በስግብግቡ የሕወሓት ጁንታ ኃይል ላይ የተደረገው የመጀመሪያው ዙር ኦፕሬሽን በስኬት እንደተጠናቀቀ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታውቀዋል።

የአየር ኃይሉ በወሰደው እርምጃም በተለያዩ ስፍራዎች ላይ የነበሩ ሮኬቶችን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ሙሉ በሙሉ ለማውደም መቻሉንም ገልፀዋል።

“የአየር ኃይሉ በወሰደው እርምጃ በተለያዩ ስፍራዎች ላይ የነበሩ ሮኬቶችን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ሙሉ በሙሉ ለማውደም ተችሏል። እነዚህ ሮኬቶች እስከ 300 ኪሎ ሜትሮች መወንጨፍ የሚችሉ በመሆናቸው እና በወንጀለኛው ቡድን ሮኬቶቹን የመጠቀም ፍላጎት በመኖሩ በመቐለ እና አካባቢዋ በነበረው የከባድ መሣሪያ ማስቀመጫ ላይ የአየር ኃይሉ እርምጃ እንዲወስድ ተደርጓል” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ።

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

አምባገነኑን እና ዘራፊውን የጁንታ ቡድን በአጭር ግዜ ውስጥ ይዘን ለፍርድ በማቅረብ ወደ ልማታችን እና እርሻችን ሰላማችን እንመለሳለን በማለት የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አህመድ አስታውቀዋል። (ኢቢሲ)

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *