የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በምዕራብ ወለጋ ዞን በተፈጸመው ጥቃት ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር ሰላሳ ሁለት እንደሆኑ፣ ጥቃቱን የመራውና ያቀነባበረው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር እያለ ራሱን የሚጠራው ቡድን ከኦነግ ሸኔ ጋር እንደፈጸሙት ተገለጸ። ከድርጊቱ ፈፃሚዎች የተወሰኑት መያዛቸው ታውቋል።
በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ ቀበሌ በተፈጸመው ጥቃት ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር ሰላሳ ሁለት እንደሆነ የገለጹት
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ ናቸው። ኮሚሽነሩ  ዛሬ ማምሻውን ለኢቢሲ እንዳሉት፤ በጥቃቱ የተነሳ የተፈናቀሉ 200 ያህል አባወራዎችን ናቸው።
የዞኑ አስተዳደር ለአማራ ቲሌቪዥን እንዳሉት ጥቃት አድራሺዎቹ ከብት በመጠበቅና እርሻቸው ላይ የነበሩ ሰላማዊ ሰዎችን ስብሰባ ጠርተው ጥድ ዛፍ ስር ከሰበሰቡ በሁዋላ ነው የገደሏቸው። ግድያው እጅግ ዘግናኝ ሲሆን ሕዝብ እንዲያየው ቀረጻው ሲጠናቀቅ አየር ላይ እንዲውል እንደሚላክ አስታውቀዋል።
መኖሪያ ቢቶችን፣ የሰብል መጠበቂያ ማማዎችን፣ በጎተራ ያለ እህል በእሳት ያጋዩት ወንበዴዎች 800 የሚሆኑ ክብቶችና ክብቶቹን እንዲነዱ አስር የሚጠጉ ሰዎችን አግተው መውሰዳቸውን አስተዳዳሪው አመልክተዋል።
በተፈጸመው ጥቃት 23 ወንድና 9 ሴቶች በድምሩ 32 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የገለጹት ኮሚሽነር ጄኔራሉ፤ 10 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና እየተከታተሉ እንደሚገኙ አመልክተዋል።
በጥቃቱ የመኖሪያ ቤቶችና አንድ ትምህርት ቤት እንደተቃጠለ ተናግረው፤ ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር በመተባበር መልሶ የማቋቋም ስራ መጀመሩን ገልጸዋል።
የጥቃት ድርጊቱን የፈጸመው አካል ኦነግ ሸኔ መሆኑን ገልጸው፤ ከጀርባ በመሆን የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) እየደገፈው እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በተለይም ቡድኑ የታጠቃቸው እንደ ስናይፐርና ብሬል ያሉ የጦር መሳሪያዎች ህወሃት ያስታጠቀው እንደሆነ ገልጸዋል። ከኦነግ ጀርባ በመሆን ህወሃት በህብረተሰቡ ላይ ጥፋት እያደረሰ እንደሆነም ገልጸዋል።
ጥቃት የተፈጸመበት ቀበሌ ከወረዳ ከተማ በ75 ኪሎ ሜትር የሚርቅ መሆኑን ገልጸው፤ ህወሃት በብሔሮች መካከል ግጭት ለመፍጠር በስሌት የፈጸመው ተግባር ስለመሆኑ ማረጋገጫ መኖሩን ተናግረዋል። ትህነግ ይህ ከሆነ በሁዋላ አስቀድሞ ለክልሉ ህዝብ ራስህን አዘጋጅ የሚል ጥሪ በዶክተር ደብረጽዮን አማካይነት ተላልፏል።
ከድርጊቱ ፈጻሚዎች መካከል የተወሰኑት መያዛቸውን ያመለከቱት ኮሚሽነር ጀነራሉ  ቀሪዎቹን ለመያዝ አሰሳው ቀጥሎ  እንደሚገኝ ገልጸው፤ ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይፈጸም ከህብረተሰቡ ጋር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የመከላከያ ሰራዊት፣ የኦሮሚያ ልዩ ሃይልና የፌደራል ፖሊስ በሶስት አቅጣጫ ከበባ አድረገው ወንበዴዎቹን እያሰሱ መሆኑንን መንግስት አስታውቋል።
የአማራ ክልል፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ የኦሮሚያ ክልልና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ” ይህንን ተጋባር ከሚፈጽምና ከሚያስፈጽም ቡድን ጋር በዚህ መልኩ መቀጠል ስለማይቻል በቃ ሊባል ይገባል” ለሚለው የህዝብ ጥያቄ መልስ ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን የሚያመላክት መግለጫ በየፊናቸው አውጥተዋል።
 • የቻይናው ሮኬት ስብርባሪ በኢትዮጵያ ቢወድቅ ምን ዓይነት የጥንቃቄ እርምጃዎች ሊወስዱ ይገባል?
  ከቁጥጥር ውጪ የሆነው የቻይና ሮኬት አካል ስብርባሪ በኢትዮጵያ ቢወድቅ ምን ዓይነት የጥንቃቄ እርምጃዎች ሊወስዱ ይገባል? ። የቻይናው 5 ቢ ሮኬት ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ወደ መሬት ለመምዘግዘግ ምድርን በመሽከርከር ላይ ይገኛል። 5 ቢ ሮኬት ከቁጥጥር ውጭ ከሆነበት ከሚያዝያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. እንስቶ በከፍተኛ ፍጥነት በመሬት ዙሪያ እየተሸከረከረ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ስፔስContinue Reading
 • ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መግለጫ
  ጠላቶቿ ፈርሰው ያልቃሉ እንጂ ኢትዮጵያ መቼም አትፈርስም፤ አዲስ አበባም ከሰላማዊ የብልፅግና ጉዞዋ አትስተጓጎልም! ሀገራችን ኢትዮጵያ በታሪኳ ለበርካታ ጊዜያት ከውጭ ጠላቶች ወረራ እና መሰል ጥቃቶች ተሰንዝሮባታል፤ ሁሉንም የውጪ ወረራ እና ጥቃቶችን በጀግኖች ልጆቿ በመመከት ጠላትን አሳፍራ መመለስ የቻለች ሲሆን በአንፃሩ ደግሞ ከአብራኳ የወጡ ከሃዲዎች እና ባንዳዎች ከውጭ ጠላት ጋር በማበር ሲያደሟትContinue Reading
 • አቡነ ማቲያስ መነጋገሪያ ሆነዋል – ኢትዮጵያ ላይ ዘመቻው እንዲከር ጥሪ አቅርበዋል
  ከትሀንግ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው መረጃ የተያዘባቸው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ሰፊ መነጋገሪያ ሆነዋል። በአዎንታና በአሉታዊ ጎን የተሰነዘረባቸው ተቃውሞ መነሻው ” ታፈንኩ” በማለት ሲናገሩ የሚያሳይ ቪዲዮ ወዳጆቻቸው ወይም የቅርብ ታዛዦቻቸው ካሰራጩና ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በኤፒ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ በቲውተር ገጻቸው ካሰራጩት በሁዋላ ነው። ቪዲዮውን ተከትሎ ሙስሊም የኢትዮጵያ ልጆች የአፍጢር ስነContinue Reading
 • Warshaan Keenyaa tiraaktaroota 950 qonnaan bultootaaf dabarse
  Magaalaa Shaashamanneetti kan argamu Warshaan Meeshaalee Qonnaa Ammayyaa Keenyaa kaleessa tiraaktaroota 950 qonnaan bultootaaf dabarse. Sirni walharkaa fuudhiinsaas qonnaan bultoota, dargaggoota waldaan gurmaa’aniifi dhaabbata Keenyaa gidduutti taasifameera. Sirnicharratti Pirezdaantiin Mootummaa Naannoo Oromiyaa, Obbo Shimallis Abdiisaa dabalatee hoggantoonni olaanoo federaalaafi naannolee, akkasumas abbootiin gadaa argamaniiru. Tiraaktaroota 950 qonnaan bultootaafi dargaggoota waldaanContinue Reading

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ዶክተር አብራሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *