“Our true nationality is mankind.”H.G.

“ሰልፉን ክልሉን ለማተራመስ ጠላት ሊጠቀምበት መዘጋጀቱ ተደርሶባታል፤ ለጠላት ዱላ አታቀብሉ”

የአማራ ክልል ለጸጥታ ሃይሉ ትዕዛዝ አስተላለፈ፤ “ሰልፉን ክልሉን ለማተራመስ ጠላት ሊጠቀምበት መዘጋጀቱ ተደርሶባታል”

አብን በአማራ ክልልና አማራ በሚገኝባቸው ሌሎች አካባቢዎች ሰላማዊ ሰልፍ እንዲካሄድ ያስተላለፈው ጥሪ ህገወጥ በመሆኑ ማንኛውም ዜጋ እንዳይሳተፍ የአማራ ክልል አሳሰበ። ማሳሰቢያውን ጥሰው በሚገኙ ላይ የጸጥታ ሃይሉ አስፈላጊውን ሰላም የማስከበር እርምጃ እንዲወስድ ታዘዘ።

“ከመስከረም 25 በሁዋላ መንግስት የለም” በሚል ሂሳብ በመላው አገሪቱ ተዘርግቶ የነበረው መንግስትን በሃይል የማስወገድ እቅድ የከሸፈው “የአማራ ክልል ሰላም በመሆኑ ነው” በሚል ትህነግ ግምገማውን ባደረገ ማግስት አብን ይህንን ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱ አነጋጋሪ ሆኗል።

አብን አማራ እየተለየ የሚደርስበት ጭፍጨፋ ልኩን በማለፉ ድምጽ ለማሰማት ሰላማዊ ሰልፍ ማዘጋጀቱን፣ ሰልፉም ጥቅምት 18 ቀን 2013 እንደሚካሄድ መውሰኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ይፋ አድርጓል። ለክልሉም ሆነ ሰልፍ እንዲደረግ በሚፈለግባቸው ቦታዎች ላሉ የአስተዳደር አካላት የማሳወቂያ ደብዳቤ ማሰራጨቱን አመልክቷል። በዚህ መነሻ መሰረት ሰልፉ የሞት ሽረት አይነት እንደሆነ በተደጋጋሚ እየገጸ ነው።

የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ እንደሚሉት ሰልፉ አሁን ላይ አስፈላጊ አይደለም። እንደውም ለጠላት ዱላ የማቀበል ያህል ነው።

Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤

ከክልሉ ውጪ የሚኖሩ የአማራ ተወልጆችን ከሚኖሩበት አካባቢ ህበርተሰብ ጋር የሚያጋጭ ሰላማዊ ሰልፍ መጠራቱ በበርካቶች ዘንድ ጥያቄ የፈጠረ ጉዳይ ሆኗል። ዓላማውም ግልጽ ያልሆነላቸው ክፍሎች “ በየቦታው ተበትኖ በሰላም እያኖረ ያለውን ምስኪን ህዝብ ጣጣ እንዳይመጣበት ፈርተናል” ሲሉም እየተደመጡ ነው።

በመቂ የሚኖረው የ39 ዓመቱ ገረመው ለዛጎል “ ጥሪው አስገራሚ ነው” ሲል ይጀምራል። እሱ ባለበት አካባቢ አንዳችም ችግር ሰምቶና አይቶ ስለማያውቅ ምን ብሎ እንደሚሰለፍ ይጠይቃል። እርግጥ በተለያዩ ቦታዎች ለማመን የሚከብዱ ዜናዎች አማራው ላይ መፈጸማቸውን መስማት ቢያምም፣ በጩኸት የሚሆን ነገር ስለማይኖር በር ዘገቶ መላ መፍለግና መተጋገዝ ብቻ መፍትሄ እንደሚሆን ያስባል። ከዚህ ውጪ ተጨማሪ ጠላት መፍጠርና ለጠላት መመቸት አግባብ መስሎ እንደማይታየው ይገልጻል።

ስለፉ ህገወጥ መሆኑንና በአሁኑ ወቅት የሚያመጣው ለውጥ እንደሌለ በዝርዝር ጠቅሶ የክልሉ መንግስት ቢያስታውቅም “ሰልፉን ከማድረግ መንግስትም ይሁን ሌላ አካል ማንም ሊያስቆመን አይችልም ለዚህ መክፈል ያለብንን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን።” ሲሉ የአብን የህዝብ ግንኙነት ጉዳዮች ኋላፊ አቶ ጧሂር መሃመድ ለሸገር ዛሬ ማለዳ ተናግረዋል።

አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ግን የሰልፉን መከልከል ሲያስረዱ “ ሰላማዊ ሰልፍ መፍትሄ የሚያመጣ ቢሆን እኛም አስተባብረን አብረን እንሰለፍ ነበር” ካሉ በሁዋላ ስለፉ ሌሎች ክልል የሚኖር ወገኖቻችንን ይጎዳል በማለት በግርድፉ ገልጸዋል። ሆን ብለው ያላብራሩት ይህ ጉዳይ የበርካቶች ስጋት ነው። ችግር ከተፈጠረም የመጨረሻው እሳት ይሆናል።

Related stories   ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ማጣራቱ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን እንደሚያካትት አስታወቀ፤ መንግስትና አማራ ክልል በማይካድራ ጉዳይ ተኝተዋል

ሌላው ችግር ከአባይ ግድብ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሻቸው ጉዳዮች መኖራቸውን እንደ ምክንያት ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚንስትር አብይ በቢኒሻንጉል ክልል የተከፈተው የውክልና ጦርነት በቀጥታ ግድቡን ከማስተጓጎልና መንገድ ከማቋረጥ ጋር የተያያዘ እንደሆነ መግለጻቸው ይታወሳል። የክልሉ መሪም ይህንን ሁሉ ጦርነትና ማተራመስ የሚያቀነባበረው፣ የሚያደራጀው፣ የሚያስለጥነውና የሚያስታጥቀው ትህነግ የሚባለው የወንበዴዎች ቡድን እንደሆነ በመረጃ መረጋገጡን አስታውቀዋል።

አቶ ግዛቸው ሌላ ያነሱት ትልቁ ጉዳይ ሰልፉን የአማራ ክልልን ለማተራመስ የመጠቀም እቅድ እንዳለ መረጃ መገነቱን ነው። “ ለጠላት ዱላ እንደማቀበል ነው” ሲሉ የገለጹት ክልሉን የማተራመስ እቅድ አገሪቱን ባጠቃላይ ለመበተን ከተወጠነው እቅድ የተቀዳ ማስፈጸሚያ መሆኑንን ነው የገለጹት። ይህ ንግግራቸው ጎልጉል የድረገ ገጽ ጋዜጣ የአማራ ክልል ሰላም መሆን ለትህነግ መንግስትን የማስወገድ ሴራ እንቅፋት መሆኑ ተገመገመ በሚል ዕርዕስ ካወጣው ቁልፍ መረጃ ጋር የሚስማማ ሆኖ ተገኝቷል።

ዛሬ የውጭና የውስጥ ባንዳዎች መልካቸውን እየቀያየሩ የሚፈጽሙት ጥቃት ህዝብረትና አንድነት በሚጠይቅበት፣ ፍጹም ጥበበና ማስተዋል በሚፈለገበት አሳሳቢ ጊዜ በመላው አገሪቱ የሚኖሩ አማሮች ስለማዊ ስለፍ እንዲወጡ ጥሪ ማስተላለፍ አብን ምን አልባትም ከአፈጣጠሩ ጋር የሚነሳበትን ሃሜት ግልጽ የሚያሳይ ስለመሆን አስተያየት እየተሰጠ ነው።

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0