በአዲስ አበባ የ13ኛ ዙር የጋራ መኖሪያ ቤቶች እድለኞች እና የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች ዛሬ ካርታ፣ ቁልፍ እና ውል ርክክብ በይፋ ተጀመረ።
በከተማ አስተዳደሩ እየተከናወነ ባለው መርሃ ግብር 51 ሺህ 229 የጋራ መኖሪያ ቤት እድለኞች እና 22 ሺህ 915 የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች ካርታ፣ ቁልፍ እና ውል መረከብ ጀምረዋል።
የካርታ፣ ቁልፍና ውል ርክክቡ ዛሬ በይፋ የተጀመረ ሲሆን፥ የሁሉም የጋራ መኖሪያ ቤት እድለኞች እና የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች እስከ ጥቅምት 12 ቀን 2013 ዓመተ ምህረት ድረስ ይረከባሉ ተብሏል።
በዛሬው እለትም ከእደለኞቹ እና የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች የተመረጡ 100 ግለሰቦች ከአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እጅ ቁልፍ፣ ካርታና ውል ተረክበዋል።
ቀሪዎቹ የቤት እድለኞች እና የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች በየክፍለ ከተሞቻቸው ርክክብ መፈፀም እንደሚችሉ ተጠቁሟል።
የከተማ አስተዳደሩ የከተማዋን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በተለያዩ መርሃ ግብሮች የጋራ መኖሪያ ቤቶችን እየገነባ በእጣ ሲያስተላልፍ ቆይቷል።
ለዓመታት በአዲስ አበባ እየተከናወነ በነበረው የልማት ስራ ከቀያቸው የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች ለተለያዩ ምጣኔ ሃብታዊ ችግር መጋለጣቸውን ተከትሎ የከተማዋ አስተዳደር መዲናይቱ በዙሪያዋ የሚገኙ አርሶ አደሮችን የምትገፋ ሳይሆን አብራቸው የምታድግ እንድትሆን የልማት ተፈናቃይ አርሶ አደሮችም የዚህ የቤት ልማት መርሃ ግብር ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል ተግባር መጀመሩ ይታወሳል።
በዳዊት መስፍን
- አትሌት ለተሰንበት ግደይ በቶክዮ ኦሎምፒክ ትሳተፉለች!!“በትግራይ ክልል በነበረው ግጭት የአትሌቷ ልምምድ ተስተጓጉሎ ይሆን?” የሚል ጥያቄ ከኢትዮጵያ ቼክ የቀረበለት አልጣኝ ሀይሌ “በነበረው ችግር ምክንያት አርፍደን መጥተናል። እኛ የነበርነው ደቡባዊ ትግራይ አካባቢContinue Reading
- የእናት አገር ጥሪ አዋጅ ታወጀ –የዱባይ ጸሃይ እንዳትሞቅ ተለክታ በመስፈሪያ ቤቱ ትፈሳለች። ባህር ላይ ተንጣሎ የሰፈረው ቤት የአረብ ንጉሳዊያን መኖሪያ መቅደስ እንጂ የአንድ ለማኝ አገር ዜጋ አይመስልም። ለጊዜው ፓላስ እንበለው።Continue Reading
- CDC Group Targets $1 Billion of African Investments in 2021Centers for disease control and prevention (CDC) Group is planning about $1 billion in Africa investments this year in sectors including infrastructure and finance andContinue Reading
- አብይ አሕመድና ጣጣቴዎች – “አብይ አሕመድ ባይታመሙ ነበር የሚገርመው”“አብይ አህመድ ሰው ናቸው። አብይ አህመድ ሰው ላይ ሊደርስ የሚችለው ሁሉ ይደርስባቸዋል። በመሆኑም ቢታመሙ፣ ጉዳት ቢደርስባቸው አይገርምም። ላለፉት ሶሰት ዓመታት ጉያቸው ውስጥ በተሰገሰጉ እንግዴ ልጆችContinue Reading