“እኛም አረፍን፣ የትግራይ ህዝብም አረፈ፣ እነሱም እስከወዲያኛው አረፉ” እንል ዘንድ ጊዜው ቀርቧል። በየትኛውም ዓይነት የሃዘን ዱላ ቢመቱንም ከፊታችን ያለው ድል ያበረታናል። ምንም ቢያሴሩም ካሁን በሁዋላ የቀብሩን ቀንና ሰዓት የመቀየር አቅማቸው ተሽመድምዷል። ቢዘላበዱም የደም አበላቸው አናታቸው ላይ እንደወጣ ስለገባን አይደንቀንም። ጭፍሮቻቸውንና ሲሰርሯቸው የነበሩት ቢያቅራሩም ድሉን ሊጎትቱት አይችሉም። ያፈሱትን ሲረጩ ውለው ቢያድሩ የደኸያሉ እንጂ ጠብ የሚል ነገር የለም። ሲያላዝኑ ቢውሉ ኑዛዜ እንጂ ቁብ እንደሌለው ይገባናል። ዛጎል እንዲህ ታምናለች።

ጥቃቅን የሚባሉትን ቀንበሮችና የዘር አፓርታይዱን ጥቅል የግፍ መዘገብ ሳንቆጥር እጅግ በርካታ ልዩ መራራ ቀናትን አሳልፈናል። ዛሬም መራር ቀን ላይ ነን። ገና መራራ ቀናት ሊያጋጠሙን ይችላሉ። አንገታችንን ለመስበርና ተስፋ ለማስቆረጥ የማይማስ የክፋትና የጭራቅ ተግባራት ውጤቶችን ልንሰማ እንችላለን። ለምን? በደም ተረግዞ፣ በደም ፋፍቶና በደም ዛር አዶ ከርቤ የሚደልቀው ጭራቅ ትህነግ አለና!! የት? በርሃ፣ ቢሮ፣ ከተማ፣ ገጠር፣ ገበያ ቦታ …

ነገሩን ሊገለብጡ የሚፈልጉ ባንዳዎችና ትራፊ ለቃሚዎች ” የርስ በስ ጦርነት” ብለው ቢያላዝኑም። ርካሽነታቸውን በወገን ደም ላይ በመደነስ ቢያሳዩንም፣ በተወጉት ገንዘብ መጠን ላንቃቸው እስኪቀደድ በወገኖቻችን አሰቃቂ ህልፈት ቢያላግጡም፣ ዛሬ ዘመቻው ደም ቀለቡ ከሆነው የኢትዮጵያ እንግዴ ልጅ ትህነግና በቁጡው የኢትዮጵያ ህዝብ መካከል በመሆኑ የሃዘናችን ማብቂያ እንደደረሰ ይሰማናል። ተስፋችን አይሞትም። ይልቁኑም ጀግንነት እንላበሳለን። ለዚህም ነው ደጀኑ ከግንባሩ በላይ እሳት የጎረሰው።

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

እኚህ የበሉበትን ወጪት ሰባሪ ባንዳዎች፣ የጠጡት ደም እረፍት ነስቷቸው ሌላውን የሚያውኩ የቀትር እባቦች፣ ዘርፈው የማይጠግቡ ጅቦች፣ ሃጢአት ያረከሳቸው የሶዶም ውላጆች፣ እስከዛሬ የፈጸሙት አልበቃ ብሏቸው በረሃ ምሽግ ውስጥ ውሎ እያደረ እድሜውን የፈጀውን ወገኖቻችንን በሉ። እነሱ በሲሰኝነት ሲናውዙና አገር ሲዘርፉ ሃሩር እየበላው ጉድጓድ ውስጥ ነብስ አውቆ የጎለመሰውን ወገናችንን ቆሉት። ሳያስበው በቅጥረኞቻቸው አማካኝነት በተኛበት ረሸኑት። ባደፈውና ሃጢያት አለት ባደረገው ልቡናቸው እየተነዱ አስከሬኑንን እርቃን አድርገው ከበሮ መቱ። ደነሱ። ጀገኑበት። ደም ምሳቸውና ደሙን ጠጡት። ይህን ስንሰማ ታመምን። ይህንን ስንሰማ የቆሽታችን እራሪ እስኪሸተን ሃዘን ተሰማን። ግና አልተሰበርንም። መከራ ጀግኖችን ይወልዳላና የፍትህ አምላክ ታግዞ ቀና አልን።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

በዚህ አላበቃም። ማይካድራ ነጹሃንን በሉዋቸው። ረሸኗቸው። ደማቸውን እንደጎርፍ አጎረፉት። የጎረፈውን ደም ለምሳቸው ዳልቻ አህያ ላይ ተቀምጠው ጠጡት። ተቀቡት። እነ ደም ቀለቡ አስከሬን በሉ። ጠገቡ። የጠጡት ትኩስ ደም አስክሯቸው ከበሮ መቱ። ጀግናው የመከለከያ ሰራዊት አንገታቸውን ሊያንቅ በተቃረበበት የፍጻሜው መጀመሪያ ይህን ሰማን። ክፉኛ አዘን። እነሱ ትኩስ የንጹሃን ዜጎችን ደም ሲጋቱ ኢትዮጵያ ከዲቃላ ልጆቿ ሲቀሩ ደም አነባች። ወዲያው ግን በቆራጥ ልጆቿ ፍርድን ልታጸና ጉዞ ላይ ስለሆነች ቀበቶዋን አጥብቃ ” ሰይጣን በምን ጣዕሙ” ተብዬዎችን ታሳድድ ገባች።

ኢትዮጵያዊያን በማይካድራ ብቻ ሳይሆን ቀደም ሲል በየቦታው ያላየነው የሞት አይነት የለም። ያላሳዩን የጭካኔ ልክ የለም። ያላሳዩን የዕብሪት አይነት የለም። ያላሳዩ የዝርፊያ ጥግ የለም። ክህደትንና ሸፍጥን አስኮምኩመውናል። እኒህ እንግዴዎች አገራችንን ተዛብተውባታል። እየጠሏት መጥምጠዋታል። በሃሰት ትርክታቸው አባልተውናል። ዛሬ የእርስ በእርስ ጦርነት እንደሚነሳ የሚሰብኩን የእንግዴ ልጆቹ እራፊዎች እንደሚሉት ግጥሚያው በአብይና በትህነግ ጭራቆች መካከል አይደለም። በኢትዮጵያ ሕዝብና በጭራቁ የገሃነቡ ንጉስ የሉሲፈር ሽንት ውጤት በሆኑት ጭራቆች መካከል ነው።

Related stories   ደመቀ መኮንን በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሚመራ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

ዛሬም፣ ነገም የበሰበሰ ምን አይፈራም እንደሚባለው ይህ የአጋንንት ሽንት ውጤት የሆነ ቡድን ሌላ በደኖ፣ ሌላ ኢሬቻ፣ ሌላ ጋምቤላ፣ ሌላ መተከል፣ ሌላ ጉሊሶ፣ ሌላ ጉርዳፈርዳ… ሌላ ማይካድራ ሊደገም ይችላል። ይህንን ማስቆም የምንችለው እኛ ዜጎች ብቻ ነን። አለኝታችን መከላከያ ስራውን እየሰራ ነው። ደጀኑ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ እንደ ትንታግ እየነደደ የበቀል በትሩን እያሳረፈ ነው። ደጀኑ ድጋፉን እያጎረፈ ነው። አገር በአንድ ተነስታ የህንን ጁንታ ስትመክት፣ ልጆቿ የየቀዬያቸው ዘብ ሲልሆኑ ጭራቁ ተስፋ ይቆርጣል። እንደ ሎጥ አምድ፣ መርዝ እንደበላች አይጥ ይፈዛል።

ይህ ምስኪኑን የትግራይን ህዝብ አግቶ ደም እየተጋተ ያለ ቡድን የኢትዮጵያ አምላክ፣ የናቶች ለቅሶና የሰራው የግፍ ክምር አንድ ላይ ሊደረመስበትና ልናርፍ በጫፍ ስለሆን እንተባበር። በየሰፈራቸን አንድም ነገር ኮሽ እንዳይል አካባቢያችንን እንጠብቅ። ድሉ በሕዝብ አቆጣጠር ተቃርቧልና ” የትግራይ ህዝብም አረፈ፣ እኛም አረፍን፣ እነሱም እስከወዲያኛው አረፉ” እንላለን።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

የዛጎል አቋም!!

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *