በርካታ ፈቃደኞች የህግ ማስከበር ዘመቻውን ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን በፍጥነት ለማጠናቀቅ ጥያቄ እያቀረቡና እየተቀላቀሉ ባለበት በአሁኑ ሰዓት ጎን ለጎን በርካታ አካባቢዎች ከትህነግ ቁጥጥር ውጪ መደረጋቸው እየተገለጸ ነው። ዛሬ በወጣው መረጃ አክሱም አየር ማረፊያ ሙሉ በሙሉ በወገን እጅ ገብታለች።

ሌፍተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ በትናትናው እለት በሰሚን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈጸመውና ” ሰይጣን ይሻላል” ያሰኘውን ጭካኔ የተሞላው የክህደት ተግባር ሲያስረዱ ነገና ዛሬ በርካታ ድሎች ይፋ እንደሚሆን ፍንጭ ሰጥተው ነበር። ጀነራሉ ሕዝብን ባስቆጣውና እልህ ውስጥ በከተተው መግለጫቸው ሰራዊቱ የተፈጸመበትን ክህደትና ጭፍጨፋ ተቋቁሞ ዳግም በመደራጀት ማጥቃት መቀጠሉንም በይፋ አስታወቀው ነበር።

ዛሬ ማለዳ ላይ እንደተሰማው የአክሱ አየር ማረፊያና ከተማዋ ሙሉ በሙሉ ” ጁንታ” በሚል ስያሜ ከሚጠራው የትህነግ መዳፍ ተላቃለች። ጁንታው በአክሱም አየር ማረፊያ አካባቢ ጠንካራ ምሽግ የገነባና ሰፊ የመከላከያ መስመር ያደራጀ በመሆኑ ከባድ ትንቅንቅ መደረጉን መረጃዎች ያስረዳሉ።

የጥቃቱን ስፋራ በዝርዝር ባይገልጹም የአየር ሃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄነራል ይልማ መርዳሳ ” እንዳሻን እየተመላለስን ደብድበናል” በማለት ጁንታው ያከማቸው የጦር መሳሪያና የነዳጅ ዲፖ እንዲሁም የተመረጡ ኢላማዎች ከጥቅም ውጭ እንደሆነ ዛሬ ለመንግስት ሚዲያዎች ተናግረዋል። ጥቃቱ ጁንታው እጁን እስኪሰጥና የህግ ማስከበሩ ስራ እስኪተናቀቅ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል። ጀነራሉ የጁንታው  አፈ ቀላጤ አየር መተን ጥለናል በሚል ላሰራጨው ዜና ” እንዳሻን በመመላለስ ደብድበናል። ህዝብ እንዳይነካ በሚል ቦታው ላይ ደርሰን ድብደባ ሳንፈጽም ተመልሰናል” ሲሉ በአየር ክልሉ ላይ አየር ሃይሉ ምን ያህል እንደተንሸራሸረ በመግለጽ ተሳልቀውበታል።

Related stories   ደመቀ መኮንን በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሚመራ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

ከዚሁ ጋር በተያያዘ

የሁመራን አይር ማረፊያና ሁመራ  አካባቢን ሙሉ ለሙሉ የተቆጣጠረው የአገር መከላከያ ሰራዊት ጥቃቱን አስፍቶ በአሁኑ ሰዓት እስከ ሽራሮ ያለውን ቦታ በመሸፈን የተለያዩ ስፍራዎችን በቁጥጥር ስር እያዋለ እንደሚገኝም የኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ አስታውቀዋል።
ሰራዊቱ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ለሚኖሩ ሰዎች ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ የእርዳታ ድርጅቶች ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር ተነጋግረው ድጋፍ ማድረግ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።
የህወሃት ጁንታ በአልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የኤርትራ መከላከያ ሰራዊትን መለዮ በማዘጋጀት ላደራጃቸው ታጣቂዎች በማልበስ ኤርትራ እንደወረረች በመግለጽ ህዝብን እያደናገረ እንደሆነም መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል። በዚህ የተቀናበረ ድራማ ህዝቡ ሳይታለል ለመከላከያ ሰራዊቱ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል መሀመድ ተሠማ ፣ ጀግናው ሠራዊታችን ማይካድራን ፣ ራውያን ፣ ሁመራ ከተማንና በዙሪያው ያሉ ቦታዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉንና የተገኘውን ድል ለማስጠበቅም ወደ አዲጎሹ እየገሰገሰ እንደሚገኝ አረጋገጡ ።
በዚህ ግንባር በተደረገ ውጊያ ፣ ህብረተሰቡ ምንም ዓይነት ጉዳት ሳይደርስበት ፣ ሠራዊታችን የነውጠኛው ታጣቂ ላይ ብቻ በማተኮር ሲቀነድበው ውሏል ።
ሜ/ጀ መሀመድ እንዳሉት ፣ በዚህ ውጊያ በርካታ ሰው ተማርኳል ፤ ቦታዎችና ንብረቶችም በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ፣ ሠራዊታችን በገባባቸው ቦታዎች ሁሉ የትግራይ ህዝብ ከፍተኛ ድጋፍ እየሰጠው ይገኛል ።
በሌሎች ግንባሮች ያለው ውጊያም ፣ በሠራዊታችን አጥቂነት ፣ በትህነግ ማፈግፈግ እንደቀጠለ ይገኛል ብለዋል ።
ሠራዊታችን የተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ፣ ጁንታው ምሽግ እንጂ ልማት ያልሰራባቸው በመሆኑ ፣ የረድዔት ድርጅቶች ከሚመለከተው የመንግስት አካል በመነጋገር ህዝቡን እንዲደግፉ ጥሪ አስተላልፈዋል ።
ፅንፈኛው ፣ ጭፍሮቹን ፣ የኤርትራን ዩኒፎርም አስለብሶ ለፕሮፓጋንዳ የሚያሳየው የተለመደ ድራማ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ፣ ልዩ ሀይል የሚላቸውን ሲቪል በማልበስ ባዶ እግራቸውን እንዲዋጉ በማድረግ ሲማረኩ ፣ የኢትዮጵያ ሠራዊት ሲቪሎችን ወጋ በማለት ቅጥፈትን ስራው አድርጎታል ።
ለጁንታው የታጠቁ የትግራይ ልጆች ለሠራዊታችን እጃቸውን እንዲሰጡ ሜ/ጀ መሀመድ ጥሪያቸውን አቅርበዋል ።

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *