አቶ ዳውድ ኢብሳ ዛሬ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ። እንደ ዜናው አቶ ዳውድ እሳቸው ከሚመሩት የኦነግ ክፋይ አመራር አባላት ጋር በአንድነት በመኖሪያ ቤታቸው መግለጫ በሚሰጡበት ወቅት ነው በድንገት በቁጥጥር ስር የዋሉት። ይሁን እንጂ ከቤታቸው ወደ እስር ቤት ይወሰዱ አይወሰዱ በግልጽ አልታወቀም። መንግስትም እስካሁን ያለው ነገር የለም። አቶ ዳውድ መንግስት ቅቡልነቱ ያከተመ በመሆኑ በኦሮሚያ የሽግግር ጊዜ መንግስት እንዲቋቋም በቅርቡ ጠይቀው ነበር።

አስራ ስድስት የሚጠጉ የድርጀቱ አመራርና መግለጫውን በቀጥታ እያስተላለፉ የነበሩ የሚዲያ ሰራተኞች የፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋለበትን ምክንያት ይህ እስከታተመ ድረስ በኦፊሳል አላስታወቀም።

አቶ ዳውድ በቅርቡ መንግስት ህጋዊ ቅቡልነት ስለሌለው የአገርን ህልውና አደጋ ላይ እንደሚጥል ጠቅሰው፣ በኦሮሚያ ክልል ጊዜያዊ መንግስት እንዲቋቋም ጥሪ ማድረጋቸው አይዘነጋም። በዚሁ ጥሪያቸው በክልሉ የመንግስት መዋቅር እየፈራረሰና ህግ እየተጣሰ መሆኑን አስታውቀው በክልሉ የሚኖሩ የሌላ ብሄር አባላት ጭምር ጥሪውን እንዲደግፉ አሳስበው ነበር።

“ትህነግ መንግስት ከመስከረም በሁዋላ የለም፤ የሽግግር መንግስት ባስቸኳይ ይቋቋም” በሚል በይፋ ማወጁን ተከትሎ አቶ ዳውድ በኦሮሚያ መንግስት እንደሌለ ጠቅሰው የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ጥሪ አቅርበው ነበር። በዚሁ ጥሪያቸው በክልሉ የሚኖሩ የሌላ ብሄር አባላት ተሳታፊ እንዲሆኑ ማሳሰባቸው በስፋት መነጋገሪያ የሆነ ሲሆን አላማውና ሃሳቡ፣ ምን ለማስተላለፍ ተፈልጎ እንደሆነ ለአብዛኞች ግልጽ አልሆነም።

ከትህነግ ጋር በበርካታ ጉዳዮች በመናበብና ትህነግ በሚመራቸው ሚዲያዎች ሰፊ ሽፋን የሚሰጣቸው የኦሮሞ አክቲቪስቶች አቋም በኦሮሚያ ተወላጆች ዘንድ ክፉኛ ቁጣን የፈጠረ ጉዳይ መሆኑንን በርካታ አስተያየት ሰጪዎች እየገለጹ ነው። እንደውም በኦነግ፣ በኦፌኮና በገዢው ፓርቲ መካከል የነበረውን የመረዳዳትና የመግባባት መንፈስ የሸረሸረው ይህ ጉዳይ እንደሆነ በርካቶች ይስማማሉ። በዚህም ሳቢያ ኦሮሚያን እየመራ ያለው ኦዲፒ ድጋፍ ለማሰባሰብ እድል ከፍቶለታል።

Related stories   የኮሚሽነር አበረ ህልፈት "በነጋዴዎች" እይታና ፤ የሃኪም ትክክለኛው መረጃ " ቸልተኛነት አይተናል"

ዳውድ በኦሮሚያ ተወላጆች ላይ የማይረሳ ጠባሳ ካሳረፈው ትህነግ ጋር በድርጅቱ ሙሉ በሙሉ እውቅና የሌለው ግንኙነት መመስረታቸው ለኦነግ መሰንጠቅ ዋንኛ ምክንያት መሆኑንን ራሱን የኦነግ ወራሽ አድርጎ የሰየመውና በምክትል ሊቀመንበሩ አቶ አራርሳ ቢቂላ የሚመራው ኦነግ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

ሁለቱ አካላት በዚሁ መነሻ በጀመሩት ውዝግብ ድርጅቱ ለሁለት ተከፍሎ ሳለና የይገባኛል ጥያቄው ምላሽ ሳያገኝ አቶ ዳውድ በድርጅቱ ስም የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ያቀረብት ጥያቄና ” መንግስት ቅቡልናው አብቅቷል” ሲሉ የትህነግን አቋም በአደባባይ ማራመዳቸው አግባብ እንዳልሆነ፣ ኦነግንም እንደማይወክል አቶ አራርሳ ቢቂላ የሚመሩት ኦነግ በይፋ መቃወሙ የሚታወስ ነው።

በዛሬው እለት አቶ ዳውድ በመኖሪያ ቤታቸው እየሰጡ የነበረው መግለጫ ዓላማና ይዘት በይፋ ባይገለጽም በኦሮሚያ አጠቃላይ የተቃውሞ ጥሪ ለማስተላለፍና ሕዝብን ለመቀስቀስ እንደሆነ ለመንግስት አስቀድሞ መረጃ መድረሱን ከሌላኛው ወገን አመራሮች ዘንድ ተሰምቷል።

በአገሪቱ ዋንኛ የሆነው የፌደሬሽን ምክር ቤት በወሰነው መሰረት እስከ ቀጣይ ምርጫ አሁን በስራ ላይ ያለው መንግስት ህጋዊ ተቀባይነት እንዳለው እየታወቀ ” መንግስት ህጋዊ ቅቡልና የለውም” ሲሉ አቶ ዳውድ ጥሪ ባስተላለፉ ቅጽበት ሊከሰሱ እንደሚችሉ የህግ ባለሙያዎች አስተያየት ሰጥተው ነበር።

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ያሳሰባቸው ገለልተኛ የኦሮሞ ተወላጅና ዜጎች እንደሚሉት አቶ ዳውድ ወንበዴ ብሎ በረሃ ለበረሃ ሲያንከራትታቸው ከነበረና የኦሮሞ ህዝብ ላይ ሊረሳ የማይችል ግፍ ከፈጸመ ቡድን ጋር አብረው ለመስራት መወሰናቸው ታሪካዊ ጥፋት ነው። ይህንኑ አቋማቸውን አስተካክለው ወደ ሰላም ንግግር ቢያመሩም እንደሚመረጥ ይመክራሉ።

በኦሮሚያ የተለያዩ ፍላጎቶችና የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከቶች በመኖራቸው ሁሉም ፓርቲዎች ራሳቸውን ብቸኛ የኦሮም ወኪል አድርገው ማየታቸው ዋናው የችግሩ ቁልፍ እንደሆነ የሚጠቁሙ ወገኖች፣ ይህን አስተሳሰብ ወደሁዋላ በመተው ምርጫውን ለህዝብ ብለው ወደ ሰላማዊ መድረክ ሊመለሱ እንደሚገባ ያስጠነቅቃሉ።

Related stories   እንግሊዝ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እቅዷን ይፋ አደረገች፤ ዶክተር ዳንኤል የማይካድራን ጂኖሳይድ ዝም ማለቱ ክህደት ነው

መንግስትም ሁሉም ወገን ወደ ድርድር እንዲመጣ ሩቅ መንገድ ሊጓዝ እንደሚገባው የሚጠቁሙት እነዚህ ገለልተኛ ወገኖች ከትህነግ ጋር በማበር የሚደረግ የትግል አማራጭ ኦሮሚያን ወደ ቀውስ ከመክተት የዘለለ ውጤት እንደማያመጣ ያስጠነቅቃሉ። አያይዘውም በኦሮሚያ ሁሉም ዓይነት አስተሳሰብ እንዳለ አለማወቅ፣ ዝም ብሎ የሚመለከተውን ዜጋ አቅም ግንዛቤ ውስጥ አለማስገባት ነገ በምርጫ ዋጋ ያስከፍላል። አብዛኛው መራጭ ያለበት የኦሮሚያ ማዕከላዊ ክፍል ፍላጎትና የኑሮ ትሥሥር ሊጤን እንደሚገባው ምክር ለግሰዋል። ሁሉም ወገኖች እንደሚሉት ዛሬ ላይ ሰላማዊ ንግግር እንዲቀድም መስራቱ አማራጭና አማራጭ ነው።

ይህ ዜና እስከታተመ ድረስ አቶ ዳውድና ካቢኔያቸው በቁጥጥር ስር ውለው ወደ እስር ቤት ስለመላካቸው የመንግስት ሚዲያዎች ይፋ መግለጫ አልተሰጠም። በመኖሪያ ቤታቸው የፖሊስ ሃይል እንደተቆጣተራቸው ግን ዛጎል አረጋግጣለች። ማስተባበያም አልወጣም። በመጨረሻ ባገኘነው ዜና ትህነግ የግጭት ቀጠናዎችን ለማስፋት አቅዶ እየሰራ መሆኑን መንግስት በቂ መረጃ በማግነቱ ውሳኔው ቅድመ መከላከል ሊሆን እንደሚችል ግምት ተሰጥቷል።

 • ዶክተር አብራሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ!
  የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሃላፊ ሆነው ለስድስት ወራት በሃላፊነት የቆዩት ዶ/ር ሙሉ ነጋ በዛሬው እለት ከስልጣን መነሳታቸውን ማረጋገጥ ተችሏል። በምትካቸው ዶክተር አብራሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንትም የሆኑት ዶ/ር አብራሃም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው እየሰሩ ይገኛሉ። ዶ∕ር አብርሃም በተለያዩ የመንግስትContinue Reading
 • እኛ የምንመርጠው አባትና አያቶቻችን የመረጡትን ነው።
  ከመንደር ወጥተናል።ሀገርን መርጠናል።ልካችን ሳንመርጥ የተወለድንበት ብሔራዊ ማንነታችን ሳይሆን ኢትዮጵያዊነት ነው። ኢትዮጵያዊነት ስንል ለህዝቦቿ ደህንነት እና የብሔራዊ ሠንደቅ ዓላማ ክብር ወዶ እና ፈቅዶ የመሞት ቁርጠኝነት የሚያላብስ ማንነት ነው። የእኛ ምርጫ በጊዜ ወቅት የሚገደብ፣ በውስጥና ውጭ አካል የሚታዘብ አጨቃጫቂና አከራካሪ አይደለም።በውርስ የሚተላለፍ ነው። የብሔሮችና ብሔረሰቦችን ሀገራዊ አስተዋፅኦ የምንለከው በአባት አያቶቻችን ከአእምሮ በላይContinue Reading
 • አውሮፓ ህብረት – ላለፉት 28 ዓመታት በኢትዮያ ተላላኪ መንግስት እንደነበር ለኢትዮጵያ ህዝብ አመነ
  “የአውሮፓ ህብረት ምርጫ የማይታዘበው በበጀት እጥረት መሆኑንን ገልጾልናል” ሲሉ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ። ህብረቱ ወዲያውኑ ” በበጀት እጥረት ምክንያት ሳይሆን የቀረነው ስላልተጋበዝን ነው” ሲል ድምጹን አሰማ። ምላሽ ሰጠ። ጉዳዩ ከዚያ በላይ አልሄደም። ነገሩ ህወሃት የሚባለው አገዛዝ ቀደም ሲል የገባው ኮንትራት ነበርና ብዙም አስገራሚ እንዳልነበር በወቅቱ ብዙ ተብሎ እንደነበርContinue Reading
 • የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አገር ለማተራመስ በህቡዕ የተደራጁ በርካታ ግለሰቦችን ከነመዋቅራቸውና መስሪያዎቻቸው በቁጥጥር ስር አዋለ፤
  በተጨማሪም በውጭ በተለያዩ ሀገራት ሆነው ይህንን ህቡዕ አደረጃጀት ሲያስተባበሩ እንዲሁም የፋይናንስ፣የሃሳብና የሎጀስቲክስ ድጋፎችን ሲያደርጉ የነበሩ ፕሮፌሰር አበራ መሸሻ፣ አቶ ተሻለ ከበደ ኢዶ፣ወይዘሮ የሀረርወርቅ ጋሻው፣ አቶ አስፋው ጀቤሳ፣ አቶ መዕረግ፣ አቶ ቢኒያም፣ አቶ ኪሩቤል፣ ወይዘሪት ሊሻን አህመድ፣ ዶ/ር ገነት፣ ወይዘሮ አረጋሽ፣ ኢንጀነር ሊሻን ግዛውና አቶ ሀገሬ አዲስ በወዳጅ ሀገራት ትብበርና  ከኢንተርፖል Continue Reading

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *