በትግራይ ክልል ላይ አተኩረው ከሚዘግቡና መረጃ ከሚያሰራጩ የማህበራዊ ገጾች መካከል አንዱ የሆነው ግዕዝ ሚዲያ እንዳስታወቀው 63 የትግራይ ልዩ ሃይል ሃላፊዎች እንዲነሱ ተደርጓል። በስም የተጠቀሱ አንድ የልዩ ሃይሉ አባል ከተወሰኑ ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን አምልጠው አዲስ ገብተዋል።

ሕወሃት የእንደርታ ተወላጅ በሆኑ የልዩ ሃይል አባላት ላይ እምነት እንደሌለውና ይህንኑ ተከትሎ 63 የሚሆኑ የአካባቢው ተወላጅ የእንደርታ ተወላጅ የልዩ ሃይል አባላት መባረራቸውን ያመለከተው ዜናው በሚጠረጠሩ ላይ አስፈላጊ የእስር ትዕዛዝ እንደተላለፈም ገልጿል።

ቁጥራቸው በይፋ ያልተገለጸ የልዩ ሃይል አባላቱ ጠፍተው አዲስ አበባ እንደገቡ ያመለከተው ዘገባው፣ ከዚህ ቀደም ወደ አማራ ክልል የኮበለሉ የትግራይ ልዩ ሃይል አባላት መኖራቸውን አስታውሷል።

ይህን አስመልክቶ ከክልሉ በኦፊሳል ማስተባበያም ሆነ ማረጋገጫ የሚሆን ዘገባ ያልወጣ ሲሆን፣ ቀደም ሲል ወደ አማራ ክልል ኮብልለዋል የተባሉትን የትግራይ ክልል ልዩ ሃይል አባላት አስመክቶ በቪኦኤ በኩል ማስተባበያ ቀርቦ ነበር። ክልሉ እንዳለው አንድም ወደ አማራ ክልል የኮበለለ የልዩ ሃይል የለም። ክልሉ ይህን ቢልም በተመሳሳይ በቪኦኤ በኩል የአማራ ክልል፣ የወልቃይትና የራያ የማንነት አስመላሽ ሃይላት አመራሮች የትግራይ ክልል ልዩ ሃይላት ወደ አማራ ክልል መኮብለላቸውን አረጋግጠው ነበር።

Related stories   ምርጫ፤ ብሄራዊ ምክክርና የዜጎች ደህንነት የመንግስት ትኩረቶች ሊሆን እንደሚገባ ተጠቆመ

በሌላ ዜና በትግራይ ክልል የሚገኙ አቃቢ ህግ ሰራተኞች መስከረም 25 ስራ ያለ መግባት አድማ እንደሚያደርጉ ለግዕዝ ሚዲያ መግለጻቸውን ሚዲያው አስነብቧል። በትግራይ ክልል የተለያዩ አፈና ስለበዛ እንዚህ የፍትህ አካላትም ፍትህ አጣን እያሉ እንደሆነ መረጃው ደረሰኝ ያለው ግዕዝ ሚዲያ አመልክቷል።

በትግራይ ክልል ብቻ የአቃቢ ህግ ባለሞያዎች ከዳኞች ያነሰ ደሞዝ እንደሚከፈላቸው እና በተደጋጋሚ የትግራይ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ ይሄ ጉዳይ ቢነገረውም ማስተካከል እንዳልቻለ፣ በዚህም ሳቢያ የፊታችን ሰኞ ስራ ባለመግባት አድማ እንደሚያደርጉ ለግዕዝ ሚዲያ በላኩት መልእክት አረጋግጠዋል። ፣ሚዲያው ይህንን ቢልም እስካሁን በክልሉ መገናኛዎች በይፋ የተተቀሰ ነገር አልተሰማም።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *