መስከረም 23 እና 24 የሚከበረውን የኢሬቻ በአል ለመበጥበጥ የተዘጋጁ 503 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ መሳሪያም ተገኝቶባቸዋል።
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ኮማንደር አራርሳ መርዳሳ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለፁት፤ የኢሬቻ በዓል ላይ የሚሳተፉ የበዓሉ ታዳሚዎች በሰላም ወጥተው እንዲገቡ ኮሚሽኑ በጥብቅ እየሰራ ነው።
የግል ፍላጎታቸውን ለማሳካት በተለያየ አቅጣጫ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ሀይሎች እንዳሉና ኮሚሽኑም እንደደረሰባቸው የገለፁት ኮማንደሩ፤ እስካሁን ድረስ 503 ሰዎች፣14 ክላሽ ፣ 26 ቦምብ እና 103 ሽጉጦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡
ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የኢሬቻ በዓል በኮረና ምክንያት እንደ ከዚህ ቀደሙ በርከት ባለ ሰው የማይከበር ሲሆን በገዳ አባቶች የተላለፈውን ውሳኔን ህብረተሰቡ ስራ ላይ ማዋል እንዳለበትም ጄኔራል ኮማንደር አራርሳ ተናግረዋል፡፡
ህብረተሰቡ ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በመሆን ከህወሓት እና ከሸኔ የተሰጣቸውን ግዳጅ በመውሰድና ኦሮሚያን የጦርነት አውድማ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ሀይሎችን በማጋለጥ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የስልጣን ጥም ያላቸው አካላት “ከመስከረም 25 በኋላ መንግስት የለም” እያሉ ህብረተሰቡን ለማወክ የሚፈልጉ አካላት በምንም ሁኔታ እንደማይሳካላቸው ጄኔራል ኮማንደር አራርሳ ተናግረዋል፡፡
የኦሮሚያ ፖሊስ የህዝቡን ሰላም የሚያውኩትን በመከታተል ህግ ለማስከበር በቁርጠኝነት መዘጋጀቱንም ኮማንደሩ ማስታቃቸውን ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል፡፡
 • የቻይናው ሮኬት ስብርባሪ በኢትዮጵያ ቢወድቅ ምን ዓይነት የጥንቃቄ እርምጃዎች ሊወስዱ ይገባል?
  ከቁጥጥር ውጪ የሆነው የቻይና ሮኬት አካል ስብርባሪ በኢትዮጵያ ቢወድቅ ምን ዓይነት የጥንቃቄ እርምጃዎች ሊወስዱ ይገባል? ። የቻይናው 5 ቢ ሮኬት ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ወደ መሬት ለመምዘግዘግ ምድርን በመሽከርከር ላይ ይገኛል። 5 ቢ ሮኬት ከቁጥጥር ውጭ ከሆነበት ከሚያዝያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. እንስቶ በከፍተኛ ፍጥነት በመሬት ዙሪያ እየተሸከረከረ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ስፔስContinue Reading
 • ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መግለጫ
  ጠላቶቿ ፈርሰው ያልቃሉ እንጂ ኢትዮጵያ መቼም አትፈርስም፤ አዲስ አበባም ከሰላማዊ የብልፅግና ጉዞዋ አትስተጓጎልም! ሀገራችን ኢትዮጵያ በታሪኳ ለበርካታ ጊዜያት ከውጭ ጠላቶች ወረራ እና መሰል ጥቃቶች ተሰንዝሮባታል፤ ሁሉንም የውጪ ወረራ እና ጥቃቶችን በጀግኖች ልጆቿ በመመከት ጠላትን አሳፍራ መመለስ የቻለች ሲሆን በአንፃሩ ደግሞ ከአብራኳ የወጡ ከሃዲዎች እና ባንዳዎች ከውጭ ጠላት ጋር በማበር ሲያደሟትContinue Reading
 • አቡነ ማቲያስ መነጋገሪያ ሆነዋል – ኢትዮጵያ ላይ ዘመቻው እንዲከር ጥሪ አቅርበዋል
  ከትሀንግ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው መረጃ የተያዘባቸው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ሰፊ መነጋገሪያ ሆነዋል። በአዎንታና በአሉታዊ ጎን የተሰነዘረባቸው ተቃውሞ መነሻው ” ታፈንኩ” በማለት ሲናገሩ የሚያሳይ ቪዲዮ ወዳጆቻቸው ወይም የቅርብ ታዛዦቻቸው ካሰራጩና ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በኤፒ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ በቲውተር ገጻቸው ካሰራጩት በሁዋላ ነው። ቪዲዮውን ተከትሎ ሙስሊም የኢትዮጵያ ልጆች የአፍጢር ስነContinue Reading
 • Warshaan Keenyaa tiraaktaroota 950 qonnaan bultootaaf dabarse
  Magaalaa Shaashamanneetti kan argamu Warshaan Meeshaalee Qonnaa Ammayyaa Keenyaa kaleessa tiraaktaroota 950 qonnaan bultootaaf dabarse. Sirni walharkaa fuudhiinsaas qonnaan bultoota, dargaggoota waldaan gurmaa’aniifi dhaabbata Keenyaa gidduutti taasifameera. Sirnicharratti Pirezdaantiin Mootummaa Naannoo Oromiyaa, Obbo Shimallis Abdiisaa dabalatee hoggantoonni olaanoo federaalaafi naannolee, akkasumas abbootiin gadaa argamaniiru. Tiraaktaroota 950 qonnaan bultootaafi dargaggoota waldaanContinue Reading
 • ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ የ200 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራረሙ
  ኢትዮጵያና የአለም ባንክ የ200 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት መፈረሙን የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚንስቴር አስታወቀ። ብድሩ አካታች የዲጂታል ኢኮኖሚን ተግባራዊ ለማድረግ የሚውል መሆኑ ተገለጸ። ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ እንደሚያመ ለክተው፣ የብድር ስምምነቱ ትናንት ተፈርሟል፣ በብድር የተገኘው ገንዘብ በዋነኝነት ኢትዮጵያ በ10 ዓመቱ መሪ የልማት እቅድ ላለመችው መጠነ ሰፊ የልማት ግብ እጅግ አስፈላጊ የሆነውንContinue Reading

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   "የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጀግኖች አርበኞች ነፃ ህክምና እንዲሰጥ ወሰነ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *