ባልተለመደ መልኩ ምሽት ላይ በተካሄደው ወታደራዊ ትዕይንት ፒዮንግያንግ ከዚህ በፊት ያልነበራት የረጅም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤል ማሳየቷ ተገልጿል።

በትዕይንቱ ላይ ምንም አይነት የውጭ ሃገር የሚዲያ ተቋማት እንዲገቡ ባለመፈቀዱ ሳቢያ የትዕይንቱን አጠቃላይ ሂደት ማወቅ አልተቻለምም ነው የተባለው። በወታደራዊ ትዕይንቱ የሃገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ከወታደራዊ ሹማምንቶቻቸው ጋር በመሆን የታደሙ ሲሆን፥ መልዕክትም አስተላልፈዋል።

Related stories   በኢትዮጵያ ከፍተኛ መረጃ የመሸከም አቅም ያላቸው ማዕከላት ሊገነቡ ነው

ኪም ሃገራቸው ራሷን ለመከላከልና የሚቃጣባትን ትንኮሳ ለመከላከል ወታደራዊ አቅሟን ታጠናክራለች ብለዋል። ኪም በንግግራቸው አንድም ሰሜን ኮሪያዊ በኮሮና ቫይረስ ባለመያዙ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የሃገሪቱን የሰራተኞች ፓርቲ 75ኛ አመት ምስረታ ምክንያት በማድረግ የተከናወነውን ወታደራዊ ትዕይንት በተለይም ምዕራባውያን በአንክሮ ተከታትለውታል።

በትዕይንቱ ላይ ወታደሮች አዲስና ዘመናዊ መሳሪያ መታጠቃቸው የተነገረ ሲሆን ለየት ያሉ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችም ታይተዋል ነው የተባለው። ከሁሉም በላይ ግን ግዙፍና ለየት ያለ ሃገር አቋራጭ ባለስቲክ ሚሳኤል መታየቱን የሳተላይት ምስሎችን ዋቢ ያደረጉ መረጃዎች ያመላክታሉ።

Related stories   ዝነኛው የቴሌቭዥን መርሀ ግብር መሪ ላሪ ኪንግ አረፈ

ምንጭ፦ ቢቢሲ – (ኤፍ ቢ ሲ)

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *