Share and Enjoy !

Shares

የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ በዛሬው እለት ሪፖርተር ጋዜጣ የአውሮፓ መቀሌ በመሄድ ድርድር ማድረጋቸውን የዘገበው ስህተት መሆኑንን አስታወቁ። ሰዎችሁ መቀሌ ሂደዋል መባሉም ሃሰት ነው አሉ። ዜናውን ማስተባበል የተፈለገው የህብረቱ የአዲስ አበባ ሰዎች ማስተባበያ እንደሚያወጡ በመሰማቱ እንደሆነ ዛጎል ሰምቷል።

አቶ ጌታቸው በግል የቲዊተር ገጻቸው ይፋ እንዳደረጉት የአውሮፓ ልዑክ ወደ መቀሌ አላመራም። ሪፖርተር እሳቸው ጠቅሶ ከልዑክ ቡድኑ ጋር በአካል ወይይት ተደርገ በሚል የተዘገበውን ዜና ” እጅግ አሳሳች” ሲሉ የገለጹት አቶ ጌታቸው ቃል በቃል ” በቅርቡ ምንም የአውሮፓ ልዑክ ወደ ትግራይ አልመጣም” ብለዋል።

ለህብረቱ ምክትል ሃላፊ ስለ ህወሃት አቋም ማስረዳታቸውን፣ ይህንንም ያደረጉት በዘመኑ ቴክኖሎጂ እንጂ በአካል አለመሆኑንን አቶ ጌታቸው ይፋ አድርገዋል። ስለውጤቱም ሆነ ስለ ተደረገው ውይይት፣ መቼ ወይም ከምን ያህል ወር በፊት በስም ላልጠቀሷቸው ሃላፊ ማብራሪያ እንደሰጡ ግን ይፋ አላደረጉም።

Related stories   አባይ ወልዱና ዶ/ር አብርሃም ተያዙ፤ የአገር መከላከያ ሰራዊትን ከሃጂ ጀነራሎችና መኮንኖች ከነጭፋራቸው ተደመሰሱ

አቶ ጌታቸው ይህንን ቢሉም ዜናውን ያተመው ሪፖርተርም ሆነ ከሪፖርተር ዜናውን ወሰደው ያሰራጩና ያነበቡ ሚዲያዎች ማስተባበያ ስለማውጣታቸው ይህ እስከታተመ ድረስ አልታወቀም። አቶ ጌታቸው ዜናውን ባያርሙትም አውሮፓ ህብረትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ሊያወጡ እንደሚችሉ ግምት ነበር። ይሁን እንጂ ዛጎል አቶ ጌታቸው ጋዜጣውን ሳይጠብቁ እርምት ያሰራጩት ይህንኑ ስመተው ነው። ሪፖርተር በፊት ለፊት ገጹ ዜናውን ማተሙ ይፋ እንደሆነ በሶሻል ሚዲያዎች የዜናው ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኖ ውሎ ነበር፤

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *