በቅርቡ ከገሪቱ የተመዘበረ የዘጠኝ ቢሊዮን ብር ሙስና ወንጀል በይፋ ክስ እንደሚመሰረትበትና በሲዳማ ክልል ከአራት ሺህ በላይ ተደራጅቶ የሰለጠነ ሃይል መጨንገፉን የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራልና የወንጀል ቢሮ ሃላፊ ዘላለም መንግስቴ አስታወቁ። ኮሚሽነሩ ከሰኔው የከፋ አደጋ ጋር በተያያዘ 1105 ” ማስተር ማይንድ” ያሉዋቸው ተጠርጣሪዎች እየታደኑ መሆኑንን ይፋ አድርገዋል።

ሃላፊው ዛሬ በሰጡት መግለጫ ከአገሪቱ የተመዘበረ ከ9.4 ቢሊዮን ብር በላይ መኖሩን አመልክተዋል። እሳቸው የሚመሩት  የፌደራል ፖሊስ ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር በመሆን ምርመራ ሲያካሂድ መቆየቱን አመልክተዋል። የሕዝብና የአገር ሃብትን ከምዝበራ መከላከል የተቋማቸው ዋና ተጋባር መሆኑንን በማመልከት እንዳብራሩት በቅርቡ ከፍተኛ የሙስና ክስ በአገሪቱ ይፋ ይሆናል። የሚጠበቀው የተጠናቀቀው የምርመራ ሰነድ ብቻ ነው። ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በተያያዘ በሙስና የተጠረጠሩ ከ280 ሚሊዮን ብር በላይ መዝብረዋል በሚል በቁጥጥር ስር ውለው የፍርድ ሂደታቸውን እየተከታተሉ መሆኑንም አመልክተዋል።

በኦሮሚያ፣ በድሬደዋና በሃረሪ በሰኔ ወር የደረሰውን አስከፊ እልቂት፣ ዘረፋና፣ ውድመት ተከትሎ በፌደራልና በክልል ደረጃ 8668 ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን፣ 4249 ተጠርጣሪዎች ላይ ማስረጃ መሰባሰቡን፣ 3377 በሚሆኑት ላይ በፌደራል ደረጃ ክስ መመስረቱን ፣ ቀሪዎቹ በክልል ደረጃ የፍርድ ሂደት እየተከታተሉ መሆኑንን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። ብሁለት ወር ውስጥ ሰፊ ቁጥር ያላቸውን ተጠርጣሪዎች ጉዳይ በማየት፣ ማስረጃ በማሰባሰብና ወደ ፍርድ ሂደት እንዲዛወሩ ማድረግ ታላቅ ስራ ከመሆኑ በላይ በአገሪቱ ታሪክ እንዲህ ያለ ሰፊ የማስረጃ ማሰባሰብ ስራ ሲሰራ የመጀመሪያው መሆኑም ተመልክቷል። ማስረጃ ያልተገኘባቸው በነጻ ተለቀዋል።

Related stories   "ሬንጀርስ" የሚባል በመሳሪያ የተደገፈ ዝርፊያ የሚፈጽም የማፍያ ቅርጽ ያለው ቡድን በቁጥጥር ስር ዋለ

በመተከል በንጹሃን ግድያ አስተባባሪነት የተጠረተሩ 504 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፤ የ”ኢንቨስተሮች” እጅ አለበት


” 1105 ማስተር ማይንድ የሚባሉት” ሲሉ ኮሚሽነሩ የጠቀሷቸው አድራሻቸውን ሰውረው እስካሁን በቁጥጥር ስር አልዋሉም። አገሪቱ ብሄራዊ መታወቂያ የሌላት መሆኑ፣ ተጠርጣሪዎችሁ የተለያየ ስም መጠቀማቸውና አድራሻ መቀያየራቸው በቁጥጥር ስር እንዳይውሉ ምክንያት መሆኑንን ያወሱት የምርመራ ቢሮ ሃላፊ ዘላለም መንግስቴ፣ አሰሳው ተጠናክሮ እንደቀጠለና ሕዝብ ድጋፉን አጠናክሮ ሊሰጥ ጥሪ አሰምተዋል።

የተሰወሩት ተጠርጣሪዊች በእነ ጃዋር መሐመድ መዝገብ ክስ ከተመሰረተባቸው መካከል እንደሆኑ ሃላፊው ጠቅሰዋል። እነዚህ ክፍሎች ተልዕኮ ተሚቀበሉ፣ የሚያስፈጽሙ፣ የሚፈጽሙና የወንጀሉ ዋና አንኳር የሆኑት መሆናቸውን አመክተዋል።

በደቡብ ክልል የወላይታ የክልልነት ጥያቄ ተንተርሶ በአገሪቱ በተለያዩ የጸጥታ መዋቅር ውስጥ የነበሩና በተለያዩ ምክንያቶች ከስራቸው የተሰናበቱ ራሳቸውን አደራጅተው የዞኑንን ጸጥታ የማስከበር ስራን ከፖሊስ ነጥቀው እንደነበር ያወሱት ኮሚሽነር ጀነራሉ፣ እነዚህ ሃይሎች ልዩ የሚቀለብ ተልዕኮ ፈጻሚ ልዩ ሃይልም አደራጅተው እንደነበር ገልጸዋል።

አራት ሺህ በላይ የሚሆኑት የቀድሞ መከላከያ፣ ልዩ ሃይል፣ የክልሉ ፖሊስና የተለያዩ የጸጥታ እርከን ላይ ሲሰሩ የነበሩ ሃይሎች በኢመደበኛ አደረጃጀት ሲያካሂዱት የነበረውን ወንጀል በቁጥጥር ስር መዋሉንና ሃሳቡ መምከኑንን የገለጹት ኮሚሽነሩ፣ እነዚህን ሃይሎች ማን እንዳስታጠቃቸውና  እንዳደራጃው ስም ጠቅሰው አልገለጹም።

Related stories   ፈቃድ የሌላቸው ግለሰቦችና ተቋማት በጥምቀት በዓል ድሮን መጠቀም እንደማይችሉ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

አቶ ጌታቸው ረዳ ባልተለመደና ከዚህ በፊት በህወሃት ታሪክ ተሰምቶ በማያውቅ መልኩ በወላይታ ባህላዊ በዓል ላይ ተገኝተው ድርጅታቸው ከጎናቸው እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲናገሩ እንደነበርና በተደጋጋሚ ሲመላለሱ እንደነበር  ይታወሳል። ከዚያም በዘለለ የህወሃት ሚዲያዎች ለወላይታ የክልልነት ጥያቄ በገሃድ ሲሟገቱና አሁን ተደራጁ ለተባሉት ሃይሎች ሰፊ ሽፋን ሲሰጡ እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም። ከዚህም በላይ ህወሃት ባደራጀውና ወዲያ መቀመጫውን አዲስ አበባ በማድርገ ራሱ ከፈጠረው ህወሃት የለየው የፌደራል ሃይሎች የተባለ ስብሰብ ውስጥ የወይላታ ተወካዮች ፊት ለፊት ተዋናይ እንደነበሩ መረጃዎች ያስረዳሉ። ኦ ኤም ኤንም ከሲዳማ ቀጥሎ ሰፊ የሚዲያ ሽፋን የሚሰጣቸው ክፍሎች እንደነበሩ ቀደ ሲል የነበሩ የቅርብ ጊዜ መዛግብትና የቪዲዮ ማስረጃዎች ምስክር ናቸው።

ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ዝርዝሩን ባይናገሩም ካ”ሁን በሁዋላ መንግስት ለኢመደበኛ አደረጃጀት ፊት አይሰጥም” ካሉ በሁዋላ በቅርቡ የክልልና የፌደራል የፖሊስ ኮሚሽነሮች በዚሁ ጉዳይ ላይ አቋም መያዛቸውን ይፋ አድርገዋል።

በቅርቡ በቤኒሻንጉል ከተገደሉት አስራ ሁለት ሰዎች ውስጥ ስምንቱን ያጠፋው ተጠርጣሪ እንደተያዘ ከሃላፊው መግለጫ ለመረዳት ተችሏል። በ97 ተጠርጣሪዎች ላይ የሰነድ መረጃ መገኘቱንና 223 ምስክሮች የቀረበባቸው ተጠርጣሪዎች ጉዳይ በፍርድ አግባብ እየታየ መሆኑንን አመላክተዋል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *