Share and Enjoy !

Shares

ዛሬ የኔታ ማለፋቸውን ሰማን። የዘመኑንን በሽታ ” አድር ባይነትን” አብዝተው በተግባር ሲያኮስሱ የኖሩት መስፋን ለተፈጥሮ መርህ ሲባል ” አለፉ” ይባል እንጂ አሉ። እስኪወሰዱ ብዕራቸው ያልዶለዶመ፣ አረጀሁ፣ ደከምኩ፣ ታመምኩ ብለው እጅ ሳይሰጡ ሃሳብ ሲዘሩ የኖሩ፣ ከሁለት ሳምንት በፌት መጣፍ ያሳተሙ የአገር ምሶሶ እንዴት ሞቱ ይባላል?

በመጥሃፍ አጥገበው፣ የሰው ልጅን ቀርጠው፣ እውነት መናገርን አስተምረው፣ ስደትን ረግመው፣ በተፈጠሩበት ምድር ግናባራቸውን ሰጥተው፣ እስኪሄዱ ባትለው የኖሩ  ብሩህ ሰው የኔታ !! እረፍትዎን ሰምቶ የትኛው ልጅዎ ይነሳ ይሆን? ማን አድርባይነትን ፈንቅሎ ይወጣ ይሆን? ዘርዎ ፍሬዋን ታፍራ፤ ባስቀመጡልን ሁሉ ልጅ ልጆቻችን ያስቡዎታል።

የኔታ ከዛሬ ሁለት ሳምንት በፊት አዲስ መጣፍ አሳትመዋል። በ91 ዓመት እድሜ ይህን ያደረገ ማን ነው? አብሪው ኮከብ አልሞትክም፤ አለህ፤ ትኖራለህ፤ ትዘከራለህ፤ ምክንያቱም ህያው ስራህ ምስክር ነዋ! ስለ የኔታ የተለያዩ አስተያየቶች እየጎረፉ ነው

ኢትዮጵያዊነት ከጎሰኝነት በላይና ውጭ የሆነ አጠቃላይ ማንነት ነው :: ኢትዮጵያዊነት የደጋው ብርድና የቆላው ሙቀት የሚገናኙበት የደጋው ዝናብ ከቆላው ወንዝ ጋር የተዛመደበት ሃይል ነው :: ኢትዮጵያዊነት ለሙሴ* ለክርስቶስና ለመሀመድ የሚጨሰው እጣን በእርገት መጥቆ የሚደባለቅበት እምነት ነው :: ኢትዮጵያዊነት በቄጤማ ጉዝጏዝ ላይ የሚታየው መተሳሰብና መፈቃቀር ነው :: ኢትዮጵያዊነት የአስተዋይነት ፣ የሚዛናዊነትና የጨዋነት ባህርይ ነው ~ ረጅምና ተጽፎ ያላለቀም ታሪክ ነው ” የወርቃማ ሀሳቦች ባለቤት የሆኑትን ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም ነፍስ ይማር ! ከተናገሩት ብሎ  ዓለማየሁ ገብየሁ ከከተበው
“ከትንንሽ አስተሳሰብ ደጅ የማይቆሙት፣ ትልቅ ትልቁን ብቻ የሚመለከቱት እና መቼም ቢሆን ኢትዮጵያን ከፊት የሚያስቀድሙት፣ የምሁር አንጓው ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ ማርያም ስማቸውን ትተው እስከወዲያኛው አሸለቡ! ነብስ ይማር!!” አቶ ብርሃኑ አሰፋ
Eyob Aleneበዘመናት የተገለጠ የኢትዮጵያዊ ጥልቅ እውቀት: ጀግንነት : ሰላማዊነት: ፍትሀዊነት: እና ሩህሩህነት ምልክታችንን ዛሬ አጥተናል:: የኔታ እድሜዎን ሙሉ የጮሁላት የኢትዮጵያ: የተሟገቱላቸው የድሆች እና : ግንባርዎን ያላጠፉለት የፍትህ አምላክ ነፍስዎን ያሳርፍልን::

መስከረም 20፤ 2013 ዓም የትውልድ ዋርካ፤ የዘመናት ዕንቁ የሆኑትን የኔታ መስፍን ወልደ ማርያም ማረፋቸው ተሰምቷል። ስለ እርሳቸው ብዙ ማለት ይቻላል። ሞት ለማንም የማይቀር ቢሆንም ስለ እርሳቸው ዕረፍት እኛ ከምንናገረው በላይ ራሳቸው ስለ ሞት የተናገሩትን አትመነዋል። ከሁሉ በላይ “ዛሬም እንደ ትናንት” የተሰኘውን የመጨረሻ መጽሐፋቸውን ከሁለት ሳምንታት በፊት አሳትመው ማረፋቸው ለአገራቸው እስከመጨረሻው የተጉ የዘመናችን ዕንቁ! የኔታ መስፍን! የቅኔ ጌታ! የዕውቀት ገበታ! ቢባልላቸው በፍጹም የሚያንስባቸው አይደለም።  ጎልጉል የድረገ ገጽ ጋዜጣ

የሰላም እረፍት ይሁንልዎ መስፍን !
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ሞትን በቀደመ ግብራቸው ህያው ሆነው ከሚያሸንፉ ጥቂት ‘ ዕድለኛ ‘ ኢትዮጵያውያን መሀከል ናቸው። ጽሁፎቻቸው ፣ አምስት አስርተ አመታትን የተሻገረ የአደባባይ አበርክቶቻቸው ትውልድ ያስታዋሰቸው ያወሳቸው ዘንድ ኗሪ ያደርጋቸዋል።
ፕሮፌሰር መስፍንን በኖረው የሀዘን ልማዳችን እየፈሰስን ደረት እየደቃን ፣ እምባ እያነባን ሳይሆን በጎ ስራዎቻቸውን እየዘከርን ፣ የተኖረ ህይወታቸውን እየተረክን የክብር ሽኝት ልናደርግላቸው ይገባል። መስፍን ህይወታቸውን ፍሬያማ አድርገው ኖረውታል ፣ ሊለቀስልን የሚገባን የባከነ ፣ የጨቀየ የዘረኝነት ኑሮ የምንገፋው እኛ ኗሪ ተብዬዎቹ ነን።
መስፍንን ሳስታውስ :
፩ . ፕሮፌሰር መስፍንና ድርጅታቸው ኢሰመጉን እንዳስታውስ ግድ ከሚሉኝ ገጠመኞች አንዱ ለሀገራዊ ክብርና ራስን መቻል ያላቸው የጸና ስሜት አንዱ ነው። ዛሬ የሰብአዊ ድርጅት የመሰረተ ሁሉ ወደ ፈረንጅ ድርጎ በማግስቱ በሚሮጥበት ዘመን ፕ/ር መስፍንና ባልደረቦቻቸው ኢሰመጉ ለኢትዮጵያውያን በ ኢትዮጵያውያን እንዲሆን እጅግ ጥረዋል።
ለዚህ ማሳያ የሚሆን አንዱን ገጠመኝ እናውሳ። በ 80 ዎቹ የስዊትዘርላንድ ኤምባሲ ለኢሰመጉ 40 ምናምን ሺህ ብር ይለግሳል። ያም ሆኖ ኢሰመጉ ያወጣው የሰብአዊ መብት ሪፓርት ይጠጥርበትና ኤምባሲው ሪፖርቱ ላይ ማሻሻያ እንዲያደርግ ጣልቃ ይገባል። ( ኤምባሲው በህወሃት ሰዎች ጫና ሳያድርበት አልቀረም ) ፕሮፌሰርና ጓደኞቻቸው ለኤምባሲው የሰጣችሁንን ገንዘብ ከህዝብ መዋጮ ሰብስበን እንመልስላችኃለን ተጽዕኗችሁን እዚያው በደጃችሁ ይሏቸዋል። ሊስትሮ አልቀረ ምን አዲስ አበቤ በጥቂት ቀናት ገንዘቡን አሰባስቦ ጨረሰ። የጉዳዩን መጨረሻ ባላውቅም ፕሮፌሰር ለሉዐላዊ ክብርና መታፈር ያላቸው አቋም ዛሬም ድረስ ትውስ ይለኛል።
፪. ሁለተኛው የፕሮፌሰር መስፍንን ስብዕና ገልጾ ያሳየኝ እውነት የተፈጠረው በድህረ ቅንጅት በአመራር አባላቱ መሀከል የገባው ልዩነት በገነነበት ሰሞን ነው። በወቅቱ ዲያስፖራ እንደ ለመደው አንተ የሀይሉ ሻውል እኔ የብርሀኑ ነጋ ነኝ ብሎ ለሁለት ተቧድኖ በነገር ይሞሻለቃል። ፕሮፌሰር መስፍን ጥፋቱ ከየትኛው ወገን ነው ተብለው ቢጠየቁ ” ሁሉንም ጭብጨባ አስክሯቸው ነው ” ሲሉ ከህዝብ ጥቅም ይልቅ የመሪዎች ተክለ ሰብዕና የሚፈጥረውን ሳንካ ለሁለቱም ወገን ሳያዳሉ በሰላ ሂስ ተችተዋል። በወቅቱ ብዙ ‘ ትላልቅ ‘ እንላቸው የነበሩ ሰዎች ከቡድን አባቶች ጀርባ መሽገው የነገር ድንጋይ ይወራወሩ ስለነበር የፕሮፌሰር ተግሳጽ ፣ ፍድረትና እውነት አይፈሬነት እጅግ የሚደነቅ ነበር። ፕሮፌሰር ‘ ትላልቅ ‘ የሚሰኙ ፖለቲከኞችን በአደባባይ ገስጸው መስመር ለማስያዝ ድፍረት የነበራቸው ሰው ነበሩ።
ስለፕሮፌሰር – የኔታ መስፍን ብዙ መጻፍ ይቻላል። እርሳቸውን ከመዘከር ባላነሰ ትልቁ ቁምነገር ሊሆን የሚገባው ከአስተምህሮታቸው መገብየቱ ፣ ለራስ ማትረፉ ነው። ፍሬ ያለው የሀገር መካሪ እያለፈ ገለባው ሁሉ ማይክራፎን በሚጨብጥበት ፣ ብዕር በሚሰድርበት በዚህ ክፉ ወቅት የፕሮፌሰር መስፍን ስንብት መንፈስ የሚሰብር ቢሆንም ትተዋቸው የሄዱትን የሀሳብ ክታቦቻቸውን እያነበብን ፣ አበርክቶዎቻቸውን እያወሳን እየተማርንበት እንጽናናለን።
ለፕ/ር መስፍን ቤተዘመዶች እግዜያብሄር መጽናናቱን ይስጣችሁ !
የሰላም እረፍት ይሁንልዎ

 

Related stories   ስብሃት ነጋ የትህነግን የውጪ አገር ሃብትና ንብረት "ለትግራይ ሕዝብ ጥቅም ሲባል" ይፋ እያደረጉ ነው

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *