የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የህግ ግንዛቤ ለማሳደግ በየሳምንቱ አርብ ከሚያቀርባቸው የህግ ማብራሪያ ጽሁፎች መካከል  ለዛሬ  በማህበራዊ ሚዲያዎች የጥላቻ ንግግር እና ሀሰተኛ መረጃ የማሰራጨት ድርጊት የሚያስከትለውን የህግ ተጠያቂነት በተመለከተ ሰፋ ያለ ማብራሪያ አቅርቧል። እንዳለ አትመነዋል።
 
1. የማህበራዊ ሚዲያ ጽንሰ ሃሳብና በአገራችን ስላለዉ የአጠቃቀም ሁኔታ
በኢንተርኔት ላይ ከምንጠቀማቸው እጅግ በጣም ዝነኛ ከሆኑ መካነ ድሮች መካከል የማኀበራዊ ሚዲያዎች ይገኙበታል። ፌስቡክ ከቢሊዮን በላይ፣ ኢንስታግራም እና ትዊተር እያንዳንዳቸው በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች አሏቸው። ማኀበራዊ ሚዲያዎች የተገነቡት የተለያዩ ሃሳቦችን፣ ፎቶግራፎችን እና የግል መረጃን ለማጋራት ነው። ይሁን እንጂ አሁን ላይ አገራችንን ጨምሮ በተለያዩ የአለመ አገራት ዉስጥ ሰዎች እነዚህን ድረገጾች ለታለመላቸዉ በጎ ተግባራት ከማዋል በተቃራኒዉ ለእኩይ ተገባረት ለምሳሌ የጥላቻ ንግግሮችን እና የሃሰት መረጃዎችን ለማሰራጨት ሲጠቀሙት ይሰተዋላል፡፡ በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተስፋፉ የመጡት ኃላፊነት የጎደላቸው መልዕክቶችና የሐሰት ወሬዎች በተለይ እንደፌስቡክ ባሉ የማህበራዊ ድረ ገጾች አንድን ቡድን፣ ብሔር የሚያንቆለጳጵሱ፣ የሌላውን ብሔር ዝቅ የሚያደርጉ፣ የሚዘልፉ፣ የሚያዋርዱ ከፋፋይ አጀንዳዎች በሀገሪቱ ለሚከሰቱ ግጭቶች ምክንያት ናቸዉ፡፡
2. የማህበራዊ ሚዲያዎች አጠቃቀም ገደብ በኢትዮጵያ
የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት ለማህበራዊ ስምሪት፣ ለፖለቲካ መረጋጋት፣ ለሀገራዊ አንድነት፣ ለሰብዓዊ ክብር እና ለብዝሃነት ጠንቅ መሆኑን በመገንዘብ በተለይም በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ በህብረተሰቡ መካከል ያሉ መልካም እሴቶች በጥላቻ ንግግሮችና በሀሰተኛ መረጃ ስርጭት ምክንያት በከፍተኛ ደረጃ እየተሸረሸሩና ለሀገርም ስጋት እየደቀኑ በመሆናቸው በቅርቡ የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር አዋጅ ቁጥር 1185 ጸድቆ ስራ ላይ ዉሏል፡፡
በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ዕውቅና ከተሰጣቸው መብቶች አንዱ አንቀጽ 29 ላይ የተደነገገው ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ቢሆንም ይህ መብት በሕገ መንግሥቱ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ስምምነቶችም ጭምር ገደብ የሚጣልበት ነዉ፡፡ በመሆኑም ሰዎች ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብታቸውን ተግባራዊ ሲያደርጉ ሰብዓዊ ክብርን፣ የሌሎችን ደኅንነትና ሰላም አደጋ ላይ ከሚጥል ንግግር መቆጠብ ይኖርባቸዋል፡፡
የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣዉ አዋጅ ስለ የጥላቻ ንግግርና ሃሰተኛ መረጃ ስርጭት ምንነት እንዲሁም ድረግቶቹን ፈጽሞ የተገኘ ሰዉ ስለሚቀጣዉ የወንጀል ቅጣት እንደሚከተለዉ እናያለን፡፡
የጥላቻ ንግግር ማለት በአንድ ሰዉ ወይም የተወሰነ ቡድን ማንነት ላይ ያነጣጠረ፣ ብሄርን፡ብሄረሰብንና ህዝብን፣ ሀይማኖትን፣ ዘርን፣ ጾታን ወይም አካል ጉዳተኝነትን መሰረት በማድረግ ሆን ተብሎ ጥላቻን፣ መድሎን ወይም ጥቃትን የሚያነሳሳ ንግግር ሲሆን ንግግሩ በቃል፣ በጽሑፍ፣ በምሥልና ሥዕል፣ በቅርጻ ቅርጽ እና በሌሎች ተመሳሳይ መንገዶች መልእክትን የማሰራጨት ተግባርን በመጠቀም የተደረገ ሊሆን ይችላል፡፡
በመሆኑም በአዋጁ አንቀጽ 4 እና 7(1) መሰረት የጥላቻ ንግግርን በብሮድካስት፣ በህትመት ወይም በማህበራዊ ሚዲያዎች ወይም በሌላ ተመሳሳይ ዘዴዎች አማካኝነት በጽሁፍ፣ በምስል፣ በድምጽ ወይም በቪዲዮ ማሰራጨት የተከለከለና ይህን የተከለከለዉን የጥላቻ ንግግር ማድረግ እስከ ሁለት አመት በሚደርስ ቀላል እስራት ወይም ከብር 100,000 ያልበለጠ መቀጮ ያስቀጣል፡፡ በጥላቻ ንግግሩ ምክንያት በግለሰብ ወይም በቡድን ላይ ጥቃት የተፈጸመ እንደሆነ ቅጣቱ ከአንድ አመት እስከ አምስት አመት የሚደርስ ቀላል እስራት ነዉ፡፡(አንቀጽ 7(2) በሌላ በኩል ደግሞ በአንቀጹ ንሁስ አንቀጽ 4 መሰረት ወንጀሉ የተፈጸመው ከአምስት ሺ በላይ ተከታይ ባለው የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ከሆነ ወይም በብሮድካስት አገልግሎት ወይም በየጊዜው በሚወጣ የህትመት ውጤት ከሆነ ቅጣቱ እስከ ሶስት አመት የሚደርስ ቀላል እስራት እና ከብር 100,000 ያልበለጠ መቀጮ ይሆናል፡፡
ከጥላቻ ንግግር በተጨማሪ አዋጁ ሃሰተኛ የሆነ መረጃ ማሰራጨትንም በወንጀልንት የከለከለ ሲሆን ሀሰት የሆነና የመረጃውን ሀሰተኝነት በሚያውቅ ወይም መረጃውን የሚያሰራጨው ሰው ካለበት አጠቃላይ ሁኔታ አንጻር የመረጃውን እዉነተኝነት ለማጣራት በቂ ጥረት ሳይደረግ የሚሰራጭ ሁከት ወይም ግጭት የሚያነሳሳ ወይም ጥቃት እንዲደርስ የሚያደርግ እድሉ ከፍ ያለ የሀሰት ንግግር ነው በሚል ትረጉም ተሰጥቶታል፡፡ በአንቀጽ 5 እና 7(3) መሰረት የሐሰት መረጃን በአደባባይ ስብሰባዎች በብሮድካስት፣ በህትመት ወይም በማህበራዊ ሚዲያዎች ወይም በሌላ ተመሳሳይ ዘዴዎች አማካኝነት በጽሁፍ፣ በምስል፣ በድምጽ ወይም በቪዲዮ ማሰራጨት የተከለከለና ይህን ተግባር የፈጸመ ሰዉ እስከ አንድ አመት በሚደርስ በቀላል እስራት ወይም ከብር 50,000 ባልበለጠ መቀጮ ይቀጣል፡፡ ወንጀሉ የተፈጸመው ከአምስት ሺ በላይ ተከታይ ባለው የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ከሆነ ወይም በብሮድካስት አገልግሎት ወይም በየጊዜው በሚወጣ የህትመት ውጤት ከሆነ ቅጣቱ እስከ ሶስት አመት የሚደርስ ቀላል እስራት እና ከብር 100,000 ያልበለጠ መቀጮ ይሆናል፡፡(አንቀጽ 7(4) በሌላ ሁኔታ ሐሰተኛ መረጃ በመሰራጨቱ ምክንያት በግለሰብ ወይም በቡድን ላይ ጥቃት የተፈጸመ ከሆነ፣ ሁከት ወይም ግጭት የተከሰተ እንደሆነ ቅጣቱ ከሁለት እስከ አምስት አመት በሚደርስ ቀላል እስራት የሚሆን ሲሆን ምንም ጉዳት ካልደረሰ ጥፋተኛውን ለማረም የተሻለ ነው ብሎ ሲያምን ፍርድ ቤት በእስራት ምትክ የግዴታ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራን በአማራጭ ቅጣትነት ሊወስን ይችላል።(አንቀጽ 7(5)(6))
ከለይ የተቀመጡት ተጠያቂነቶች እንዳለሆነዉ በአዋጁ አንቀጽ 6 ስር ንግግሩ የሌላ ሰዉ ሆኖ ለትምህርታዊ ወይም ሳይንሳዊ ጥናት አካል ለማድረግ፤ንግግሩን በተመለከተ የዜና ዘገባ ወይም ትንታኔ ለመስራት ወይም የፖለቲካ ትችት ለመስጠት፤የኪነጥበብ ፣ ትወና ወይም መሰል የስነጥበብ ውጤት በማድረግ ህብረተሰብን ለማስተማር፤ ወይም የሃይማኖት አስተምህሮት አካል እንደሆነ እንዲሁም ንግግሩን ያሰራጨው ወይም ያደረገው ሰው የመረጃውን እውነተኛነት ለማረጋገጥ በሱ ሁኔታ ካለ ሰው የሚጠበቀውን ምክንያታዊ ጥረት ያደረገ እንደሆነ እንደ ጥላቻ ንግግር ወይም የሃሰት መረጃ ስርጭት የማይወሰድ ስለመሆኑ በልዩ ሁኔታ ተደንግጓል፡፡
3. በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመቅረፍ ምን መደረግ አለበት
በመሆኑም ህብረተሰቡ የጥላቻ ንግግርና ሃሰተኛ መረጃን ማሰራጨት በወንጀል የሚያስጠይቅ መሆኑን ከመረዳት ባለፈ ተግባሩ እጅግ በጣም አስነዋሪና ለሀገር መፈራረስ ምክንያት መሆኑን በመገንዘብ ሃሰብን በነጻነት የመግልጽ መብቱን በአግባቡ መጠቀም አለበት፡፡
በመንግስት በኩልም ለነዚህ የጥላቻ ንግግሮች እንዲሁም ሃሰተኛ መረጃ ስርጭቶች ምክንያት የሆኑትን በህብረተሰቡ መካከል ለተፈጠሩት ቁርሾዎች እና አለመግባባቶች ብሄራዊ መግባበቶችንና እርቆች እንዲፈጸሙ ሁኔታዎችን ማመቻቸት እንዲሁም ህጉን በሚጥሱ ግለሰቦች ላይም ተገቢዉን እርምጃ መዉሰድ አስፈላጊ ነዉ፡፡ ከዚህም ባለፈ ለማህበረሰቡ በተለይም ለወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል በጉዳዩ ላይ ሰፊ የሆነ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መሰራት አለባቸዉ፡፡
 • “በተለምዶ ‘ሸኔ’ የሚባለው ራሱን ‘የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት’ ብሎ የሚጠራው ቡድን ነው”
  በርካቶች ‘ሸኔ’ እያለ እራሱን የሚጠራ ድርጅት በሌለበት እንዴት አሸባሪ ተብሎ ይሰየማል ሲሉ ይጠይቃሉ። ይህ ስያሜ አንዳች ነገር ለመሸፈን ተፈልጎ ነው በሚል ጥርጣሬያቸውን የሚገልፁ ምሁራንም አልጠፉም። ለመሆኑ ‘ሸኔ’ ማነው? በዚህ ጉዳይ ላይ በዛሬው ዕለት የተጠየቁት የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዮስ ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተዋል፦ “በተለምዶ ‘ሸኔ’ የሚባለው እራሱን ደግሞ ‘የኦሮሞContinue Reading
 • በቡድን ተደራጅተው የውንብድና ወንጀል የፈጸሙት ተከሳሾች ከ18 እስከ 20 ዓመት በሚደርስ እስራት ተቀጡ፡፡
  ተከሳሾች 1ኛ ተመስገን ማርቆስ፣ 2ኛ ዳንኤል ተዘራ፣ 3ኛ ሲሳይ ተሸመ፣ 4ኛ አቤል ውብሐረግ የተባሉ ተከሳሾች በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32(1)(ሀ) እና 671(2) በመተላለፍቸው ዐቃቤ ህግ ክስ መስርቶባቸዋል፡፡ ተከሳሾቹ ጥቅምት 5 ቀን 2011 ዓ.ም ከለሊቱ 9፡00 ሰዓት ሲሆን በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ወረዳ 17 ጤናContinue Reading
 • “ዶክተር ነኝ” በማለት ሲያጭበረብር የተገኘ ግለሰብ በእስራትና በገንዘብ ተቀጣ
  የጎባ ወረዳ ፍርድ ቤት በጎባ ሪፈራል ሆስፒታል “የህክምና ዶክተር ነኝ” በማለት በተደጋጋሚ ህብረተሰቡ ላይ የማጭበርበር ወንጀል ፈጽሟል ያለውን ግለሰብ በ6 ዓመት ከ6 ወር እስራትና በገንዘብ ቀጣ። ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት የቅጣት ውሳኔውን ያሳለፈው በጎባ ከተማ ኦዳ በሃ ቀበሌ ነዋሪ በሆነው አብዱልጀዋድ አማን ላይ ነው። ግለሰቡ በተደጋጋሚ በጎባ ሪፈራል ሆስፒታልContinue Reading
 • የፍትህ ያለህ የሚሉት የ87 ዓመት አረጋዊቷ እሮሮ
  <<ጉልበቴ እንደዛሬው ሳይደክም በ1976 ዓ.ም የሰራሁትን መጸዳጃ ቤት በተንሻፈፈ ፍርድ አፍርሽ ተብዬ ተወስኖብኝ የፍትህ ያለህ! ፍትህ ተዛብቶብኛል የሚሉት ገርበ ጉራቻ ከተማ ነዋሪ የ87 ዓመት አዛውንቷ ወይዘሮ እናኑ ክብረት ናቸው፡፡ ሰሚ አጥቼ እያለቀስሁ እገኛለሁና ህዝብና መንግስት ይፍረደኝ>> ሲሉ ለዝግጅት ክፍላችን አቤቱታቸው አቅርበዋል። በገርበ ጉራቻ ከተማ ተወልደው እንዳደጉ የሚናገሩት ወይዘሮ እናኑ ክብረት፤Continue Reading

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   “በተለምዶ ‘ሸኔ’ የሚባለው ራሱን ‘የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት’ ብሎ የሚጠራው ቡድን ነው”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *