የትግራይ ክልልን ህገወጥ ሲል የሰየመው የፌደሬሽን ምክር ቤት የበጀት ማዕቀብ መጣሉን ተከትሎ ውሳኔው አገር ይበታትናል ሲሉ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ገልጸዋል። ውሳኔውን ህዝብ ላይ ጦርነት ማወጅ እንደሆነም ተናግረዋል። ውሳኔው ከመዘግየቱ በቀር ትክክለኛ መሆኑንን በርካቶች እየገለጹ ሲሆን፣ ገና ዝርዝር አፈጻጸሙ በተከታታይ እንደሚገለጽ መንግስት አስታውቋል።

ዶክተር አብርሃም ተከስተ ለቢቢሲ  ውሳኔው በትግራይ ሕዝብ ላይ ጦርነት እንደማወጅ ይቆጠራል ሲሉ፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት የህዝብ አገልግሎት እንዳይዛነፍ፣ ህዝብ እንዳይጎዳ፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ስራቸውን እንዳይበደል፣ ልማት እንዳይቆም የበጀት ማዕቀቡ በጥናት እንደሚከናወን መግለጹን ያነጋገራቸው ቢቢሲ አላነሳባቸውም። መንግስት መተደጋጋሚ ጦርነት ውስጥ የመግባት ዓላማ እንደሌለው፣ ይልቁኑም ጊዜያዊ ህጋዊ አስተዳደር ለመመስረት ማቀዱንም አስመልክቶ ቢቢሲ በዘገባው አላከተተም። ዶከተሩም ምላሽ አልሰጡበትም።

” ጦርነት የማድረግ ሃሳብም ሆነ እቅድ የለም” ሲልመንግስት በተለያዩ ጊዜያት ይፋ ሲያደርግ ቢቆይም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሰብሳቢው እንዳስታወቁት በዚህ ውሳኔ ሕዝብ እንዳይጎዳ ጥንቃቄ ይወሰዳል። በቅርብ ክትትል የሚያደርጉ አካላት ተመድበው የሚከታተሉት የአፈጻጸም ዝርዝር መመሪያ የሚወጣበት፣ ውሳኔው ህገመንግስቱን በመጣስ የራሱን ምርጫ በራሱ ውሳኔ አካሄዶ ከህጋዊነት ወደ ህገወጥነት የተሸጋገረውን ሃይል ላይ ብቻ እንደሆነ አመልክተዋል።

የቢቢሲ ሙሉ ዘገባ ከታች ያለው ነው።

የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሕገወጥ መንገድ የተቋቋመ ነው ላለው የትግራይ ክልል ም/ቤትና ካቢኔ የፌዴራል መንግሥት የበጀት ድጎማ እንደማያደርግ መግለጹ ክልሉን ከፌዴሬሽኑ እንዲወጣ የሚገፋ ነው አሉ።

ይህ ውሳኔ እስካሁን ሲወሰድ የነበረው “ሕገወጥ እርምጃ” ቀጣይ አካል ነው ያሉት አብርሃም (ዶ/ር)፣ እርምጃው ኃላፊነት የጎደለው ከመሆኑ በተጨማሪ “የትግራይ ክልልን ከፌዴሬሽኑ እንዲወጣ የሚገፋ ነው” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀደም ብሎ የትግራይ ክልል ምክር ቤትና ከፍተኛ የሕግ አስፈፃሚው አካል በሕገመንግሥቱ ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ ሁሉም የፌዴራል ተቋማት ምንም ዓይነት ሕጋዊ ግንኙነት እንዳያደርግ የወሰነ ሲሆን፤ በማስከተልም ከፌዴራል መንግሥቱ የሚደረግ የበጀት ድጎማን እንዳያገኝ መወሰኑን የምክር ቤቱ አፈጉባኤ ለብሔራዊው ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

Related stories   ሱዳን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ላይ የሉዓላዊነት ጥያቄ እንደምታነሳ አስጠነቀቀች፤ "ብሄራዊ የጀግንነት ጥሪ ያፈልጋል"

ይህንን ውሳኔ በሚመለከት አብረሃም ተከስተ (ዶ/ር) ለቢቢሲ እንደተናገሩት ምክር ቤቱ የፌደራል መንግሥት ከክልሎች ከሚሰበስበው ገቢ ላይ ለትግራይ ክልል መንግሥት ድጎማ እንዳይሰጥ ውሳኔ ማሳለፉ “በሌላ አገላለጽ ትግራይ የፌዴሬሽኑ አካል አይደለችም እንደ ማለት ነው” ብለዋል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤቱን ውሳኔ “በትግራይ ክልልና ሕዝብ ላይ ጦርነት እንደማወጅ” አድርገው እንደሚቆጥሩት የተናገሩት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፤ ለዚህም ደግሞ ምክንያታቸውን ሲገልፁ ፌዴሬሽኑ እና የፌዴሬሽኑ አባል መንግሥታት አንዱ የሚያገናኛቸው የበጀት ሥርዓቱ መሆኑን አመልክተዋል።

የትግራይ ክልል የፌዴሬሽኑ አባል ናት ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንት አብረሃም (ዶ/ር)፤ እርምጃው ፌዴሬሽኑን የሚበትን ነው ብለዋል። የፌዴሬሽኑ አባላት አንዱ መሳሪያ የበጀት ግንኙነቱ ነው የሚሉት አብረሃም (ዶ/ር) ትግራይን ከበጀት ውጪ ማድረግ ማለት “ከፌዴሬሽኑ እንድትወጣ የሚገፋ ነው” ነው ሲሉ ተናግረዋል።

እርምጃውን “በጣም አደገኛ” ያሉት አብረሃም (ዶ/ር)፣ አገሪቷን ወደ ቀውስ የሚያስገባ፣ የሚበትን በማለት “ኃላፊነት የጎደለው እርምጃ” ሲሉም ኮንነውታል።

የፌደራል መንግሥት ገቢ የሚሰበስበው ትግራይን ጨምሮ ከክልሎች ነው ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ ይህንኑ መልሶ ለክልሎች እንደሚያከፋፍልም ተናግረዋል።

ከትግራይ የሚሰበስበውን ገቢ ለትግራይ አላካፍልም ማለት “እብደት ነው” በማለት ውሳኔውን አጣጥለውታል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ እንዳለው ወደዚህ እርምጃ የሚገባ ከሆነ ክልሉ ለፌደራል መንግሥቱ ከትግራይ የሚሰበስበው ገቢ ላይ እርምጃ እንደሚወስድም አመልክተዋል።

እርምጃው ምን ዓይነት ነው ተብለው የተጠየቁት አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) የፌደራል መንግሥት ባለፈው ዓመት ብቻ ከትግራይ ክልል ወደ ሰባት ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን፣ በዚህ በተያዘው 2013 ዓ.ም ደግሞ ወደ ዘጠኝ ቢሊየን ብር እሰበስባለሁ ብሎ ማቀዱን ገልፀዋል።

Related stories   ህወሃትና ኦነግ ሸኔ በሽብርተኛ ድርጅትነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሐሳብ ቀረበ

ስለዚህ ይህንን ሰብስቦ ሕጋዊ የፌዴሬሽኑ አካል ለሆነችው ትግራይ አላከፋፍልም የሚል መንግሥት “የእብደት ሥራ ነው” በማለት እንዲሁ ዝም ብለን አናይም ሲሉ ተናግረዋል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሕገወጥና ተፈጻሚነት የሌለው ነው ያለውና ባለፈው ዓመት ማብቂያ ላይ ከሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች በተለየ በትግራይ ክልል በተናጠል የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ የተቋቋማው የክልሉ መንግሥት ላይ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

በዚሁ መሰረትም ሁሉም የፌዴራል ተቋማት ከትግራይ ክልል ከፍተኛ አስፈፃሚ አካላት ጋር እንደሕጋዊ አካላት በመቁጠር ደብዳቤ መፃፃፍ፣ መረጃ መላላክ፣ የፌዴራል ተቋማት ለክልል ተቋማት የሚሰጧቸውን ድጋፎች መስጠት፣ በፌዴራል ደረጃ የሚካሄዱ መድረኮች ላይ ማሳተፍ የመሳሰሉ ጉዳዮችን እንዳያከናውኑ ወስኗል።

ከዚህም ጎን ለጎን የክልሉ ሕዝብ መሰረታዊ የልማትና የአገልግሎት ተጠቃሚነቱ እንዳይስተጓጎል እንደ ቀበሌ ፣ወረዳ ፣ ከተማ ካሉ ሕጋዊ መዋቅሮች ጋር ብቻ ግንኙነት እንደሚደረግና በዚህም ላይ ክትትል እንደሚደረግ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ አደም ፋራህ ለኢቲቪ ተናግረዋል።

የበጀት ድጎማን በተመለከተም “በሕገወጥ መንገድ የተቋቋመው የትግራይ ምክር ቤትና ካቢኔ ሕጋዊ ሰውነት ስለሌለው” ከፌዴራል መንግሥት የበጀት ድጎማ እንደማያገኝ ተነግሯል።

ነገር ግን የፌደራል መንግሥቱ በትግራይ ክልል ካሉ የከተማ አስተዳደሮች፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ጋር በሚኖር ግንኙነት አማካይነት ሕዝቡ ማግኘት የሚገባውን መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲያገኝ የሚደረግ መሆኑና ክትትልም እንሚደረግበት ተነግሯል።

 • ዶክተር አብራሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ!
  የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሃላፊ ሆነው ለስድስት ወራት በሃላፊነት የቆዩት ዶ/ር ሙሉ ነጋ በዛሬው እለት ከስልጣን መነሳታቸውን ማረጋገጥ ተችሏል። በምትካቸው ዶክተር አብራሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንትም የሆኑት ዶ/ር አብራሃም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው እየሰሩ ይገኛሉ። ዶ∕ር አብርሃም በተለያዩ የመንግስትContinue Reading
 • እኛ የምንመርጠው አባትና አያቶቻችን የመረጡትን ነው።
  ከመንደር ወጥተናል።ሀገርን መርጠናል።ልካችን ሳንመርጥ የተወለድንበት ብሔራዊ ማንነታችን ሳይሆን ኢትዮጵያዊነት ነው። ኢትዮጵያዊነት ስንል ለህዝቦቿ ደህንነት እና የብሔራዊ ሠንደቅ ዓላማ ክብር ወዶ እና ፈቅዶ የመሞት ቁርጠኝነት የሚያላብስ ማንነት ነው። የእኛ ምርጫ በጊዜ ወቅት የሚገደብ፣ በውስጥና ውጭ አካል የሚታዘብ አጨቃጫቂና አከራካሪ አይደለም።በውርስ የሚተላለፍ ነው። የብሔሮችና ብሔረሰቦችን ሀገራዊ አስተዋፅኦ የምንለከው በአባት አያቶቻችን ከአእምሮ በላይContinue Reading
 • አውሮፓ ህብረት – ላለፉት 28 ዓመታት በኢትዮያ ተላላኪ መንግስት እንደነበር ለኢትዮጵያ ህዝብ አመነ
  “የአውሮፓ ህብረት ምርጫ የማይታዘበው በበጀት እጥረት መሆኑንን ገልጾልናል” ሲሉ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ። ህብረቱ ወዲያውኑ ” በበጀት እጥረት ምክንያት ሳይሆን የቀረነው ስላልተጋበዝን ነው” ሲል ድምጹን አሰማ። ምላሽ ሰጠ። ጉዳዩ ከዚያ በላይ አልሄደም። ነገሩ ህወሃት የሚባለው አገዛዝ ቀደም ሲል የገባው ኮንትራት ነበርና ብዙም አስገራሚ እንዳልነበር በወቅቱ ብዙ ተብሎ እንደነበርContinue Reading
 • የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አገር ለማተራመስ በህቡዕ የተደራጁ በርካታ ግለሰቦችን ከነመዋቅራቸውና መስሪያዎቻቸው በቁጥጥር ስር አዋለ፤
  በተጨማሪም በውጭ በተለያዩ ሀገራት ሆነው ይህንን ህቡዕ አደረጃጀት ሲያስተባበሩ እንዲሁም የፋይናንስ፣የሃሳብና የሎጀስቲክስ ድጋፎችን ሲያደርጉ የነበሩ ፕሮፌሰር አበራ መሸሻ፣ አቶ ተሻለ ከበደ ኢዶ፣ወይዘሮ የሀረርወርቅ ጋሻው፣ አቶ አስፋው ጀቤሳ፣ አቶ መዕረግ፣ አቶ ቢኒያም፣ አቶ ኪሩቤል፣ ወይዘሪት ሊሻን አህመድ፣ ዶ/ር ገነት፣ ወይዘሮ አረጋሽ፣ ኢንጀነር ሊሻን ግዛውና አቶ ሀገሬ አዲስ በወዳጅ ሀገራት ትብበርና  ከኢንተርፖል Continue Reading

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *