“Our true nationality is mankind.”H.G.

መንግስት ሆይ!! “አሜሪካ ጦርነት አወጀችብኝ” ብለህ በይፋ አውግዝ! ለዓለም አውጅ

ኢትዮጵያዊያን በአሜሪካ ምርጫ የበኩላችሁን አድርጉ። መንግስት ይህን የጦርነት አዋጅ ለተባበሩት መንግስታትና ለወዳጅ አገሮች እንዲሁም ለመላው ዓለም ዛሬ ነገ ሳትል አሳውቅ። አትልመጥመጥ። ችግርን ወደ መልካም አጋጣሚ መለወጥ ይቻላልና እንደ ሕዝብ እኛም አንድ እንሁን። ባንዳዎችን በየመንደራችን እንመክት።

የኢትዮጵያ መንግስት ለፕሬዚዳንት ትራምፕ የጦርነት አዋጅ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አማካይነት የሰጠው ምላሽ ደረጃውን ያልጠበቀና በሚፈለገው ደረጃ ዓለም ድርጊቱን እንዲያወግዝ የጠየቀ አይደልም። ጉዳዩ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚጥስና የጦርነት አዋጅ በመሆኑ ሆኖ ሳለ ምላሹ የተልፈሰፈሰና በቀጥታ አዋጁን የሚኮንን አይደለም። ከዚህ አንጻር መንግስት የጠነከረ አቋሙን ሊያሳይ ግድ ይላል።

ይኽ እብሪተኛ ቢናገረውም ትርጉሙ አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ማወጇን የሚያረጋግጥ ነው። ” ግብጽ ግድቡን ታወድመዋለች” ማለት በሎጅስቲክ መርዳትን ጨምሮ ለግብጽ እውቅና መስጠት ነው። ይህ ብቻ አይደለም ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት መስራችና ሉዓላዊነቷ የተጠበቀ አገር እንደመሆኗ የዓለም አቀፉን ህግ መጣስም ነው። ከድህነት ለመውጣት የሚፍጨረጨሩ ህዝቦችን መናቅና ሃብታቸውን በፍትሃዊ መንገድ እንዳይጠቀሙ በሃይል ማገድ በመሆኑ ተቀባይነት እንደሌለው ዓለም እንዲያውቀው መደረግ አለበት። 

Related stories   “…ለዛሬ ብለን ነገን ከምናበላሽ፣ ለነገ ስንል ዛሬን እንሠዋ” አብይ አህመድ

ትራምፕ አምልጦት ሚስጥሩን አስታወከው እንጂ መንግስት አስቀድሞ መረጃ ስላለው የህዳሴውን ግድብ ከአገር ውስጥ ባንዶችና ከግብጽ ጥቃት ለመጠበቅ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ሲያስታውቅ በግድቡ የአየር ክልል በረራ መታቀቡን፣ ወደ ግድቡ የሚጠጋ ማንኛውም በራሪ አካል እንደሚመታ፣ ይህን የማድረግ ሙሉ ቁመና እንዳለ፣ መከላከያና አየር ሃይል እንቅልፍ እንደማይተኙ፣ የአየር ክልላችን ፍጹም አስተማማኝ ጥበቃ እንደሚደረግለት ለሕዝብ ማስተማመኛ መስጠቱ የሚያኮራ መሆኑንን ለመግለጽ እንወዳለን።

Related stories   ወደ ድርደር ? ከታንክ ወደ አህያ የወረደው ትህንግ በማን ሊወከል?

ይህ የመሪ ሞገስ የሌለው ትፋታም ብር ከመከልከል ውጭ ምንም የሚያደርገው ነገር የለም። እሱንም አድርጎታል። ወደፊትም ልማታችንን አቁመን ለእሱ ካልታዘዝን ድጋፉ እንደማይኖር አረጋግጧል። ከዚህ በሁዋላ ምን የሚያስፈራ ነገር አለ? ምን ሊከለክለን ይችላል ብለን እንሰጋለን?

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የሰጠው ጥቅልል ምላሽ ከታሪክ አንጻር ኢትዮጵያን በክፉ ቀን የከዱ መኖራቸውን አውስቷል። አዎ! አሜሪካ በሶማሌ ወረራ ወቅት ክዳናለች። ወያኔ የሚባል የሽፍታ ቡድን አገራችን ላይ ነግሶ እንዲፈረካክሰን አድርጋለች። ዛሬም ከግብጽ ጋር ሆና ከድህነት ለመውጣት በራሳችን ሃብት፣ ማንንም ሳንጎዳ የምንገነባውን ግድብ እንዳንጨርስ ጦርነት አውጃለች።

Related stories   ትህነግን በብሄራዊ ውይይት እንዲሳተፍ የሚደረግ ግፊት መኖሩን መንግስት ይፋ አደረገ፤ " ፍጹም ተቀባይነት የለውም" ብሏል

አሜሪካ በታሪኳ ወራዳ መሪ ሰይማ በይፋ ጦርነት አውጃብናለች። ይህ ጦርነት በሎጂስቲክም ሆነ እውቅና በመስጠት ረገድ ታላቅ ወንጀል ነውና አገር ወዳዶች በያለንበት እንስራ። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እንዳለው ለወራሪና ለባንዳ እንዲሁም ለሃያላን ተንበርክከን አናውቅም። ወደፊትም አይሆንም። ይህ ትውልድ የቀደመውን ገድል ያድሳል። መንግስት ሆይ አሜሪካ ጦርነት አውጃለችና በግልጽ ” ጦርነት ታወጀብኝ” ብለህ አውግዝ!!

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0