Share and Enjoy !

Shares

ዛሬ በኦሮሚያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡት አቶ ልደቱ አያሌው አቃቤ ህግ ላቀረበባቸው የዋስትና ክልከላ ውሳኔ ለመስጠት ለመስከረም 26 ቀን 2013 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ድህንነት ያስታጠቃቸው መሳሪያ ዋስትና እንደማያስከለክላቸው ገልጸዋል።

አቶ ልደቱ የተቃዋሚ ፖለቲካ አመራር ሆነው ከትህነግ ጋር በሚስጢር ይሰራሉ በሚል ይቅርብባቸው ስለነበር በድንገት ታስረው መንግስት እንዳስታጠቃቸው በራሳቸው አንደበት መናገራቸው ከእስሩ በላይ ከፍተኛ መነጋገሪያ መሆኑ ይታወሳል። 

በ1997 ቅንጅት ያገኘው ድምጽ ተወስዶ፣ ፓርቲው እንዲበተን ታላቁን ሚና ተጫውተዋል በሚል ጥርስ ውስጥ የገቡት አቶ ልደቱ፣ በዛው ወቅት ለድህንነታቸው መጠበቂያ የሚቃወሙት ድርጅት እንዴትና በምን ሂሳብ ሊያስታጥቃቸው እንደቻለ ከእስር ሲወጡ ምናልባትም ወደ ፖለቲካው መድረክ የሚመለሱ ከሆነ አስቀድመው የሚያስተባብሉት ጉዳይ እንደሚሆን ይጠበቃል። አብዛኞች እንደሚሉት ከሆነ ግን አቶ ልደቱ ትንሽም ቢሆን አንሰራርቶ የነበረው ተሳትፏቸው ዳግም ሊያንሰራራ እንደማይችል በተደጋጋሚ አስተያየት ሲሰጡ ተሰምቷል። የዛሪውን የፍርድ ቤት ውሎ ኢትዮ ኤፍ ኤም እንደሚከተለው ዘግቦታል።

የምስራቅ ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ ልደቱ አያሌው በመቶ ሺ ብር ዋስ ከእስር እዲፈቱ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ታግዶ ለዛሬ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ትዕዛዝ መስጠቱ የሚታወስ ነው፡፡

Related stories   የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነ እስክንድር ነጋ ጉዳይ የተፋጠነ ፍትሕ መስጠት እንዲቻል ከቀጠሮ ቀን በፊት ችሎት ሰየመ

ዛሬ የኦሮሚያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡት አቶ ልደቱ አያሌው አቃቢ ህግ የተሰጣቸው ዋስትና ሊከለከል ይገባል ያለበትን አራት ምክንያቶች አቅርቧል፡፡

ቀዳሚው አቶ ልደቱ ቢለቀቁ ምስክሮችን ያስፈራሩብኛል የሚል ሲሆን ሁለተኛው የተገኘባቸው መሳሪያ ህገወጥ ስለሆነ
ዋስትና ሊሰጣቸው አይገባም ፡፡

በሶስተኝነት ደግሞ አቶ ልደቱ የህክምና ቀጠሮ ያላቸው በአሜሪካ ስለሆነ ውጪ ቢሄዱ በዛው ይቀሩብኛል የሚል ነው፡፡

አራተኛው የአቶ ልደቱ ፓርቲ ደጋፊዎች በምስክሮቼ ላይ ተጽዕኖ ያሳርፉብኛል የሚል መሆናቸውን የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አዳነ ታደሰ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስረድተዋል፡፡

ለዚህ አቃቤ ህግ ላቀረበው አቤቱታም አቶ ልደቱ እስካሁን ከአስር ጊዜ በላይ ፍር ቤት ቀርቤያለሁ፤ በቀረብኩባቸው ጊዜያት ሁሉ በነጻ ብለቀቅም ዋስትና ቢሰጠኝም ፖሊስ እኔን ለመልቀቅ ፈቃደኛ አይደለም፡፡ በዚሁ መንገድ ከሁለት ወር በላይ ሆኖኛል፡፡

ይሄ የሚያሳየው አቃቤ ህግ በእኔ ላይ ወንጀል አግኝቶ ሳይሆን እየከሰሰኝ ያለው የተለያዩ ቀጠሮዎችን በማራዘም ፣ ይግባኝ በመጠየቅ እና በማስከልከል እስር ቤት እንድቆይና በእስር ቤት ውስጥ ህይወቴ እንዲያልፍ ነው የሚፈልገው፡፡

ከዚህ አንጻር የሚያነሳቸው መከራከሪያዎችም ተገቢነት የላቸውም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡
የመጀመሪያው ምስክሮች ቤቴ ሲፈተሸ በአካል ቀርበው የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡

Related stories   ስብሃት ጨምሮ ፍርድ ቤት የቀረቡ ተጠርጣሪዎች " ጥፋተኛ አይደለንም፣ መከላከያ ሰራዊት ዋሻ ውስጥ ተደብቀን ያዘን" አሉ

የተገኘውን መሳሪያ በእኔ እጅ እንዳለ አልካድኩም፡፡ ለፍርድ ቤቱም ማረጋገጫ የሰጠሁት እኔ ራሴ ነኝ፡፡ ከመንግስት የተቀበልኩት መሳሪያ መሆኑን አስረድቼያለሁ፡፡

በሁለተኛ ደረጃም ውጪ ሄጄ መታከም እንዳለብኝ ለፍርድ ቤቱ የተናገርኩት እኔ ነኝ፡፡ ይህንን አቃቤ ህግ እንደ አዲስ ያገኘው አይደለም፡፡ እኔ ራሴ ነኝ የተናገርኩት ሲሉ ውድቅ አድርገውታል፡፡

ሶስተኛው በፓርቲ ደጋፊዎች ማስፈራሪያ ያደርሳል የሚለው ህጋዊ ፓርቲ በመሆኑ ደጋፊዎቹም ሰላማዊ ናቸው፡፡ እንዲህ ዓይነት ህገ ወጥ ስራን አንሰራም፡፡

በመጨረሻም ህገወጥ መሳሪያ በቤቱ ተገኘ የሚባለው ፈጽሞ ተገቢ አይደለም ሲሉ አቶ ልደቱ ተከራክረዋል፡፡ አሁን እየተደረገ ያለው መንግስት ራሱ ባስታጠቀኝ መሳሪያ ራሱ እየከሰሰኝ ነው፡፡ ይህ በማስረጃ የተረጋገጠ ነው፡፡ ከመንግስት እደተቀበልኩኝ ማስረጃ አቅርቤ ውድቅ ተደርጎብኛል፡፡ ህገወጥነው የሚያስብል ምንም ነገር የለም ብለዋል፡፡

በመጨረሻም የሁለቱን ወገን ክርክር ያደመጠው ፍርድ ቤት ለመስከረም 26 ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ላይ ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ሰጥቷል፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *