የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በተፈጸሙ ወንጀሎች ዙሪያ በኦሮሚያ ክልል ሲካሄድ የነበረው ምርመራ መጠናቀቁን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ። ይህንኑ አመልከቶ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ እና ኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጉዳዩን አስመልክተው በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫው ምክትል አቃቤ ህጉ አቶ ፍቃዱ ጸጋ ባለፉት ወራት በኦሮሚያ ክልል በተካሄደው የምርመራ ሂደት ውስጥ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ፣ ከፌደራል ፖሊስ፣ከኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ እና የኦሮሚያ ፖሊስ ጋር በጋራ ሲሰራ መቆየቱን አስታውቀዋል።
በዚህም በ488 የክስ መዝገብ 5 ሺህ 728 ግለሰቦች ላይ ክስ ተመስርቶባችዋል ነው ያሉት።
በዚህም 3 ሺህ 377 ተከሳሾች በፌደራል መንግስት ስልጣን ስር የሚወድቅ ወንጀል በመፈጸማቸው ተጠያቂነታቸው በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሲሆን፤2 ሺህ 351 ተከሳሾች ደግሞ በኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ስር ይሆናል ተብሏል።
ከተጠርጣሪዎች ብዛት፣ ከወንጀሉ ስፋት እና ወንጀሉ ከተፈጸመበት ቦታ ስፋት አኳያ ምርመራው ጊዜ እንደወሰደ ነው የፌደራል ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ህጉ አቶ ፍቃዱ ጸጋ የተናገሩት።
በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ተከሳሾች በ114 የክስ መዛግብት ክሳቸው መደራጀቱም ነው የተገለፀው፡፡
በኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ደግሞ በ374 የክስ መዛግብት ክሳቸው ተደራጅቷል።
ከእነዚህ ውስጥ 63 ግለሰቦች በሀረር በፈረሱ ሃውልቶች ምክንያት በሽብር ህጉ መሰረት ተጠያቂ የሚሆኑ ናቸው ተብሏል።
ከአርቲስት ሃጫሉ ግድያ በኋላ በኦሮሚያ በተከሰተው ሁከት 167 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን 360 ሰዎች የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው እና ከ4 ቢሊየን 673 ሚሊየን ብር በላይ የንብረት ጉዳት መድረሱን በምርመራ እንደተጣራ በመግለጫው ተነስቷል።
የፌደራል ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ህጉ አቶ ፍቃዱ ጸጋ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህጉ አቶ ሁሴን ኡስማን በጋራ መግለጫቸው ፍርድ ቤቶች የፍርድ ሂደቱን ለማየት በሚያስችል መንገድ ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን እና የህግ የበላይነትን የማስከበሩ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
በምስክር ስናፍቅ – ፋና
- “የትኅትና ገመድ የመጨረሻዋ ቋጠሮ ብርቱ ክንድ ናት፤ ከተሠነዘረች ሳታደቅቅ አትመለስም”“የትኅትና ገመድ የመጨረሻዋ ቋጠሮ ብርቱ ክንድ ናት። ከተሠነዘረች ሳታደቅቅ አትመለስም” ሲሉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ገለጹ። ጠቅላይ ሚንስትርሩ ይህን ያሉት ለጥምቀትና ከተራ በዓል እንኳንContinue Reading
- Ethiopia: What’s Next After Tigray?n early 2018, amidst incessant protests especially in Ethiopia’s Oromo and Amhara regions, Abiy Ahmed Ali became the new prime minister of Ethiopia. His ascentContinue Reading
- “ አንገት ቆረጣ ” የ – ሰለጠነው የ- እርስ በርስ መበላላት!ሃኪሙ የተረኛ ስም ጠራ፤ አስናቀ “ አቤት” ብሎ ከተቀመጠበት ተነሳ፡፡ ሃኪሙ አስናቀን በምልክት “ የት አለ” ሲል ጠየቀው፡፡ አስናቀ መዘናጋቱን አስታወቆ የተጠየቀውን ሊያመጣ ላፍታ ወደContinue Reading
- Death toll from violence in Sudan’s West Darfur risesCAIRO (AP) – The death toll from tribal violence between Arabs and non-Arabs in Sudan’s West Darfur province climbed to at least 83, including womenContinue Reading