“የጁንታው ፀሐይ እየጠለቀች ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የህግ ማስከበሩ ዘመቻ ወደ መገባደጃው መቃረቡን አስታወቁ። የትግራይ ሕዝብ በጁንታው ቡድን መከራ እያየና ሲያይ የኖረ ሕዝብ እንደሆነም ጠቅሰዋል።
“ይሄንን መርዶ ጁንታው በቁሙ ተረድቶታል” በማለት ጁንታው ቡድን ጸሃይ እንደጠለቀበት የተረዳበትን አግባብ በቲውተር ገጻቸው ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ጁንታው ” አሁን የሚይዘውን የሚጨብጠውን የሚያጣበት ጊዜ ነው። በጣዕር መንፈስ በየቦታው የመጨረሻውን የጥፋት ድግስ ይደግስ ይሆናል” ብለዋል።

ሱሉሱ የዞረበት የደደቢቱ ሽፍታ ሲመሽ በርካታ የተስፋ መቁረጥ አስከፊ ወንጀሎችን ሊያከናውን ስለሚችል አብይ አህመድ “ሕዝቡ በንቃትና በተደራጀ መንገድ አካባቢውን እንዲጠብቅ አደራ እላለሁ” የሚል ጥሪ አስተላልፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ከማለታቸው ቀድሞ ሕዝብ በያለበት ራሱን አደራጅቶ አካባቢውን እየተበቀ እንደሆነ፣ በአዲስ አበባ ብቻ አንድ ቀን ውስጥ ከሁለት ሺህ በላይ የጥቆማ መልዕክት መስጠቱን፣ ከዚህም ውስጥ ከዘጠና በመቶ በላይ ትክክለኛ ጥቆማ መሆኑንን አዳነች አቤቤ ከቀን በፊት ከምስጋና ጋር ማስታወቃቸው ይታወሳል።
ጀንበር ከመጥለቋ ጋር በተያያዘ “የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ወገኖቻችን በየአካባቢያችን ምንም ዓይነት አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳይደርስባቸው ሁላችንም የወንድሞቻችን ጠባቂ እንሁን” የሚል ጥሪ ያስተላለፉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፣ ” የኢትዮጵያ ጠላት ስግብግቡ ጁንታ ነው። የትግራይ ሕዝብ እንደሌላው ሕዝብ በጁንታው መከራ ያየ ሕዝብ ነው። ጁንታው ለፍርድ እንዲቀርብ የትግራይም ሕዝብ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር አብሮ እየተዋጋ ነው። አካባቢዬን እጠብቃለሁ፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ የመከራ ቀንበር እሰብራለሁ። ጁንታውን ለፍርድ አቀርባለሁ – ይህ ነው ቃል ኪዳናችን” ብለዋል።
በተለያዩ ግንባሮች የተገኘውን ድል ተከትሎ የዘመቻው መሪዎች እንዳስረዱት የትግራይ ሰላማዊው ሕዝብ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ሰጥቷል። አብሮ ተዋግቷል። መከላከያ በተቆጣጠራቸው ከተሞች ሕዝቡ ከትግራይ ወገኖቹ ጋር ተጋብቶ በፍቅር እንደሚኖርና ችግሩ ያለው ከጁንታውና አረመኔው የህወሃት መሪኦውችና ጋሻጃግሬዎች ጋር ብቻ መሆኑንን ሲናገሩ ተሰምቷል።
- ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸውበጦርነት የተመታውና ህልውና ሙሉ በሙሉ እንዳከተመለት የተነገረለት ትህነግ በዲፕሎማሲ አስደንጋጭ ቀውስ እንደገጠምው ተሰማ። ሌት ከቀን ሲሟገቱላቸው የነበሩ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች “ አዋረዳችሁን” ሲሉ ሃዘናቸውን እንደገለጹላቸው ታወቀ።Continue Reading
- መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋልሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የጁንታውን ሃይል በከፍተኛ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቁ። ” ጁንታው ካሁን በኋላ ሰራዊትና ጠባቂ ይዞ መንቀሳቀስ አይችልም”Continue Reading
- Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho… To set the record, Mr. Obang, my self as part of his admirers and supporters, started out his career in search of justice for hisContinue Reading
- ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫኢዜማ አዲስ አበባ ላይ ካሸነፈ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግለሰብ ንብረት በሁለት ዓመት ውስጥ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ። የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ነጋ ለዓመታት እንደ ፖለቲከኛም ሆነ እንደContinue Reading
- “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገውአዲስ አበባ በጥናት የተዘረፉ ዜጎች ቁጥር ቀላል አይድለም። ስም መጥቀስ አያስፈልግም እንጂ ያለውን አስረክቦ በባልደረቦቹ ድጋፍ ከእብደት የዳነ ስፖርተኛ ታላቅ ምሳሌ በሆነ ነበር። አንድ በህይወትContinue Reading