መለስ የሚባለው የትህነግ መሪ አውራ በነበረበት ዘመኑ በጉራፈርዳ የደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ ” የምስራቅ ጎጃም ሰፋሪዎች” ሲል ነበር የተዛበተው። መለስ ለአማራ ያለውን ጥላቻና መነሻው የማይታወቅ “ቂም”  መደበቅ በማይችልበት ደረጃ ” አካባቢው ላይ ውድመት ያደረሱ ሰፋሪዎች” ብሎ ነበር የጠራቸው። እንዲህ ያለው ደግሞ ህዝብ በቀጥታ እየሰማ ነው። ፊልሙም፣ መረጃውም አለ።

ይህ ሁሉ ቢሆንም በ”ስትራቴጂ፡ የሚያስቡ መሪዎች የሌሉት የአማራ ሕዝብ ዛሬ ድረስ እየተጨፈጨፈ ነው። ዛሬ ድረስ እየተፈናቀለ ነው። ነገ ላለመጨፍጨፉ ዋስትና እያጣ ነው። አሁን ያለው ትውልድ በደሉ ምን እንደሆነ ሳይረጋገጥ በሄደበት ሁሉ መከራ እየተፈራረቀበት የዜና ፍጆታ ሲሆን ካድሬዎች የሚሰጡት ምላሽ፣ ራሳቸውን የአማራ ተቆርቋሪ የሚያደርጉ ክፍሎች ባዶ ቀረርቶ ህዝቡን ሊታደገው አላቻለም።

ዛሬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ በፌስቡክ ገጻቸው “… ማለቂያ የሌለው የጅምላ ጭፍጨፋ፣በገፍ መፈናቀል፣የዘመናት የልፋት ውጤት የሆነ ንብረት ውድመት የየሳምንቱ መርዶ መስማት የተለመደ እየሆነ መጥቷል።ስለሆነም ነገሩን ላለማባባስ ሲባል በዝምታ ማለፋ የሚጎዳ መሆኑን በተግባር እያየነው በመሆኑ ያገባናል ባዮች በሙሉ ልንነጋገርበት ይገባል” ሲሉ ጥቃት አድራሺዎቹን ” አንዳንድ” አንዳንድ ብለዋቸዋል።

በቤኒሻንጉል ህወሃት አደራጅቶና አሰልጥኖ እንዲሁም አስታጥቆ ጥቃት እንዳደረሰ የክልሉ መሪ በይፋ ተናግረዋል። ዛሬ ገዱ ” አንዳንድ ” ሲሉ ህዝብ እንዲያልቅ ሳይታክት የሚሰራውን ቡድን መጥራታቸው ከምን መነሻ እንደሆነ ግልጽ አይደለም። አማርኛ አጥሯቸው? ወይስ ፈርተው? ወይስ ምን? እስከመቼስ ነው ካድሬ ” አንዳንድ ያኮረፉ ሃይሎች” እያለ የሚደልለው?

የሶማሌ ክልል መሪ ሙስጣፌ የኦጋዴን ነጻ አውጪ የሆኑ መታሰራቸውን ተከትሎ ተጠይቀው ” ከንግዲህ ወዲህ በሶማሌ ክልል ውስጥ የሽብር ጥቃት እፈጽማለሁ ብሎ ማሰብ አይቻልም። ሰላማዊ ትግል ሲፈቀድ ጠመንጃ ማስረከብ ብቻ ሳይሆን፣ ሃሳባችሁንም ጭምር እንድትቀየሩ ነው” በማለት መናገራቸውን ስነሰማ ማን ነው ለአማራ ክልል እንደዚህ የሚልለት ብለን ለመጠየቅ እንገደዳለን።

ህወሃት ከየስፍራው ለቃቅሞ እንዳሻው ኮትኩቶ ያሳደጋቸው ካድሬዎች የሙስጣፌን አይነት ወግ ሲጠበቅባቸው ዛሬም በቀድሞው ልቡናቸው የሚያስቡ ይመስላሉ። ጎልጉል እንዳለው ምንም እንኳን አማራውን ነካክቶ እልህ ውስጥ በማስገባት ጠብመንጃ እንዲያነሳ ታቅዶ እንደሚሰራ ቢታወቅም ገዱ “ብስትራቴጂ እናስብ” ምናምን የሚለው ጥሪ ለማን እንደሆነ ግልጽ አይደለም። ለምንም ሃሳባቸውን ማሽሞንሞን እንደፈለጉ ምክንያት የላቸውም። ይልቁኑም ተራ የካድሬ ቀረርቶ ካልሆነ በቀር።

አሮጌ ስልቻ አዲሱን ሃሳብ እንደማይችል ቢታወቅም፣ ህወሃት ሆን ብሎ ተተኪ ድርጅትና ተፎካካሪ አቅም እንዳይፈጠርና አገሪቱም ሆነ ክልሎች አማራጭ እንዳይኖራቸው አድርጎ ቢያልፍም፣ እዛው ባለበት የ18ኛው ክፍለዘመን እሳቤው ላይ ተቸክሎ ” ጭሬ ላፍሰው” ፖለቲካው እየሰራ ያለው እየታወቀ አቋም ወስዶ ” እነሱም አረፉ እኛም አረፍን” የሚባልበትን ዘመን አፍጥኖ ከማምጣት ይልቅ ” መክረን” የሚለው አካሄድ የላላ ይሆናል። ለዚህም ነው በርካቶች አስተያየታቸውን ያቃለሉት። መለስ ያላገጠበት የጉራ ፈርዳ የቀደመው ግፍ እንዲህ ይታወሳል።

Related stories   የ80ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን በአዲስ አበባ ተከበረ

የአንደኛ ክፍል ተማሪ ከውቅቱ የደቡብ ክልል መሪ ሽፈራው ሽጉጤ በተጻፈና መተፈረመ ደብዳቤ ” ክልላችንን ለቀህ ውጣ” ተብሎ ነበር። የዚህ ሪፖርት አቅራቢ ይህን ደብዳቤ አግኝቶ ሪፖርት ማድረጉን ያስታውሳል። እውን መሪ ቢኖር ለአንደኛ ክፍል ተማሪ ደብዳቤ ጽፎ ” ውጣ ከክልላችን” ያለን አመራር በቅጽበት ለፍርድ ባቀረበ ነበር። ዳሩ ክልሉ ላይ እንደ ኮሶ ተጣብተው ይነግዱ ለነበሩ የመለስ ጭፍራዎች ሽፈራው ቀኝ እጅ ስለነበር ማን ነክቶት!! የሚያሳዝነው ይኸው ሰው ለጠቅላይ ሚኒስትርነት በህወሃት በኩል መታጨቱ ነው። ከዛም በላይ አሁን ድረስ አምባሳደር ሆኖ መቀጠሉ ነው። ከሌብነቱ በላይ የግፍ ተወናይ መሆኑንን ማሰብ ያማል።

ሽፈራው ሽጉጤን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ለውጡን እንደገና በአዲስ በቅሎ ሊሰግርበት የነበረው ትህነግ ፣ ያሰበው ባይሳካም ከሽፈራው ጋር አብረው እየሰሩ ላለመሆናቸው ማረጋገጫ የለም። እሱ ብቻ ሳይሆን ” ያልተቆረጠው የትህንግ የስለላ መዋቅር” በዞንና በወረዳ አልፎም ቀበሌ ድረስ ባለው ግንኙነት አገር እያመሰ መሆኑንን በቅርቡ ዘገበን ነበር። ይህንን ያንብቡ ያልተቆረጠው የጌታቸው አሰፋ እጅ – የትህነግ አንጋፋ አመራሮች መታገት – ሳምሶን አዳነ

በመተከል በተደጋጋሚ፣አሁን ደግሞ በጉራፈርዳ አማራ እየተመረጠ ለምን ይጨፈጨፋል? ጎልጉል የሚሰኘው የድረ ገጽ ጋዜጣ የትህነግ አዲሱ ሤራ – አማራን በውክልና እልህ ውስጥ መክተት  በሚል ዕርዕስ ” ስብሃት ነጋ የሚባለው የትህነግ (ህወሃት) ማፊያ ቡድን አውራ ገና ወደ በረሃ ከመግባቱ በፊት አዲስ አበባ ፒያሳ ከገብረ ትንሳኤ ኬክ ቤት ዝቅ ብሎ ፍሎሪዳ ቡና ቤት መጠጥ ጠግቦ ሲወጣ ሽንት ያዘው። ከዚያም ከፍሎሪዳ እንደወጣ ያለው አደባባይ ላይ ለመሽናት አብሮት ከነበረው ባልደረባው ጋር በመሆን በሞቅታ እያወጋ ተጠጋ። አደባባዩ ላይ ሲሸና እየገለፈጠ “አማራ ላይ እንሽና” ማለቱን በወቅቱ አብሮት ከነበረው ሰው በጀብድ ሲወራ መስማቱን የመረጃ ምንጫችን ይናገራል ” በሚል መግቢያውን ካስነበበ በሁዋላ

በዚሁ ግምገማ መሠረት የትህነግ ኃላፊዎች በስብሃት ነጋ መሪነት ባደረጉት ግምገማ “አማራው ክልል ሰላም መሆኑ ዕቅዳችን እንዳይሳካ አድርጓል” የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል። እንደ መፍትሄ ያቀረቡት ይህን ከጅምሩ ሊያጠፉት በመታገያ ደብተራቸው ላይ በጠላትነት የፈረጁትን ሕዝብ በግድያ፣ በጥቃት፣ በትንኮሳ፣ ወዘተ ትዕግስቱ እንዲያልቅ ማድረግ ነው። ትዕግስቱ ሲያልቅና በተለይ በማንነቴ ላይ የተቃጣውን እመክታለሁ በማለት ወደ ኃይል ርምጃ ሲገባ አገሪቱ ትተራመሳለች። ስለዚህም ይህ ይሆን ዘንድ ምን መደረግ አለበት ተብሎ አዲስ ዕቅድ በማፊያው ቡድን ህወሃት ተነድፏል።

አሁን ባለው ትኩስ መረጃ በጉርዳ ፈርዳ ሰላሳ አንድ የአማራ ተወላጆች ተጭፍጭፈዋል። በገጀራ ተቆራጠው የተገደሉ አሉ። አይነ ሰውርና ነፍሰጡር እህቶች ተመርጠው ተገድለዋል። ለሁለት ተከታታይ ቀናት ነው ጭፍጨፋው የተካሄደው። 2635 ሰዎች ቀዬያቸውን ለቀው በሽሽት ለማኝ ሆነዋል።

Related stories   በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 110 ሺህ ዶላር ተያዘ

ይህንኑ ተከትሎ የፈረደበት የአገር መከላከያ ሰራዊት ፈጥኖ ደርሶ ሁኔታውን የተቆጣጠረ ሲሆን፣ ፖሊስና የአካባቢው አመራሮች በጉዳይ እጃቸው አለባቸው ተብሎ ሃያ አንድ የሚሆኑ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ኤታማዦር ሹሙ እርምጃ እንደሚወሰድ በገሃድ ተናግረዋል። አፈ ጉቤውም በተመሳሳይ እገር ለመበተን ጸብ በሚዘሩ ላይ ምህረት የሌለው እርምጃ ተግባራዊ ይሆናል ብለዋል። ቀደም ሲል ታጣቂ የነበሩ ሚሊሻዎች ትጥቅ እየፈቱ ነው። አዲስ የሚሊሻ አስተዳደር እንደሚቋቋምም ተወስቷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ይህን ተከትሎ በፌስ ቡክ ገጻቸው የትእግስትም ልክ አለው አይነት መልዕክት አስፍረዋል።  ከጥቅምት እስከ ጥቅምት ያለው አንድ አመት ብቻ በግልፅ የሚነግረን ግፍና መከራው ተጠክሮ መቀጠሉን ነው። ማለቂያ የሌለው የጅምላ ጭፍጨፋ፣በገፍ መፈናቀል፣የዘመናት የልፋት ውጤት የሆነ ንብረት ውድመት የየሳምንቱ መርዶ መስማት የተለመደ እየሆነ መጥቷል።ስለሆነም ነገሩን ላለማባባስ ሲባል በዝምታ ማለፋ የሚጎዳ መሆኑን በተግባር እያየነው በመሆኑ ያገባናል ባዮች በሙሉ ልንነጋገርበት ይገባል። ሙሉ ሃሳባቸው ከስር ያንብቡ   

ዛሬም በጉራ ፈርዳ…
የአማራ ህዝብ ለፍትህ፣ለነፃነት እና ለአብሮነት ሲታገል ቢኖርም እስካሁን በኢትዮጵያ አስተማማኝ ሰላም፣ፍትህና የህግ የበላይነት ሰፍኖ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በየትኛውም የአገራችን ክፍል በሰላም ፣ በነፃነት እና በደስታ መኖር የሚቻልባት አገር ባለቤት መሆን አልተቻለም።ይልቁንም ከጊዜ ወደ ጊዜ ግፍና መከራው አየተጠናከረ በአሰቃቂ ሁኔታ መጨፍጨፋና በገፍ መፈናቀሉ ተስፋፍቶ ቀጥሏል።
ይህንን ሁኔታ ለመረዳት ብዙም ሩቅ ሳንሄድ ይህንን አንድ አመት ብቻ ወስዶ አዝማሚያውን መገምገሙ ብቻ በቂ ነው።ከጥቅምት እስከ ጥቅምት ያለው አንድ አመት ብቻ በግልፅ የሚነግረን ግፍና መከራው ተጠክሮ መቀጠሉን ነው። ማለቂያ የሌለው የጅምላ ጭፍጨፋ፣በገፍ መፈናቀል፣የዘመናት የልፋት ውጤት የሆነ ንብረት ውድመት የየሳምንቱ መርዶ መስማት የተለመደ እየሆነ መጥቷል።ስለሆነም ነገሩን ላለማባባስ ሲባል በዝምታ ማለፋ የሚጎዳ መሆኑን በተግባር እያየነው በመሆኑ ያገባናል ባዮች በሙሉ ልንነጋገርበት ይገባል።
ይህ በአማራ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እየተፈፀመ ያለው በማንም ህዝብ ሳይሆን በጥቂት ቡድኖችና ግለሰቦች ሴራ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉንም የኢትዮጵያ ህዝብ በአጋርነት የሚያሰልፍ የትግል አቅጣጫ ነድፎና ስትራቴጅያዊ ግብ ወስኖ በጋራ መንቀሳቀስ ጊዜ ሊሰጠው አይገባም። በክስተት ላይ ያነጣጠረ ጩኸት አልቃሻ ከማድረግ የዘለለ ጥቅም የለውምና።
ሕዝብን እንደ ጠላት ፈርጆ ዘመቻ የሚያቀናብር ሃይል ማንም ይሁን ማን በቃህ ሊባል ይገባል። ሕዝብ በሰሜንም በደቡብም መሮታል። ሕዝብ ግፍ ጠግቧል። ሕዝብ መንገዱን የሚያሳየው ካገኘ መላውን እንዴት እንደሚፈልግ ያውቃል። ዛሬ ይህ ሳይሰማ አማራ እየተመረጠ ጥቃት እንደሚደርስበት ተሰምቷል። መረጃ አስቀድሞ ይፋ ሆኗል። መንግስትም ሆነ ክልል የት ናቸው? የሞት አዋጅ መስማት ተለመደ። ድሃ መጨፍጨፍና ማፈናቀል ንግድ ሆነ። አፈናቃዮቹ ያገሳሉ። ተፈናቃዮቹ ያነባሉ። ቅጥረኞቹ አይነስውር፣ ነፍሰጡር፣ ህጻን ሳይለዩ ይገላሉ። ካድሬዎች ” አንዳንድ ያኮረፉ ሃይሎች” ይላሉ። እስከመቼ?

 

 • ሀገሪቷን ከጥፋት ለመከላከል ፣ ህግን ለማስከበር ፌዴራል ፖሊስ ተግባሩን ያጠናክራል
  ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ሀገሪቷን ከጥፋት ለመከላከል ፣ ህግን ለማስከበር በጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል በ19ኛ ዙር ያሰለጠናቸው 6 ሺህ 431 የፖሊስ አባላት መመረቃቸው ተመላክቷል፡፡ ከተመራቂዎቹ መካከል 792 የሚሆኑት የአፋር ክልል ልዩ ኃይል አባላት መሆናቸውም ተገልጿል። በምረቃ ስነ ስርዓቱ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍContinue Reading
 • Congolese President Presents Initiative to Resolve GERD Dispute
  Congolese President and current chair of the African Union Felix Tshisekedi presented an initiative to resolve Ethiopia’s dispute with Egypt and Sudan on the Grand Ethiopian Renaissance Dam. The initiative was announced by Tshisekedi during his talks with the Head of Sudan’s Transitional Sovereign Council Abdel Fattah al-Burhan and Sudan’sContinue Reading
 • US Special Envoy Donald Booth arrives in Juba today
  The United States Department of State has said in a press release yesterday that the US Special Envoy Donald Booth will arrive in Juba today May 8, 2021. “U.S. Special Envoy for Sudan and South Sudan Donald Booth will travel to South Sudan from May 9 to May 13, 2021.Continue Reading
 • SSOMA boycotts Rome talks due to killing of rebel commander
  The South Sudan Opposition Movements Alliance (SSOMA) affiliated with Gen. Thomas Cirillo have said that they were going to boycott the Rome peace talks which were slated to commence May 8, 2021. A statement by SSOMA seen by Radio Tamazuj over the weekend read in part, “SSOMA would like toContinue Reading

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *