ጥቅምት 24 qen ዓ.ም እኩለ ሌሊት ትህነግ በመቀሌ የሚገኘውን የሰሜን እዝ ላይ ድንገተኛ ጥቃት በመክፈት ክህደትፈፀመች። በተመሳሳይ በዚህ እለት በዳንሻ የሚገኘውን የጦር መሳሪያ ካንፕ ለመዝረፍ አቅዳ ተንቀሳቅሳለች።
በዳንሻ የሚገኘውን የጦር ካምፕ ለመዝረፍ ትህነግ ቀድማ ስለመዘጋጀቷ በዳንሻ የሚገኙ የጦር ካምፕ መሪወች ምናልባትም ከጥቂት የትግራይ ተወላጅ የሰሜን እዝ አባላት ውጭ መረጃ ያለው ሰው አልነበረም።
ትህነግ በካምፑ የሚገኘውን ዘመናዊ የጦር መሳሪያወች ለመዝረፍ ወደ ካምፑ ድንገተኛ ተኩስ ከፈተች። የጦር ካምፑ መሪወች ከነበሩት መካከል ጄኔራል ሙሉአለም በዙሪያው ያሉትን ወታደሮች በማስተባበር ድንገተኛውን ጥቃት መመከት ጀመሩ።በዚህ ወቅት ነው እንግዲህ አንድም አስገራሚ በሌላ በኩል ደግሞ አሳዛኝ ክስተቶች የተፈጠሩት።
ከአሳዛኙ ክስተት እንጀምር:-
በዳንሻ የሰሜን እዝ የጦር ካምፕ ውስጥ ከሚገኙ የጦሩ አመራሮችና ወታደሮች መካከል አብዛኞቹ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ወታደሮች ከዘራፊው የትግራይ ልዩ ሀይል ጎን በመሰለፍ በነ ጀኔራል ሙሉአለም ላይ እና በመላ ኢትዮጵያዊያን ላይ ክህደት ፈፅመዋል።
አስገራሚው ክስተት ደግሞ እንሆ:-
ቁጥራቸው 4 የሚሆኑ የትግራይ ተወላጅ የጦር ካምፑ መሪወችና ወታደሮች ደግሞ ህውሓት የኢትዮጵያ ጠላት ናት። የኢትዮጵያን መከላከያ በመውጋት ታሪክ ይቅር የማይለው ክህደት ፈፅማለች። በሚል ከነ ጀኔራል ሙሉአለም ጋር በመወገን ጥቃቱን በመመከት ተባብረዋል ።
ጥቃቱን ለመመከት የተደረገው ተጋድሎ ባጭሩ:-
በሁለቱም ወገን ለ 20 ሰዓታት የፈጀ ከባድ የቶክስ ልውውጥ ተካሂዷል። እነ ጄኔራል ሙሉአለም እና ታማኝ ጓደኞቹ ድንገተኛ ጥቃት በመፈፀም የጦር መሳሪያ ለመዝረፍ አሰፍስፎ የመጣውን የተደራጀ የትህነግ ልዩ ሀይል በመመከት ትልቅ ጀብድ ፈፅመዋል ።
በዳንሻ የሚኖሩ የአማራ ተወላጅ ሚኒሻወች ፤የአማራ ልዩሀይሎችና ሚኒሻወች ደግሞ ወደ ካምፑ ፈጥነው በመድረስ ለነጄኔራል ሙሉአለም እና የሰሜን እዝ የጦር አባላት ደጀንነታቸውን በተግባር አስመስክረዋል።
በአጠቃላይ ትህነግ አቅዳው የነበረውን የከባድ መሳሪያ ዝርፊያ በጀግንቹ ከባድ ተጋድሎ ከሽፋል። ያልጠበቀችውን ኪሳራ ተከናንባ ወደ መጣችበት እንድትፈረጥጥ አድርገዋል።
በዚህ ታሪካዊ ተጋድሎ ጄኔራል ሙሉአለም እና ለሀገር ህልውና ሲሉ ተጋድሎ የፈፀሙት ታማኝ የትግራይ ተወላጅ የመከላከያ አባላት መካከል መጠነኛ የመቁሰል አደጋ ቢገጥማቸው ሁሉም በህይወት ተርፈዋል።
አጠቃላይ ምስጋና!
ምስጋና 1:-
ለሰሜን እዝ የመከላከያ አባላት፤ለጄኔራል ሙሉአለም እና ለታማኝ የትግራይ ተወላጅ የመከላከያ አባላት፤
ምስጋና 2:-
በዳንሻ ለሚኖሩ የአማራ ተወላጅ ሚኒሻወች፤ የአማራ ልዩ ሀይል እና ለሚኒሻ አባላት
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
ድል ሳይወድ ተገዶ ወደጦርነት ለገባው የመከላከያ ኃይላችን !
ድል የእብሪተኞች የንቀት በትር ደጋግሞ ለቀጠቀጠው ልዩ ኃይላችንና ሚሊሻችን !
©Rational View

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   የምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ አቅል ያጣ ፍላጎት ግን ምንድን ነው!?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *