በቅርቡ አንድ እጅግ የማከብረው ዘማሪ ደወለልኝና አንድ በzoom የተዘጋጀ ውይይት እንዳለና እኔን እንድገኝ ጠየቀኝ። እኔም ጥሪውን ተቀበልኩት። ውይይቱ የነበረው ስለ ዝማሬና ዘፋኝነት ነው። በzoom ወደ ሚደረገው ፕሮግራም ገብቼ ሳዳምጥ ያንን ዝግጅት ያዘጋጁት አገልጋዮች የተነሱበትን ሐሳብ አከብራለሁ። ይህንን ዝግጅት ይመለከተኛል ብለው በማዘጋጀታቸው ምስጋና ይገባቸዋል። ሆኖም ግን ውይይቱ ወደ አንድ ጽንፍ ያደላና የሙግት አካሄድ ግድፈት እንዳለበት አስተውያለሁ። ያንንም ለጋበዘኝ ዘማሪ ነግሬያለሁ።
ከዚህ በመነሳት እኔ “ከሰላም ሰው ነኝ” ስራ በኃላ አንዳንዶች ዘፋኝ ሊያደርጉኝ ሲሞክሩ፤ አንዳንዶቹ ትውልድ አሳች አድርገው ሲናገሩ አያለሁ ፣ እነዚህ ጥቂት ግለሰቦች በሰዎች ፊት “የሰላም ሰው ነኝ” ዝማሬን ምክኒያት ያድርጉት እንጂ በእኔ ላይ ያላቸውን (መነሻው ምን እነደሆነ ፈጽሞ የማላውቀው) ጥለቻቸውን የሚያነጸባርቅ ድርጊታቸውን ከጀመሩ ብዙ አመታት ተቆጥረዋል። እነዚህን አገልጋዩች የበደልኳቸው ነገር ቢሮር እግራቸው ላይ ወድቄ ይቅርታ በጠየኳቸው ነበር ነገር ግን ለእነርሱ መልካም ከማድረግ ውጭ ምንም ክፉ ነገር ያላደረኩባቸው ናቸው ፤ በተደጋጋሚ በጽሁፍ እና በውስጥ ለውስጥ ሽኩቻ የእኔን ነገር ለማጥላላትና በቅዱሳን ልብ ጥያቄ ለመጫር በትጋት የሚሰሩት። ያልገባቸው ነገር ቢኖር እኔን ከፕርቴስታንቱ ልብ ማውጣት ይሳካላቸው ይሆናል ፣ ከእግዚአብሔር ልብ ግን ማውጣት አይችሉም።
.
ከእነዚህም አንዳንዶቹ ከእኔ በፊት በግልጽ ማህበራዊ መዝሙር ሰርተው በሆፕ ሚውዚክ ቻናል በመልቀቅ ፈር ቀዳጅ ሊባሉ የሚችሉ ሆነው “ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ እንዲሉ ሆኖ ነገሩ” እኔ በህፕ ቻናል መልቀቄ የተለየ ሀጢያት እንደሰራ ሰው በማድረግና አለምን እና ቤተክርስቲያንን ልታጋባ ነው በሚል ቅዱሳን በእኔ ላይ ያላቸው ቅንነት እንዲበላሽ የሚያደርግ ስራ በድብቅ እና በግልፅ ይሰራሉ ። አንዳንድ ሰዎች ደመ መራራ የሚባሉት ሌላው ሰው ሲያደርገው ማንም ምንም ያላለበትን ጉዳይ እነሱ ሲያደርጉት እንደትልቅ ነገር ይቆጠራል እኔ ምናልባት ደመ መራራ ሆኜ ይሆን? ቤተክርስቲያን አካባቢ አንዲት የምሰማት አባባል አለች ‘ይሄን ጉዳይ በሶሻል ሚዲያ እናጬኸው’ ይላሉ። የእኔን ጉዳይ እየተከታተሉ በሶሻል ሚዲያ የሚያጮሁ ግሩፓች አሉ አዎ በደንብ አሉ።ነገር እነዚህ ሰዎች ሳያውቁት የበለጠ ላመንኩበት ነገር እንድበረታ እና በሌሎች ዘንድ ተሰሚነት እንዲኖረኝ እያገዙኝ ነው ። እግዚአብሔር ይባርካቸው።
በተቃራኒው ሌሎቹ ደግሞ እጅግ በጣም ጥሩ ሀገራዊ እና መፅሐፍ ቅዱሳዊ ስራን እንደሰራሁ ይነግሩኛል ፤ ስለዚህ ከዚህ በመነሳት ትክክለኛ የግል አቋሜን ዛሬ በዚህ ጽሑፍ አስቀምጣለሁ ።
.
ሆፕ ቻናል
አንደኛ ማህበራዊ ስራ በአለማውያን ሚዲያ በግልጽ መስራት የጀመርኩት እኔ አይደለሁም ከኔ በፊት እነዚህ ተሰርተዋል።
1- ዘማሪት ሀና ተክሌ  ፍትህ የተሰኘ ማህበራዊ መዝሙር በሆፕ ኢንርቴመንት
2-ዘማሪ ዳዊት ጌታቸው የዘሪቱ ከበደን ሰይፍህን አንሳ የተሰኘውን ሥራዋን ሰርቷል
ከነዚህ ሌላ አበጋዝ ሾታ የሊሊን መዝሙር አቀናብሯል
ተወልጄ ያደኩበት ቤተሰብ ወደ ኪነጥበብና ዘፈን ለመግባት በጣም የተመቻቸና ቀላል የነበረበት ነው። መንገዱንም አውቀዋለሁ ወደ ጌታ የመጣሁበት በአለም ላይ ያለ የሚገኝ ዝናና ክብርን ንቄ ነው። እኔም በዚያ ለመቀጠል ብፈልግ ኖሮ ማንም ሳይከለክለኝ አደርገው ነበር። ሆኖም ጌታ በ21 አመቴ ላይ አገኘኝ ፍቅሩ ህይወቴን ለወጠው። ከዛ ዘመን ጀምሮ አሁን እስካለሁበት ጊዜ ድረስ ዘፈን ስለ መዝፈን አስቤም አላውቅም። ወደፊትም አላስብም። የጀመርኩትም የዘፋኝነት መንገድ የተውኩት ክርስቶስ ገብቶኝ ነው። “የሰላም ሰው ነኝ” ስራ ከዝማሬ ወደ ዘፈን ለመንደርደር የተደረገ ጉዞ አይደለም። ያንን የሚያስቡ ተሳስዋል። ዘፋኝነት በዘመኔ ሁሉ ላይታሰብ፣ ለሞተልኝና ራሱን ስለ ስለ እኔ አሳልፎ በሰጠኝ ፍቅር ተማርኬ ዘመኔን ሁሉ ለእርሱ ልዘርም ራሴን በፈቃዴ ለክርስቶስ የሸጥኩ ዘማሪት የክርስቶስ ባሪያ ነኝ። ቤተክርስቲያን እንዳልዘምር ብከለከል እንኳን እነደማንኛውም ክርስቲያን ሌላ ስራ እየሰራሁ እኖራለሁ እንጂ ዘፋኝነት አይታሰብም። ከፈለኩት እኮ ከምነግራችሁ በላይ አሁን ድረስ ለኔ ሁሉም የተመቻቸ ነው።
የሰላም ሰው ነኝ ለምንና እንዴት ተሰራ?
በመሰረቱ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አንድ ክርስቲያን በኪነጥበብ ውስጥ ያለው ድርሻ (በስነ ጽሑፍ፤ በግጥም፤ በድራማና በፊልም፣ በሙዚቃ) ወዘተ በማህበረሰቡ ውስጥ ሊኖረው የሚገባ ተሳትፎን በተመለከተ የተቀመጠ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርህ የሌለ ከመሆኑም በላይ ቀዩ መስመርም አልተሰመረም። ስለዚህም በደፈናው ሁሉን ነገር “ሐጢያት ነው” በማለት ክርስቲያን ለአገሩ፤ ለማህበረሰቡ በምን መልኩ መስራት አለበት የሚለው እስከ አሁን አልተመለሰም።
ከዚህ በፊት በጥቂቱ ተናግሬያለሁ “የሰላም ሰው ነኝ” ን ስራ ስሰራ እጅግ ጸልያለሁ ለመስራት ስነሳ ደግሞ የተለያዩ ሰዎችን አማካሬያለሁ። ብዙዎቹ አበረታተውኛል። ስለዚህ የሰላም ሰው ነኝ የሚለው አስቀድመን ከወንድም ተሾመ ጋር የምሰራው “ሰላም ኢትዮጵያ” የተሰኘ ፕሮጀክት አንድ አካል የነበረ ነው። ስራውን ለመስራት ሳስብ ለብቻዬ ልሰራውን? ምን ላድርግ? የሚለውን ብዙ ጊዜ አስቤያለሁ። ምክንያቱም ሰላም ለአገራችን እጅግ አስፈላጊ ነውና። ያንን ሳስብ በአንድ የእምነት አጥር ውስጥ ብቻ የተከለለን ስራ መስራት ስራውን የሚወስነው ከመሆኑም በላይ አገሪቱ ላለችበች ጥያቄ መልስ መሆን የሚችል ነገር ላይ የራሴን አስተዋጽኦ ለማድረግ ተነሳሁ። ማህበራዊ ሐሳብ ያለው ስራን ለአገሬ ለማበርከት። ከዚያ አብረውኝ የሚሰሩ የነበሩ ቅዱሳን ይህን ስራ ከዘሪቱ ከበደ፣ ቻቺ ታደሰንና ቤቲ ጂን ከዘማሪ እስራኤል አቤል ጋር ብሰራው የበለጠ ተጽኖ እንደሚኖረው መከሩኝ እኔም በፍጹም ቅንነት ሰራሁ።
ብዙ ክርስቲያኖች ዘማሪ ሰለሆንኩ ዘፈን ከሚሰሩ ሰዎች ጋር ስላዩኝ እንደደነገጡ አስባለሁ። እኛ የሰራነውን አገራችን ስለ ሚያስፈልጋት ሰላም ለአገራችም ነው የሰራነው እንጂ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚመለክበት ዝማሬ አልሰራንም። በአንድ አገር ያለ ኦርቶዶክስ፣ ሙስሊም፣ ፕሮቴስታንት እና ሌሎችም ለአገር ጉዳይ አንድ ላይ እንደሚሰሩ እኛም ከተለያዩ ስፍራ ብንመጣም የሰራነው ስለ አገር ሰላም ነው። ሰላም ባይኖር ምንም ማድረግ አንችልም ይህ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው። ሰላም ሐይማኖት፤ ዘር ክልል ወይም ገደብ የለውም። ለሰው ልጆች ሁሉ ሰላም ያስፈልጋል። በአገር ደረጃ ሰላም ከሌለ በምንም ደረጃ እንቅስቃሴ አይኖርም። እኔ በዝማሬ የወንጌል መልዕክተኛ እንደመሆኔ፤ ለአገሬ ሰላም እጸልያለሁ፤ በማህበራዊ ተሳትፎዬ ማድረግ ያለብኝ ሁሉ አደርጋለሁ። የሰላም ሰው ነኝ ስራ ከዚያ የመነጨ ነው። አገሬን ትውልድን የሚጠቅም ማንኛውም ማህበራዊ ስራን መጽሐፍ ቅዱስ በሚለው መልኩ እሰራለሁ።
ዘፈን ሐጢያት ነው!!
ዘፈን ሐጢያት እንደሆነ ከሚያምኑ ክርስቲያኖች መሐል አንዷ ነኝ። በዋናነት አምናለሁ። ያንን ባለምን የዘፈን አለምን ትቼ አልመጣም ነበር። ያንን ያደረኩት የኢየሱስ ፍቅር እንጂ ማንም አስገድዶኝ አይደለም። ወደ ዋናው ሀሳቤ ስመለስ ዘፈን ሐጢያት ነው። ዘፈን ማለት ስለ ሰላም ስለ ፍቅር ስለ አገር አንድነት በዜማ መናገር ማለት አይደለም።
ዘፈን ማለት፦ መሴሰንን፣ ጣኦት ማምለክን፤ አመጽን፤ ሰው ማምለክን፣ ሰው ተኮር፤ ሐጢያት ተኮር፤ ግልሙትና የሚያስፋፉ፤ ጸብን የሚዘሩ ስጋዊነትን የሚያቀነቅኑ፤ በሙዚቃና በዜማ የተሰሩ ነገሮች በሙሉ ዘፈን ናቸው።የቤተክርስቲያን ወጣቶች ዘፈን መዝፈን ፈልገው ወደዘፈን አለም ቢገቡ እኔ ተወቃሽ ልሆን አይገባም። ዘፋኝ አይደለሁም አልዘፈንኩምም።
አበቃው
እኔ መዘመሬን እቀጥላለው!
 • እኛ የምንመርጠው አባትና አያቶቻችን የመረጡትን ነው።
  ከመንደር ወጥተናል።ሀገርን መርጠናል።ልካችን ሳንመርጥ የተወለድንበት ብሔራዊ ማንነታችን ሳይሆን ኢትዮጵያዊነት ነው። ኢትዮጵያዊነት ስንል ለህዝቦቿ ደህንነት እና የብሔራዊ ሠንደቅ ዓላማ ክብር ወዶ እና ፈቅዶ የመሞት ቁርጠኝነት የሚያላብስ ማንነት ነው። የእኛ ምርጫ በጊዜ ወቅት የሚገደብ፣ በውስጥና ውጭ አካል የሚታዘብ አጨቃጫቂና አከራካሪ አይደለም።በውርስ የሚተላለፍ ነው። የብሔሮችና ብሔረሰቦችን ሀገራዊ አስተዋፅኦ የምንለከው በአባት አያቶቻችን ከአእምሮ በላይContinue Reading
 • የመረጃ መንታፊዎች ዋትሳፕን እንደ ጥቃት ማድረሻ መሳሪያ እየተጠቀሙ መሆኑ ተገለጸ
  የመረጃ መንታፊዎች በቢሊየን የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች ያሉትን ዋትሳፕ የማህበራዊ የትስስር ገጽ ለአጥፊ ተልዕኮ እየተጠቀሙበት መሆኑን የበይነ መረብ ደህንነት ምርት አቅራቢው ቼክ ፖይንት ኩባንያ ገለጸ፡፡ የበይነ መረብ ደህንነት ተመራማሪዎች አዲስ አጥፊ ሶፍትዌር ያገኙ ሲሆን÷ የመረጃ መንታፊዎች በተጠቁ የዋትሳፕ የመልዕክት መቀበያዎች ቫይረስ ለማሰራጨት እየተጠቀሙ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ እንደ ቼክ ፖይንት መረጃ አደገኛ የሆኑ መተግባሪያዎችContinue Reading
 • A mother & child reunite after seven years apart
  Alferrid who left home when he was three years old goes back to his poor mum with a cow and a calf as a gift on the eve of Id Al Adha. (Part I) Alferrid Mohammed came to Addis Ababa the capital of Ethiopia when he was three years old.Continue Reading
 • ልጇን ከተገላገለች ከሰዓታት በኋላ የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰደችዉ ተማሪ
  ተማሪ ጌጤ ናደዉ ልጇን ከተገላገለች ከሰዓታት በኋላ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ለመግባት የሚያስችላትን ፈተና  ወስዳለች። ተማሪ ጌጤ ናደዉ በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ ነዋሪ  ነች። በ2010 ዓ.ም የመሰናዶ ትምህርቷን ጨርሳ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባት የሚያስችል ዉጤት  ባይመጣላትም÷ በሁኔታዎች ተስፋ ያልቆረጠችዉ ጌጤ ድጋሚ በግል ለመፈተን ቅድመ ዝግጅት አድርጋ ብትጠባበቅም ኮሮና ቫይረስContinue Reading

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   A mother & child reunite after seven years apart

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *