የፌዴራል ፖሊስ ጥብቅ ፍተሻ እያደረገ ያለው ከአማራ ክልል በሚመጡ መንገደኞች ብቻ ሳይሆን ወደ መዲናዋ በሚያስገቡ በሁሉም በሮች ላይ ተመሳሳይ የቁጥጥር ስራ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል እንደሻው ጣሰው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በአልን ምክኒያት በማድረግ በአዲስ አበባ የሽብር ድርጊት ለመፈጸም እና ይህንኑ ተከትሎ ሁከት እና ግጭት እንዲፈጠር በዝግጅት ላይ የሚገኙ አካላት እንዳሉ ደርሰንበታል ያሉት ኮሚሽነር ጄኔራሉ መረጃውን መሰረት በማድረግ ወደ አዲስ አበባ በሚያስገቡ በሁሉም በሮች ላይ ጥብቅ ፍተሻ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል ።

የበዓሉን እንቅስቃሴ ለማደፍረስ ዕቅድ ያላቸው ሀይሎች እንዳሉ ፖሊስ በምርመራ እንደደረሰበት ጠቁመው፤ እነዚህ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቀቆጠቡ አሳስበዋል።

Related stories   የአምነስቲ " ሽንቁረ ብዙ" ሪፖርት የተከፋዮች የቲውተር ዜና ድምር

ከመስከረም 25 በኋላ መንግስት አይኖርም በሚል የተለያዩ እንስቃሴዎች የሚያደርጉ አካላት እንዳሉ ገልጸው የህዝቡን ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል።

በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ወደ አዲስ አበባ መግቢያ በሮች በሱልልታ፣ ለገጣፎ፣ ቡራዩ፣ ገላንና ሰበታ ፍተሻ እየተደረገ እንደሆነም ኮሚሽነር እንዳሻው ጣሰው ተናግረዋል።

አላስፈላጊ እንቅስቃሴዎችን ለመግታት ፖሊስ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን ገልጸው፤ በበዓሉ ለመታደም የሚመጡ ምዕምናንና እንግዶችም ትክክልኛውን የይለፍ ባጅ ማድርጋቸውን ማረጋገጥ እንዳለባቸው ተናግረዋል። ይህን ተላልፎ በሚገኝ ማንኛውንም አካል አይታገስም ፤ ፖሊስ እርምጃ ይወስዳልም ብለዋል።

ፖሊስ ከኅብረተሰብ ጋር በትብብር እየሰራ ነው ያሉት ሀላፊው፤ ህብረተሰቡ ለየት ያለ እንቅስቃሴ ሲመለከት የተለመደ ትብብርንና ጥቆማውን ለፖሊስ እንዲሰጥ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Related stories   በእነ ጃዋር የህክምና ጥያቄ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሁሉንም ተከራካሪዎች ጥያቄ ውድቅ አደረገ፤ ቃሊቲ ሆነው ይታከማሉ፤

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *