“Our true nationality is mankind.”H.G.

የምዕራብ ዕዝ ኦነግ ሸኔን ሙሉ በሙሉ እንደመታ አስታወቀ፤ ቢቤኒሻንጉል ተከታታይ እልቂት ትህነግ እጁ እንዳለበት ተረጋገጠ

 
የምዕራብ ዕዝ ም/አዛዥ ሜ/ጀ ይርዳው ገ/መድህን የኦነግ ሸኔ ሃይል ላይ በተወሰደ እርምጃ ሃይሉ መመታቱን አስታወቁ። የኢፌዲሪ የመከላከያ ሚኒስትር እንዳስታወቀው ሰራዊቱ ህገመንግስታዊ ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣና አካባቢዎቹ ላይ የመንግስት መዋቅሮች የወትሮ እንቅስቃሴያቸውን እያከናወኑ ነው። ለሁለት ከተከፈለውና  በአቶ ዳውድ የሚመራው ኦነግ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ይህ ካልሆነ አገሪቱ ወደ ማያበራ ቀውስ ታመራለች ባለበት ማግስት የኦነግ ሸኔ ሃይል መመታቱ ነው ይፋ የሆነው።
 
ሜ/ጀ ይርዳው ገ/መድህን  የግዳጅ ቀጣናው በተፈጥሮ አስቸጋሪ መልካዓ ምድራዊ አቀማመጥና የአየር ፀባይ ያለው ቢሆንም ዕዙ የተሰጠውን ግዳጅ በብቃት እየፈጸመ ነው ብለዋል። አያይዘውም ሰራዊቱ ችግሮችን ተቋቁሞና አሸንፎ ተቋሙ የሰጠውን ተልዕኮ በንቃትና በትኩረት መፈፀሙን አረጋግጠዋል ።
“ሰራዊቱ በሰራው ጠንካራ ስራ ሽፍታው ኦነግ ሸኔ እንደተመታና አሁን ላይ አካባቢው የተረጋጋ ፣ ህጋዊ የመንግስት መዋቅሮች ያሉበት ፣ የተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች የሚከወኑበት ሆኗል” ሲሉ አዛዡ ገልጸዋል።
አቶ ዳውድ እንደሚሉት አብዛናው የኦሮሚያ ክልል መዋቅሮች የተሸራረፉና አሁን ያለው መንግስት ቅቡልነት ስለሌለው አስቸኳይ ሁሉን የሚያካትት የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ጠይቀዋል። ይህ ካልሆነ አገሪቱ ወደማትወጣው ቀውስ ታዘግማለች ብለዋል። 
ትህነግና ኦነግ በሚናበብ መልኩ በህብረት እየተመጋገቡ ተመሳሳይ መግለጫ ቢያወጡም የአገሪቱ የመከላከያ ሃይል ትልዕኮውን እንደሚወጣ ደጋግሞ እያስታወቀ ነው። መንግስትም በሃይል ስልጣን እንቀማለን በሚል በተደራጀ መልኩ የሚንቀሳቀሱትን ሃይላይ ትህነግን ጨምሮ  የከረረ ተቋማዊ ርምጃ በመውሰድ ላይ ይገኛል። 
 
ሜ/ጀ ይርዳው ገ/መድህን እንዳሉት ፣ ዕዙ በዋናነት ህገ-መንግስቱን በሀይል ለመናድ የሚንቀሳቀሱ ፀረ-ሰላም ሀይሎችን መቆጣጠር ፣ ከሁለቱ ሱዳኖች ጋር በስፋት እንደመዋሰኑ በድንበሮች ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ አይኑ ብሌን የሚያየውን ታላቁ ህዳሴ ግድብ ደህንነት በትኩረት መጠበቅ ፣ በዕዙ የግዳጅ ቀጠና የሚገኙ የፀጥታ ሃይሎችን አቅም ማጠናከርና በጋራ የመስራት ተግባራት እያከናወነ መሆኑንን አመልክተዋል።
ም/አዛዡ ፣ ዕዙ እስካሁን ከተዋጣቸው ግዳጆች የተገኙ ውጤቶችን እንደ ግብዓት በመጠቀም ማስቀጠል ፣ እጥረቶችን ማረምና በቀጣይ ለሚሰጡት ግዳጆች አቅም የሚፈጥሩ ተግባራት ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ የመከላከያ ሚኒስቴር በኦፊሳል የፌስ ቡክ ገጹ አስታውቋል።
በተያያዘ ዜና በቤኒሻንጉል ነጹሃንን እያደፈጡ በሚያጠቁ ሃይላት ላይ በተወሰደ የማሳደድ ዘመቻ አስራ አራት ሽፍቶች ሲገደሉ። ቁጥራቸው ለጊዜው በውል ያልተገለጸ ተማርከዋል። የክልሉ መስተዳድር ለቪኦኤ እንዳረጋገጡት ይህ ታጣቂ ሃይል ከትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ተልዕኮ የሚቀበልና የሚረዳ መሆኑንን አረጋግጠዋል። ይህም በማስረጃ መረጋገጡን ተናገዋል።
በክልሉ በኢንቨስትመንት ስም የገቡ ባለሃብቶች በስራ ቀጠራ ስም ታታቂዎችን እንደሚያደራጅ፤ እንደሚያስታጥቁና ለዚሁ ተግባር እንደሚያሰማሩ ያስታወቁት የክልሉ መስተዳድር፣ አሁን ላይ ሽፍቶቹን የመንጠር ስራ ተጠናክሮ እየተሰራ መሆኑንን ይፋ አድረገዋል።
በቅርቡ 14 ሰዎችን በተሽከርካሪ ሲሄዱ ጠብቀው መንገድ ላይ የጨፈጨፉት ሽፍቶች ስምንት ሰዎችን ማቁሰላቸው ከተሰማ በሁዋላ ህዝብ ቁጣ አሰምቶ ነበር። አካባቢው በኮማንድ ፖስት ስር ሆኖ በተደረገው ጥብቅ አሰሳ ቁጥራቸው ከተጠቀሰው በላይ ሽፍቶች መደምሰሳቸውን መከላከያ አሰሳውን አተናክሮ እርምጃ እየወሰደ መሆኑንን ገልጸዋል።
ፎቶ መከላከያ ሚኒስቴር ፊስ ቡክ 

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   “አቡነ ማቲያስ የሰጡት መግለጫ የግላቸው እንጂ የቅዱስ ሲኖዶስ ወይም የቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ አይደለም”
0Shares
0