የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶከተር ደብረጽዮን ገ/ ሚካኤል የትግራይ ሕዝብ ዝግጅቱን አጠናክሮ እንዲጠብቅ ማሳሰባቸውን “አሁን የደረሰን ዜና” ዜና ሲል የትግራይ ማስ ሚዲያ ኤጀንሲ አስታወቀ።
በወለጋ ጉሊሶ እጅግ ዘግናኝ የተባለ የጅምላ ጭፍጨፋ በአማራ ተወላጆች ላይ መፈጸሙን ተከትሎ የትግራይ ሕዝብ ዝግጁ እንዲሆን ጥሪ ያቀረቡት መስተዳድሩ የሃይል እርምጃ መወሰዱን ጠቁመዋል።
የሃይል እርምጃ ወሰደ ሲሉ የከሰሱት የፌደራል መንግስትን ሲሆን የትና መቼ እርምጃው እንደተወሰደ በይፋ የተገለጸ ነገር የለም። በደፈናው ህብረተሰቡ ዝግጅቱን እንዲያጠናክር ጥሪ ያስተላለፉት ርዕሰ መስተዳድሩ የዝግጅቱን አይነትም አልጠቆሙም።
ህወሃት ከገዢው ፓርቲ ራሱን ካገለለ በሁዋላ እየተካረረ የሄደው ልዩነት ዋና መንስዔ ለበርካቶች ግልጽ ባልሆነበት ሁኔታ ህወሃት ሰፊ ቁጥር ያለው ሚሊሻና ልዩ ሃይል መልምሎ ሲዘጋጅ እንደነበር ይታወቃል። በተላያዩ ጊዜያት እንደተደመጠው ክልሉ ቀለብ በማዘጋጀት፣ ምሽግ በመቆፈርና የጦርነት ዝግጅት በማድረግ ላይ መቆየቱ የሚታወስ ነው።
Related stories   " ሟቾችን በተመለከተ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው " ኦሮሚያ ክልል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *