Share and Enjoy !

Shares

” ሃያ አራትና ሰባት 24/7 ” አሉ ሜጄር ጄነራል ይልማ መርዳሳ ሃይሉ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ዋና አዛዥ፣ እጅግ በሆነ የራስ መተማመን እና እርጋታ ኮዱን ሲያብራሩ ” ሃያ አራት ሰዓት እና ሰባት ቀን” መሆኑንን አስረዱ። አየር ሃይል ሃያ አራት ሰዓት በቀን፣ በሳምንት ሰባቱንም ቀን ሳይተኛ አገሩን ከጠላት እንደሚጠብቅ ለማረጋገጥ የሚጠቀሙበት መሃላ ነው።

አውቆም ይሁን ሳያውቅ የኢትዮጵያን ክልል የሚያልፍ አካል ፈቃድ እስካላገኘ ድርስ የማይታሰብ መሆኑንን ያስረዱት ጀነራሉ፣ የኢትዮጵያ አየር ሃይል በላቀ ቴክኖሎጂ ከመዘመኑ በላይ የታተቀውን ዘመናዊ መሳሪያ መጠቀም የሚያስችለውን እውቀት በብቃት የተላበሰና ሙሉ በሙሉ ዲጂታል መሆኑንን አስረደትዋል።

በኢትዮጵያ ቲሊቪዥን በኩል ቀርበው ለሕዝብ መረጃ የሰጡት የአየር ሃይል አዛዥ እንዳሉት፣ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ጥቃት ለማድረስ የሚያስቡትን የሚያስቀረት፣ ቀደም ሲል ባልነበረ ሁኔታ ዛሬ ላይ ያለማቋረጥ ከአራት ሰአት በላይ አየር ላይ በግዳጅ ስራ የሚቆይ ተዋጊ ጀት ባለቤት ሆኗል። ከፍተኛ ቴክኖሎጂ ያረፈባቸው ተዋጊ ሄሊኮፕተሮች ታጥቋል።

” እንኳን አውሮፕላን፣ እኛ ካልፈቀድን ወፍ እንኳን አይበርም” ሲሉ በሙላት ያስታወቁት ጀነራሉ ይህ እመርታ የታየው ከለውጡ በሁዋላ የኢትዮጵያን አየር ሃይል ለማዘመን በተወሰደ እርምጃና ኢንቨስትመንት ነው።

Related stories   በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከሃሰተኛ መረጃ ራሳቸውን እንዲጠብቁ ጥሪ ቀረበ፣ የተጭበረበረ መረጃ ተሰራጭቶ ነበር

የታላቁን የህዳሴ ግድብ አስመልክቶ ሲናገሩ ” ለአፍታም ከአይናችን ብሌን ለይተን ካማናወጣቸው የኢትዮጵያ ልዩ ስፋርዎች አንዱ ነው” ካሉ በሁዋላ የህዳሴ ግድብ ክልል የአየር ላይ ማዕቀብ መደረጉን አውስተዋል። አይዘውም ይህንን አልፎ የሚመጣ አካል ካለ አየር ሃይላችን በግድቡ ክልል ሳይጠጋ ዋጋውን እንደሚሰጠው፣ ይህንን የማድረግ ሙሉ አቅም መፈጠሩንና ዜጎች ሃሳብ እንዳይገባቸው አስረግጠው ተናግረዋል።

እየሳቁ በሙሉ መረጋጋት ውስጥ ሆነው የሚናገሩት ጀነራሉ ” በአጭር ጊዜ ውስጥ የፈለገውን ሚሽን / ግዳጅ የሚተገብር” ሲሉ ነው የኢትዮጵያን አየር ሃይል የገለጹት።

እጅግ ዘመናዊ የሚባል ራዳር መተከሉን በደፈናው ቦታ ሳይገልጹ ጀነራሉ ተናግረዋል። ራዳሩ የትኛውም አካል የኢትዮጵያን ክልል በአራት መቶ ሜትር ዘልቆ ሲገባ የሚያስታውቅ፣ ከዲጂታል የመከላከያ መሳሪያዎች ጋር ተናቦ እንደአስፈላጊነቱ ምላሽ እንዲሰጥ በሰኮንድ ጊዜ ውስጥ የሚሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

ኦፕሬሽኑ በጥብቅ ቁጥጥር ስር የሚሰራና ማንኛውም አካል ስህተት ሊሰራበት በማይችልና ጠላት እጁን ሊያስገባበት በማይችልበት መልኩ የተደራጀ መሆኑንን ጀነራሉ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ አስታውቀዋል። አያይዘውም ባህር ዳርና ደብረዘይት የአየር ሃይል ማዘዣዎች ኦፕሬሽን የሚካሄደባቸው መሆኑን በይፋ ገልጸዋል። ይህንን ያሉት በምን መነሻ እንደሆነ ግን አላብራሩም።

Related stories   " አሜሪካ ስለ ዴሞክራሲ፣ ጸጥታና ደህንነት የማውራት ሞራል የላትም፤ የአገራችን ሚዲያዎች ያሳዝናል"

የኢትዮጵያ አየር ወለድ ኮማንዶ በአዲስ ተደራጅቶ በሽህ የሚቆጠሩ አባላቶቹን በፈረንሳይ ባለሙያዎች አሰልጥኖ ካስመረቀ በሁዋላ ሚጀር ጄነራል ይልማ መርዳሳ ይህንን መግለጫ መስጠታቸው ምን አልባትም ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እየፎከሩ ላሉ የውስጥና የውጭ ሃይሎች ማስጠንቀቂያ ሊሆን እንደሚችል አስተያየት ተሰጥቷል።

የኢትዮጵያ መንግስት ዘመናዊ የጦር ጀቶች፣ ሚሳኤሎች፣ ራዳርና ተዋጊ ሂሊኮፕተሮች ከፈረንሳይ መግዛቱን የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ከስምምነቱ ጀምሮ መዘገባቸው አይዘነጋም። ከሩሲያ እጅግ ዘመናዊ የአየር መቃወሚያ መጋዛቱ ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ስልጣን ከመጡ በሁዋላ ወደ ፈረንሳይ በመሄድ ይህንን ስምስምነት ማጽናታቸው፣ የአየር ወለድና የባህር ሃይል ተመልሶ እንዲቋቋም ማድረጋቸው፣ ለዚህም ፈረንሳይ ከሽያጭ ውል ውጪ በርካታ ሙያዊና የቴክኒክ ድጋፍ ማድረጓ የአገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘግበው ነበር።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *