አፍሪካ በየዓመቱ ከምታገኘው የእርዳታ ገንዘብ በላይ እንደምትመዘበር የተባበሩት መንግስታት ጥናትን ጠቅሶ አልጀዚራ ገለጸ። በጥናቱ መሰረት አፍሪካ ከምሲኪን ህዝቦቿ ጉሮሮ በየዓመቱ ከ89 ቢሊዮን ዶላር በላይ በራሷ ልጆች ትመዘበራለች።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥናት እንዳመለክተው  አፍሪካ ይህን ያህል ሃብት የምትመዘበረው በግብር ማጭበርበርና ስርቆት ነው። በዚሁም 89 ቢሊየን የሚጠጋ ዶላር በምትመዘበረው አፍሪካ ዝርፊያው ከዓመት ዓመት እየጨመረ ነው።

አፍሪካ ከምትመዘበረው መጠኑ ከፍተኛ የሆነ ሃብት ውስጥ ግማሹ ስርቆት የሚከናወነው በከበሩ ማእድናት ወርቅ፣ አልማዝና ፕላቲኒየም ሲሆን ትርፍን በመሸሸግና ህገወጥ ንግድ በማስፋፋት በሚደረግ የግብር ስወራ በጥቅሉ አፍሪካ የምትከስረው ሃብት በየዓመቱ ከውጭ አገራት ለልማት ከምትቀበለው እርዳታ እንደሚበልጥ አልጀዚራ ጥናቱን ጠቅሶ ዘግቧል።

ተመድ ይፋ ያደረገው ባለ 248 ገጽ ሪፖርት የግብር ማጭበርበሩና ዝርፊያው አስቀድሞ ከተገመተውና ከተተነበየው እጅግ እንደሚልቅ አመልክቷል። ዝርፊያው የታዳጊ አገራቱን የውጭ ምንዛሬ ክምችት የሚፈታተንና አሉታዊ ታጽዕኖ የሚያሳድር ሆኗል።

የተመድ የንግድና የልማት ጉዳዮች ሴክሬታሪ ጀነራል ሙክሂሳ ኪትዪ” ህገወጥ ዝርፊያውና የፋይናንስ ስርዓቱ አፍሪካውያንን እየበዘበዘ ነው” ማለታቸውን አልጃዚራ አስነብቧል። ሙክሂሳ አያይዘውም በአህጉሪቷ የሚገኙ ተቋማትን እምነት እንደሚያሳጣ እንዲሁም ግልጽነትና ተጠያቂነት ላይ ጥላ እንደሚያጠላበት አመልክተዋል።

በተቋሙ የአፍሪካ ጉዳዮች የፖሊሲና የምርምር ባለሙያ የሆኑት ጁኒየር ዳቪስ ሪፖርቱ መረጃ ካማጣቀስ አንጻር ውስንነቶች እንዳሉበትም ገልጸዋል፡፡

Related stories   ዶክተር አብራሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ!

ኢትዮጵያ በድድርና እርዳታ ካገነችው፣ እንዲሁም ካላት መጠነኛ የውጭ ንግድ የውጪ ምንዛሬ ገቢዋ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ሃብት መዘረፏን በተከታታይ ሲዘገብ ነበር። በነጮቹ አቆጣጠር  ከ2000 እስከ 2009 ባለው የ9 ዓመት ዕድሜ ውስጥ ብቻ  ከ 11 ቢሊዮን 700 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ በህገወጥ መንገድ ከአገር እንዲሸሽ ተደርጎ ሌቦቹ በውጪ አገር ባንኮች በግል ሂሳባቸው እንዳከማቹ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት መርሀግብር ሥር ጥናት ያካሄደው “ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ” የተባለው አለማቀፍ ተቋም ባወጣው ባወጣው ሪፖርት ማጋለጡ አይዘነጋም።

ጥናቱን ባካሄደው ተቋም መረጃ መሠረት፦ በስርቆት፣ በሙስናና በተለያዩ ህገወጥ መንገዶች የተገኘ ነው የተባለው ይህ ትልቅ መጠን ያለው ገንዘብ፤ መለስ ዜናዊ በተገኘበት ዓለም አቀፍ መድረክ ሪፕርቱ ከመውጣቱ 6 ወር በፊት ይፋ ከሆነው 8 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ጋር ሲነፃፀር በ3 ነጥብ 26 ቢሊዮን ብልጫ አለው። ይህ3 ቢሊዮን 260 ሚሊዮን ዶላር በአንድ ዓመት ጊዜ ማለትም የቀድሞው ሪፖርት ባልሸፈነው የ2009 ዓም ብቻ የተዘረፈ መሆኑ ጥናት አድራጊውን ተቋም ያስገረመ ነው።

ከ2009 በሁዋላ በተለያዩ መልኩ በሚወጡ ሪፖርቶችና መረጃዎች ጋር ሲደመር አገሪቱ በጥቅሉ ከ 23 ቢልዮን በላይ የውጭ ምንዛሬ መዘረፏ ይጠቀሳል። መንግስታዊ ተቋማት ይህንን ሪፖርት በይፋ አምነው ባያረጋግጡትም ዝርፊያው ስለመፈጸሙ ግን በገሃድ በተደጋጋሚ፣ በተለያዩ መድረኮች እየተገለጸ ነው። ዘረፉ የተባሉት ወገኖችም የሚያስተባብሉት ጉዳይ አይደለም።

Related stories   የኮሚሽነር አበረ ህልፈት "በነጋዴዎች" እይታና ፤ የሃኪም ትክክለኛው መረጃ " ቸልተኛነት አይተናል"

መንግስት ይህ ከአገር ሸሸ የተባለው ገንዘብ ያለበትን አድራሻ ከወዳጅ አገሮች ጋር በመሆን የደረሰበት እንደሆነና ገንዘቡን ለማስመለስ ውስጥ ውስጡን እየሰራ መሆኑንን አቃቤ ህግ በቅርቡ መናገሩ ይታወሳል።

 • “ዶክተር ነኝ” በማለት ሲያጭበረብር የተገኘ ግለሰብ በእስራትና በገንዘብ ተቀጣ
  የጎባ ወረዳ ፍርድ ቤት በጎባ ሪፈራል ሆስፒታል “የህክምና ዶክተር ነኝ” በማለት በተደጋጋሚ ህብረተሰቡ ላይ የማጭበርበር ወንጀል ፈጽሟል ያለውን ግለሰብ በ6 ዓመት ከ6 ወር እስራትና በገንዘብ ቀጣ። ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት የቅጣት ውሳኔውን ያሳለፈው በጎባ ከተማ ኦዳ በሃ ቀበሌ ነዋሪ በሆነው አብዱልጀዋድ አማን ላይ ነው። ግለሰቡ በተደጋጋሚ በጎባ ሪፈራል ሆስፒታልContinue Reading
 • የፍትህ ያለህ የሚሉት የ87 ዓመት አረጋዊቷ እሮሮ
  <<ጉልበቴ እንደዛሬው ሳይደክም በ1976 ዓ.ም የሰራሁትን መጸዳጃ ቤት በተንሻፈፈ ፍርድ አፍርሽ ተብዬ ተወስኖብኝ የፍትህ ያለህ! ፍትህ ተዛብቶብኛል የሚሉት ገርበ ጉራቻ ከተማ ነዋሪ የ87 ዓመት አዛውንቷ ወይዘሮ እናኑ ክብረት ናቸው፡፡ ሰሚ አጥቼ እያለቀስሁ እገኛለሁና ህዝብና መንግስት ይፍረደኝ>> ሲሉ ለዝግጅት ክፍላችን አቤቱታቸው አቅርበዋል። በገርበ ጉራቻ ከተማ ተወልደው እንዳደጉ የሚናገሩት ወይዘሮ እናኑ ክብረት፤Continue Reading
 • ሕወሃት 7 ቢሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ ለወንጀል መፈጸሚያነት ማዋል እንዳይችልና እንዳያሸሽ ተደረገ
  ህገ ወጥ ቡድኑ ብር 6,762,942,319 (ስድስት ቢሊየን ሰባት መቶ ስልሳ ሁለት ሚሊዬን ዘጠኝ መቶ አራባ ሁለት ሺ ሦስት መቶ አስራ ዘጠኝ ብር) የሆነን ገንዘብ ለወንጀል መፈጸሚያነት ማዋል እንዳይችልና በሕገ-ወጥ መንገድ እንዳያሸሽ (እንዳይሰዉር) መከላከል መቻሉ ተገለጸ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕወሃት ሕገ-ወጥ ቡድን ታሳስ 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሰሜን ዕዝ ላይContinue Reading
 • የወንጀል ተካፋይ የሆነን ሰው ምስክር አድርጎ ከክስ ነፃ ስለማድረግ
  1. ከክስ ነፃ የማድረግ ምንነትና አይነት ከክስ ነፃ ማድረግ ማለት ከቃሉ መረዳት እንደሚቻለው በህግ ከሚጣል ግዴታ፣ ከመከሰስ ወይም ከቅጣት ነፃ ለማድረግ የሚወሰን ውሳኔ ነው፡፡ ከክስ ነፃ ማድረግ የተለያየ አይነት ያለው ሲሆን ምስክርን ከክስ ነፃ ማድረግ፣ ለህዝብ ጥቅም ሲባል የመንግስት ሀላፊዎችን ከክስ ነፃ ማድረግ፣ የሉዓላዊነት ነፃነት እና የዲፕሎማሲ ነፃነት ሊሆን ይችላል፡፡Continue Reading

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *