንም በትዕግስት መታለፉን ጠቅሰው፤ ከዚህ በኋላ በመሰል ተግባር የሚሳተፉ ማናቸውንም አይነት ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠንቀቀዋል። ሰራዊቱ በአሁን ወቅት ማናቸውንም አይነት ተልዕኮዎችን በብቃት ማከናወን በሚያስችል ሙሉ ቀመና ላይ መሆኑንም ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ብርሃኑ ጁላ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *