ልዑካናቸውን በመያዝ ወደ ኢትዮጵያ አቅንተው የነበሩት አውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ እና ደህንነት ፖሊሲ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆሴፕ ቦረል ፎንትለስ ባለፉት ሶስት ሳምንታት ውስጥ ትግራይ ክልል እንዳልሄዱ ተቀማጭነታቸው አውሮፓ የሆነ ዲፕሎማት ለዛጎል ተናገሩ። ዲፕሎማቱ ይህንን ያሉት ሪፖርተር ዛሬ ምንጮች ነገሩኝ በማለት ” የኅብረቱ ከፍተኛ ልዑካን ወደ ትግራይ ክልልም በማምራት፣ ከክልሉ መንግሥት አመራሮች፣ እንዲሁም ከደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ጋር መወያየታቸውን ለማወቅ ተችሏል” በማለት መዘገቡን ተከትሎ ነው።

ሆኔፕ ቦረል ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር በምስራቅ አፍሪቃ የጸጥታ ጉዳዮች መምከራቸው ሚስጢር እንዳልሆነና በውቅቱ የተገለጸ ጉዳይ እንደነበር ያመለከቱት ዲፕሎማት፣ ከጉብኝቱ ሶስት ሳምንት በሁዋላ ድርድር ስለመካሄዱ መግለጽ የተፈለገበት ምክንያት ” ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ እንጂ ሌላ ምክንያት የለውም” ብለዋል። ዜናው እንዲህ ያለ ትልቅ ጉዳይን የሚመለከታቸውን አካላት አለማካተቱንም አግባብ እንዳልሆነ አመላክተዋል።

አቶ ጌታቸው በአካል ተገናኝተው ከህወሃት አመራሮች ጋር ምክክር መደረጉንና ማብራሪያ መስጠታቸውን ለሪፖርተር መናገራቸው እጅግ እንዳስገረማቸው ያስታወቁት ዲፕሎማት በግል ችግሮች በውይይት ቢፈቱ ፍላጎታቸው መሆኑንን አልሸሸጉም። ይሁን እንጂ እንዲህ ባለው አግባብ የሚመጣ ለውጥ የለም።

ሆሴፕ ቦረል ፎንትለስ ትግራይ ክልል ሄደው ቢሆን ኖሮ የትግራይ ጉዳይ ላይ የሚሰሩ ሚዲያዎችና የማህበራዊ ገጽ አቀንቃኞች ለዜናው ቅርብ ይሆኑ እንደነበር ያመለከቱት ዲፕሎማት፣ ያ ሆኖ ከሆነ ዜናው አዲስ ግኝት ሊሆንም አይችልም ነበር ብለዋል። ሆሴፕ በይፋ እንደተገለጸው በስማሌ ክልል ብቻ ነው ጉብኝት ያደረጉት። የዚህም ምክንያት ግልጽ ሲሆን እሳቸው ራሳቸው ይህንኑ አስመክተው በአንደበታቸው ስለ ጉብኝታቸው ይፋ አድርገዋል። በዛን ወቅት ወደ ትግራይ ከነልዑክ ቡድናቸው ማምራታቸውን ግን ፍንጭ አልሰጡም።

Related stories   እንግሊዝ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እቅዷን ይፋ አደረገች፤ ዶክተር ዳንኤል የማይካድራን ጂኖሳይድ ዝም ማለቱ ክህደት ነው

በተደጋጋሚ አሜሪካ ምክር መለገሷን ያመለከቱት ዲፕሎማቱ፣ ህወሃት የአገር ውስጥ ሽማግሌዎችን ከገፋ በሁዋላ ምንም አይነት የንግግር መድረክ እንዳልተካሄደ ሙሉ በረጃ እንዳላቸው፣ እሳቸው በተመደቡበት የስራ ሃላፊነት የውጭ አገር፣ በተለይም አውሮፓ ህብረት አካባቢ እንዲህ ያለ ሃሳብ ካለ አስቀድመው እንደሚያውቁ ለዛጎል አብራርተዋል።

ዲፕሎማቱ እንዳሉት ከሆነ የሰላም ንግግር ማንም ያድርገው ማን የሚደገፍና ሰላምን እስካመጣ ድረስ ሊበረታታ ይገባል። መንግስታቸው ለውይይት ሁሌም ዝግጁ ነው። በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል እንደ ማንኛውም ክልል የራሱን ድርሻ ሊጫወት ሲገባው ከሌሎች ክልሎች በተለየ ማግኘት መፈለጉና ተጽዕኖ ለማድረግ መመኘቱ ችግሩን እንዳሰፋው እግረ መንገዳቸውን ጠቅሰዋል።

ዜናው ያካተተው አቶ ጌታቸው ረዳን ብቻ ነው። የአውሮፓው ልዑክ ትግራይ መሂዱንና ማብራሪያ እንደተደረገለት፣ ቀታይ ውይይት እንደሚኖር ማረጋገጫ በመስጠት ምስክር ከሆኑት አቶ ጌታቸው ጎን ለጎን አዲስ አበባ ትልቅ ቢሮ ያለው የአውሮፓ ህብረት፣ ለሚዲያዎች በራቸው ክፍት እንደሆነ የሚነገርላቸው የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤትና የብልጽግና ፓርቲ ድምጽ በዜናው አልተካተተም። ወይም ከተጠቀሱት አካላት መረጃ ለማግኘት መሞከሩ አልተጠቆመም።

ህወሃት የመደራደሪያ አቅም በመግንባት ታላላቅ አገራት ጣልቃ እንደገቡ ለማሳየት ፕሮፕጋንዳ ዜናውን እንደሚጠቀምበትና እንደሚፈልገው አስተያየት  የሰጡ ገልጸዋል። በዛጎል የአዲስ አበባ ተባባሪ አማካይነት አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን ምን አልባት በቪዲዮ ኮንፍራንስ ከህወሃት ሰዎች ጋር ንግግር ተደርጎ ከሆነ አንደማያውቁ፣ ከዚህ ውጭ ግን የአውሮፓ ባለስልጣናት ከሶስት ሳምንት በፊት ወደ ትግራይ ክልል አለማምራታቸውን ገልጸዋል።

Related stories   የኢትዮጵያ “ትንሣኤዋን እውነተኛ ልጆቿ እንጂ ጠላቶቿ ወዲያው አያዩትም” ተመስገን ትሩነህ

 

 

 

 

 • ዶክተር አብራሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ!
  የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሃላፊ ሆነው ለስድስት ወራት በሃላፊነት የቆዩት ዶ/ር ሙሉ ነጋ በዛሬው እለት ከስልጣን መነሳታቸውን ማረጋገጥ ተችሏል። በምትካቸው ዶክተር አብራሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንትም የሆኑት ዶ/ር አብራሃም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው እየሰሩ ይገኛሉ። ዶ∕ር አብርሃም በተለያዩ የመንግስትContinue Reading
 • የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አገር ለማተራመስ በህቡዕ የተደራጁ በርካታ ግለሰቦችን ከነመዋቅራቸውና መስሪያዎቻቸው በቁጥጥር ስር አዋለ፤
  በተጨማሪም በውጭ በተለያዩ ሀገራት ሆነው ይህንን ህቡዕ አደረጃጀት ሲያስተባበሩ እንዲሁም የፋይናንስ፣የሃሳብና የሎጀስቲክስ ድጋፎችን ሲያደርጉ የነበሩ ፕሮፌሰር አበራ መሸሻ፣ አቶ ተሻለ ከበደ ኢዶ፣ወይዘሮ የሀረርወርቅ ጋሻው፣ አቶ አስፋው ጀቤሳ፣ አቶ መዕረግ፣ አቶ ቢኒያም፣ አቶ ኪሩቤል፣ ወይዘሪት ሊሻን አህመድ፣ ዶ/ር ገነት፣ ወይዘሮ አረጋሽ፣ ኢንጀነር ሊሻን ግዛውና አቶ ሀገሬ አዲስ በወዳጅ ሀገራት ትብበርና  ከኢንተርፖል Continue Reading
 • የ80ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን በአዲስ አበባ ተከበረ
  በበዓሉ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ የደረሰችው አባቶቻችን እና እናቶች በከፈሉት መሰዋእትነት ነው ብለዋል። በጊዜው የነበሩት አርበኞቻችን ታላቅ ነበሩ፤ ሀገር መገንባት ከባድ ነው ማፍረስ ግን ቀላል ነው፤ ሁሉም ሀገሩን መጠበቅ አለበት ነው ያሉት። ልጅ ዳንኤል ጆቴ ሰላም በቀላሉ አይገኝም፤ ችግሮች የትም አሉ፤ የኛContinue Reading
 • “የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጀግኖች አርበኞች ነፃ ህክምና እንዲሰጥ ወሰነ
  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጀግኖች አርበኞች በከተማዋ አስተዳደር ስር ባሉ የጤና ተቋማት በሙሉ ነፃ ህክምና እንዲሰጥ መወሰኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል። የከተማ አስተዳደሩ 80ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን ምክንያት በማድረግ ከነፃ ህክምና አገልግሎቱም በተጨማሪ ጀግኖች አርበኞች ማህበር የጠየቀው መሬት እንዲሰጠው መወሰኑንም ምክትል ከንቲባዋ ማስታወቃቸውን ኢቢሲ ዘግቧል። በበአሉContinue Reading
 • የኮሚሽነር አበረ ህልፈት “በነጋዴዎች” እይታና ፤ የሃኪም ትክክለኛው መረጃ ” ቸልተኛነት አይተናል”
  ለኮሚሽነሩ ህልፈተ ህይወት ዋናው ምክንያት የልባቸው ጉዳይ ቢሆንም በወቅቱ ወደ ሆስፒታል ሲመጡም የስኳር መጠናቸው ከ400 በላይ ደርሶ እንደነበር ዶክተር ሀብታሙ ገልፀዋል።   ኮሚሽነር አበረ ህይወታቸው ማለፉ መደረጉን ተከትሎ ” አንድ ጠላት ተቀነሰ” ሲሉ የትህነግ ደጋፊዎች ሰሜታቸውን በደስታ እየገለጹ ነው።  በተመሳሳይ ” ነጋዴዎች” አጋጣሚውን በመጠቀም ገና ከሃዘን ያላገገመውን የአማራ ክልል ለማተራመስContinue Reading

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *